ጨረቃ
እንደ ልብ ወዳጅ ሌት ተቀን ተናፍቃ
እንደ እናት ጉርሻ በስስት ተጠብቃ
ምድሩን አፍክታ ሰማዩን አድምቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ!
ምንዳዬን አብዝቶ ኃጢያቴን አክስሞ
ከሲዖል ‘ሚያነፃኝ ሩሄን አለምልሞ
ከቤቱ መራቄ ሽሽቴ እንዲያበቃ
አቅፎ አድራሼን ይዛ ብቅ አለች ጨረቃ።
ሳይሰስት ‘ሚያድለኝ ከሰነቀው ፀጋ
‘ሚያቆመኝ ከደጁ እዝነቱን ፍለጋ
በስክነት ተውቦ ምህረትን ተኩሎ
እነሆ ብቅ አለ በጨረቃ ታዝሎ።
አህለን ያረመዳን
አህለን ቢከ ያረመዳን
አህለን ያረመዳን
አህለን ቢከ ረመዳን
**********
እንደ ልብ ወዳጅ ሌት ተቀን ተናፍቃ
እንደ እናት ጉርሻ በስስት ተጠብቃ
ምድሩን አፍክታ ሰማዩን አድምቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ!
ነፍሴ እንዳትሰንፍብኝ ለስጋዬ አድልቼ
ፅድቁን እንዳልረሳ ለእኩይ ተረትቼ
በክብር ‘ሚያስጠራኝ ተቅዋን አጎናፅፎ
የኃጢአቴን ሸክም ከላዬ አራግፎ።
እዝነትን የቸረኝ ከስስት አርቆ
የመስጠትን ዋጋ ያሳየኝ አልቆ
ብቅ አለ ረመዳን የበጎነት ማሳ
ሳይጎድል ትውስታው ጣዕሙ ሳይረሳ።
አህለን ያረመዳን
አህለን ቢከ ያረመዳን
አህለን ያረመዳን
አህለን ቢከ ረመዳን
********
እንደ ልብ ወዳጅ ሌት ተቀን ተናፍቃ
እንደ እናት ጉርሻ በስስት ተጠብቃ
ምድሩን አፍክታ ሰማዩን አድምቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ!
ተራዊህ ሙናጃው የሌሊት ሹክሹክታ
ሪዷውን ሽቶ የኸልዋ ቆይታ
አዝካር ሶለዋቱ የዱዓው ትውስታ
የወንድም ናፍቆት መሃባው ትዝታ።
ያንተ ትብስ አንተ ወጋችን ማሰሪያ
የመተጋገዣ ያብሮነት ማደሪያ
ተቅዋን ሊያላብስ የተኛን ሊያነቃ
የእዝነቱ ወር መጣ ብቅ አለች ጨረቃ።
በኢባዳ ወዝተው ደምቀው በአዝካሩ
ከቁርአን ሸንጎ ተርቲብ እየቀሩ
በመላእክት አክናፍ ዙሪያቸው ተከቦ
ሩሃቸው ይጠግባል ስጋቸው ተርቦ።
ኸይሩን ሚን አልፊዋን ማግኘት እየጓጉ
ሌሊቱን በስቲግፋር በዱዓ እያነጉ
የሊቃውን ፀጋ በረካውን ሽተው
ሲያነቡ ይፈጅራል የከርሞውን ናፍቀው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የካቲት 23/2012 ተፃፈ
********
#ረመዳን_18_ቀናቶች_ይቀሩታል 4/6/2017
@yasin_nuru @yasin_nuru
እንደ ልብ ወዳጅ ሌት ተቀን ተናፍቃ
እንደ እናት ጉርሻ በስስት ተጠብቃ
ምድሩን አፍክታ ሰማዩን አድምቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ!
ምንዳዬን አብዝቶ ኃጢያቴን አክስሞ
ከሲዖል ‘ሚያነፃኝ ሩሄን አለምልሞ
ከቤቱ መራቄ ሽሽቴ እንዲያበቃ
አቅፎ አድራሼን ይዛ ብቅ አለች ጨረቃ።
ሳይሰስት ‘ሚያድለኝ ከሰነቀው ፀጋ
‘ሚያቆመኝ ከደጁ እዝነቱን ፍለጋ
በስክነት ተውቦ ምህረትን ተኩሎ
እነሆ ብቅ አለ በጨረቃ ታዝሎ።
አህለን ያረመዳን
አህለን ቢከ ያረመዳን
አህለን ያረመዳን
አህለን ቢከ ረመዳን
**********
እንደ ልብ ወዳጅ ሌት ተቀን ተናፍቃ
እንደ እናት ጉርሻ በስስት ተጠብቃ
ምድሩን አፍክታ ሰማዩን አድምቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ!
ነፍሴ እንዳትሰንፍብኝ ለስጋዬ አድልቼ
ፅድቁን እንዳልረሳ ለእኩይ ተረትቼ
በክብር ‘ሚያስጠራኝ ተቅዋን አጎናፅፎ
የኃጢአቴን ሸክም ከላዬ አራግፎ።
እዝነትን የቸረኝ ከስስት አርቆ
የመስጠትን ዋጋ ያሳየኝ አልቆ
ብቅ አለ ረመዳን የበጎነት ማሳ
ሳይጎድል ትውስታው ጣዕሙ ሳይረሳ።
አህለን ያረመዳን
አህለን ቢከ ያረመዳን
አህለን ያረመዳን
አህለን ቢከ ረመዳን
********
እንደ ልብ ወዳጅ ሌት ተቀን ተናፍቃ
እንደ እናት ጉርሻ በስስት ተጠብቃ
ምድሩን አፍክታ ሰማዩን አድምቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ!
ተራዊህ ሙናጃው የሌሊት ሹክሹክታ
ሪዷውን ሽቶ የኸልዋ ቆይታ
አዝካር ሶለዋቱ የዱዓው ትውስታ
የወንድም ናፍቆት መሃባው ትዝታ።
ያንተ ትብስ አንተ ወጋችን ማሰሪያ
የመተጋገዣ ያብሮነት ማደሪያ
ተቅዋን ሊያላብስ የተኛን ሊያነቃ
የእዝነቱ ወር መጣ ብቅ አለች ጨረቃ።
በኢባዳ ወዝተው ደምቀው በአዝካሩ
ከቁርአን ሸንጎ ተርቲብ እየቀሩ
በመላእክት አክናፍ ዙሪያቸው ተከቦ
ሩሃቸው ይጠግባል ስጋቸው ተርቦ።
ኸይሩን ሚን አልፊዋን ማግኘት እየጓጉ
ሌሊቱን በስቲግፋር በዱዓ እያነጉ
የሊቃውን ፀጋ በረካውን ሽተው
ሲያነቡ ይፈጅራል የከርሞውን ናፍቀው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የካቲት 23/2012 ተፃፈ
********
#ረመዳን_18_ቀናቶች_ይቀሩታል 4/6/2017
@yasin_nuru @yasin_nuru