በቁርኣን ውስጥ የምናገኛቸው ልብ የሚያሞቁ ታሪኮች
#ሱራቱ_አት_ተውባህ
ነቢዩ ሙሐመድ (ሰለላሁአለይሂ ወሰለም) እና አቡበክር (ረዲዓላሁ ዐንሁ) ከቁረይሾች ለመደበቅ ዋሻ ውስጥ በነበሩበት ወቅት ቁረይሾች ዋሻውን ለመፈተሽ በመጡ ጊዜ አቡበክር ድንጋጤ ላይ ነበርና እንዲህ አሉት: ''አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነው''
[9:40]
ከአላህም በዋሻ ውስጥ እያሉ እርጋታን እና የሸረሪት ድር ዋሻው መግቢያ ላይ መስራቷን ሰበብ አድርጎ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.አ.ወ) እና ሰሃቢውን ጠበቃቸው።
#ሱራቱ_አድ_ዱሀ
ነቢዩ ሙሐመድ () ለ6 ወራት ያህል ዋሂይ አልወረደላቸውም ነበር። አላህ የጠላቸው እና ከነቢይነት የተሰናበቱ መስሏቸው ነበር ፣ በጣምም ተጨነቁ። ከዚያም አላህ ከረጅም ጊዜያት በኋላ ዋሂይ አወረደላቸው...
"በረፋዱ እምላለሁ። በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤ ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡ መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡።'' [93:1-4]
#ሱራቱ_አል_ቀሰስ
አላህ ሙሳ (አለይሂ ሰላም) ህፃን እያለ በጊዜው ህፃናትን እየገደለ ከነበረው ፊርኣውን ለመጠበቅ ለሙሳ እናት ዘንቢል ውስጥ እንድትከተው እና ወንዝ ውስጥ እንድትጥለው ነገራት። እናትየውም ልቧ ተሰብሮ ነበር። ''የሙሳም እናት ልብ ባዶ ሆነ።" (28:10)
አላህም ልቧን ለማጠንከር.. "እኛ ወዳንቺ እንመልሰዋለን» አላት። [28:7] ሙሳም (አለይሂ ሰላም) ያለበት ዘንቢል የፊርኣውን ቤት ገባ እና ፊርኣውን ልጁን ለማሳደግ ተስማማ አጥቢም ቀጠረለት እናቱም አጥቢው ሆና ተቀጠረች፤ ሙሳም ወደ እናቱ ተመለሰ።
#ሱራቱ_አት_ተህሪም
አሲያ በአላህ በማመኗ ምክንያት በባሏ ፊርኣውን እየተሰቃየች እያለች እንዲህ ብላ ዱዓ አደረገች... «ጌታዬ ሆይ! አንተ ዘንድ በጀነት ውስጥ ለእኔ ቤትን ገንባልኝ፡፡'' [66:11]
አላህም ዱዓውን ተቀብሏት በጀነት የሚኖራትን ቤት አሳያትና እሷም ቤቷን ባየች ጊዜ ፈገግ ብላ ስቃዩ በርትቶባት ሞተች።
#ሱራቱ_አሽ_ሹዐራእ
ፊርኣውን ሙሳ (አለይሂ ሰላም) እና ሕዝቦቹን ለማጥፋት እያሳደዳቸው በነበሩበት ጊዜ ሙሳና ሕዝቦቹ ባህር ጋር ደረሱና ሚሄዱበት መንገድ ጠፋቸው ወደኋላ እንዳይመለሱ ፊርኣውን እና ጦሩ አሉ፤ ከዚያም ሕዝቦቹ ለሙሳ በቃ ደረሱብን ባሉ ጊዜ ሙሳ እንዲህ አላቸው...
«ተዉዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፡፡ በእርግጥ ይመራኛል» [26፡62] አላቸው
አላህም እንዲህ አለው... «ባሕሩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክንበት፡፡ (መታውና) ተከፈለም፡፡ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ኾነ፡፡" [26:63]
#ሱረቱ_ዩሱፍ
ነቢዩላህ ዩሱፍ (አለይሂ ሰላም) በወንድሞቹ ጉድጓድ ውስጥ ከተወረወረ በኋላ አባቱ ያዕቁብ (አለይሂ ሰላም) በጣም ከማልቀሱ የተነሳ ዐይነ ስውር ሆኖ ነበር። ልጆቹ ማልቀስ እንዲተው እና ዩሱፍን ከማስታወስ እንዲቆጠብ ቢነግሩትም እሱ እንዲህ ይላቸዋል... «ጭንቀቴንና ሐዘኔንና የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡'' [12:86]
ትግእስተኛ በመሆኑም አላህ ሱብሃነሁወተአላ የማየት ችሎታውን እና ዩሱፍን መለሰለት።
#ሱራቱ_አል_አንቢያ
ነቢዩላህ አዩብ (አለይሂ ሰላም) ጤናው መጥፎ ነበር ፣ ልጆቹ ሞተውበታል ፣ ሕዝቦቹም አግልለውት ነበር ከዚያም አላህን እንዲህ ብሎ ተጣራ... «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» [21፡83]
አላህም እንዲህ አለ ''ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጉዳትም በእርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ አስወገድን። ቤተሰቦቹንም ከእነሱም ጋር መሰላቸውን ከእኛ ዘንድ ለችሮታና ለተገዢዎች ለማስገንዘብ ሰጠነው።'' [21:84]
#ሱራቱ_አል_ካህፍ
አላህ መልካም አባታቸው የሞቱባቸው ለሁለት የቲም ለሆኑት ልጆች ግድግዳ ስር የተቀበረ ሀብት አስቀምጦላቸው ነበር።
የተቀበረውን ሀብቱን በከተማው ያለው ማንም ሰው ማየት አይችሉም፣ ካጠገቡ ይኖሩ የነበሩት ሁለቱ የቲም ልጆችም ቢሆን አይተውት አያውቁም። ልጆቹ ሲያድጉ ግድግዳው ቀስበቀስ እየፈረሰ አላህ እስኪያድጉ የጠበቀላቸውን ሀብት አሳያቸው፡፡
"ላንተ የተፃፈልህ ሪዝቅ አንተ ጋር ይደርሳል፤ ከሁለት ተራሮች መካከል እንኳን ቢሆን!"
ይህን የማያውቁ ብዙ ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ ሼር ፣ ኮፒ ሊንክ ፣ ሪፖስት እና ትንሽዬ ኮመንት በማድረግ እናሳውቃቸው።
“አስታውስም፤ ማስታወስ ምእመናንን ትጠቅማለችና፡፡“
[ሱራቱ አዝ-ዛሪያት 51:551
ነቢዩ () እንዲህ ብለዋል: “አንድን ሰው ወደ መልካም ነገር የመራ ሰው ከመራው ሰው እኩል ምንዳ አለው (ምንም ሳይቀንስበት)።“
[ሳሂህ ሙስሊም 18931]
@yasin_nuru @yasin_nuru