የአክሱም እህቶቻችን እንኳን ሊፈቀድላቸው ጭራሽ እስርና ዛቻ እየደረሰባቸው ነው‼
===============================
(የግፍ ግፍ! መብታቸው ተነጥቆ፣ ጭራሽ ዛቻና ማስፈራሪያ፣ እስርና ማስጠንቀቂያ እየተፈለመባቸው ነው!)
||
✍ «በአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ የተለያዩ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን ገለፁ!
በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን የአክሱም ከተማ በሂጃባቸው ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎች እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ ምንም አይነት መፍትሔ አለማግኘታቸውን ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በተማሪዎች እና ወላጆቻቸው ላይ በፀጥታ ሀይሎች እና በትምህርት ቤቶቹ ዳይሬክተሮች የተለያዩ ማስፈራሪያ እና ዛቻ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ የገለፁ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የታሰሩ ተማሪዎችም እንደነበሩ ተገልጿል።
ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች አንድ ተማሪ ለሀሩን ሚዲያ እንደገለፀችው "እኛ የቻልነው ታግለናል ነገር ግን ምንም ለውጥ ልናመጣ አልቻልንም" ብላለች።
ሂጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት የሄዱ ተማሪዎች ላይ የተለያዩ ድብደባ እና ማዋከብ እንደተፈፀመባቸው ተማሪዎቹ ገልፀዋል።
ሌላኛዋ ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች የከተማዋ ተማሪ "ለምን ሂጃብ ለብሰን እንማር አላችሁ?" በሚል ለ17 ሰኣት ታስረው እንደነበር ገልፃ ከዚህ በኋላ መሰል ጥያቄ እንዳያነሱ ማስፈራሪያ እና ዛቻ እንደተፈፀመባቸው ገልፃለች።
የጠየቅነው በሀገሪቱ ህገመንግስት የተፈቀደ ሀይማኖታዊ ግዴታችን የሆነውን ሂጃብ ለብሰን ትምህርታችንን እንማር ቢሆንም ምላሽ ግን እስከ ቤተሰቦቻችን ማስፈራሪያ ዛቻ ማዋከብ እና ድብደባ ነው ሲሉ ተማሪዎቹ ገልፀዋል።
የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ በበላ ሀገሪቱ ከ499 ሺህ በላይ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል ያለ ቢሆንም በአክሱም ከተማ ግን አንድም ሙስሊም ሴት ተማሪ ምዝገባ አለማድረጉን ተማሪዎች ገልጸዋል።»
©: ሀሩን ሚዲያ