ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_21
...ከፊት ለፊቴ ድንቅር ብላ ቆማለች አፌን በእጆቼ አንስቼ አይኔ እስከተከፈተልኝ ድረስ አፈጠጥኩኝ እሷ ግን ምንም አይነት ነገር ሳታወራ ረጋ ብላ በአትኩሮት ተመለከተችኝ ቁመቷ አጠር ያለ ነበር ከመደንገጤ የተነሳ ቃሎቼ መክነው አንደበቴም ተሳስሮ ነበር ትንሽ ወደ ቀልቤ ስመለስ አይኔን ወደታች ልኬ በእጇ አንዳች ነገር ከያዘች ብዬ ተመለከትኩኝ ነገር ግን ምንም አልያዘችም ነበር በትንሹም ቢሆን ራሴን ማረጋጋት ችያለሁ ቀስ እያለች ወደኔ መጠጋት ጀመረች ቤቱ ያለው አንድ መውጫ እሱንም ደግሞ እሷ ዘግታዋለች ወደሗላ እንዳልሸሽ ጭራሽ ወደ ገዳዩ ነው ምገባው በዚ ግዜ አንዳች ነገር መወሰን እንዳለብኝ ተረዳሁ...እኔም ቀስ እያልኩ እጆቼን ጨብጬ ውስጤን አጠንክሬ ወደሷ መጠጋት ጀመርኩ መሞት እንደው የማይቀር ነው ቀኔ ከሆነ ልሙት ብዬ ራሴን አጀገንኩኝ በጣም ተቀራረብን ሳይቀደሙ መቅደም ነው ራሴን አዘጋጅቻለሁ "እሷ ቀድማ ከመታችኝ ነፍሴን እዚሁ ነው ምነጠቀው ስለዚህ መወሰን አለብኝ" ብዬ ለራሴ ነገርኩት በመሃላችን የአንድ እርምጃ ልዩነት እንደቀረን አሽቀንጥሬ ገፈተርኳት አጠገባችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ሄዳ ተዘረጋች እላዩ ላይ ያለውንም ዕቃ ናደችው ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ የሁካታ ድምፅ ተሰማ ወዲያውኑ ከዛ ቤት በፍጥነት ወጣሁ ገፍትሬ የጣልኳት ሴትዮ "አንድዬ" ብላ ስትጣራ ሰማሁት አሁንም ከዛ ቦታ ለመውጣት የጀመርኩትን ሩጫ አላቆምኩም ዞር ብዬ ስመለከት ሰውዬው በሩ ላይ ቆሞ እየተመለከተኝ ነው ልክ ደረጃው ጋ ስደርስ በእጁ የያዘውን ወደኔ ወረወረው አንድ ደረጃ ከፍ ብል ኖሮ መጥረቢያው የሗላ ጭንቅላቴ ላይ ይሰነቀር ነበር...ነገር ግን ደረጃውን አልወጣሁትም ነበር "ትረፊ ያላት ነፍስ" አልኩኝ ለራሴ መጥረቢያው እንዳልመታኝ ሲመለከት ሴትየዋን ስጥላት ከወደቀው ዕቃ መሃል ብራማ አብረቅራቂ ቢላዋ ይዞ ወደኔ መገስገስ ጀመረ እኔም ለማምለጥ መሮጤን ቀጠልኩ ደረጃው እንደጨረስኩ ወደ ደረጃው የሚያስገባውን በር ዘጋሁት ነገር ግን ሰውዬው ለመክፈት ቅንጣት አላዳገተውም ነበር መጥረቢያውንም ቢላውንም ይዞ እየተከተለኝ ነው በጣም ፈጣን ነው ሲሮጥ አሁን ኮሪደሩ ላይ ወጥቻለው ከሆስፒታሉ ወጥቼ ወደ ውጪ ልሩጥ ወይስ ወዴት ልደበቅ አልኩና ትንሽ አመነታሁ ከዛም ሌሎቹን የታካሚ መኝታ ክፍሎችን ነበር ዝም ብዬ ከፈትኳቸው ከዛም እኔ ሆስፒታሉ አጠገብ ወዳለው ጫካ ውስጥ ተደበኩኝ የነበርኩበት ቦታ የሆስፒታሉን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ነገር ግን ሰውዬውን አላየሁትም ነበር በጣም ተደናገጥኩኝ ይህ አወዛጋቢ ሰውዬ ወዴት እንደተሰወረ አስደነገጠኝ ዙሪያ ገባዬን ቃኘሁኝ ሰውዬው አሁንም የለም ነገር ግን ከሆስፒታሉ ውስጥ የጫጫታ እና የዋይታ ድምፅ ተሰማኝ ይህ ሰው ጓደኞቼን አንዳች ነገር እንዳደረጋቸው ጠረጠርኩ ከዛም ካለሁበት ቦታ ስምዘገዘግ ወደ ውስጥ ገባሁ ሁሉንም ክፍሎች ተመለከትኩኝ ማንም አልነበረም ጓደኞቼን ትቼ ከሄድኩበት ስፍራ አጣሗቸው ተንበርክኬም አፌን ከፍቼ ጮውኩኝ የቀረሁት እኔ ብቻ ኀኝ "ወንድ ከሆንክ ና ውጣ እንደ ድመት ተደብቀህ አታድን" ብዬ ጮውኩኝ ደጋግሜም አልኩት ያገኘሁትን ዕቃ ሁሉ ገለባበጥኩኝ ነገር ግን እሱ ዝርም አላለም ነበር ግድግዳውን ታክኬ ስቅስቅ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩኝ ከዛም ወዲያውኑ ማልቀሴን አቆምኩኝ ከተቀመጥኩበትም ተነሳሁ ቀጥ ብዬ መኪናችን ወደቆመበት ስፍራ አመራሁ ሻንጣዬን አውርጄ የእጅ ባትሪ አውጣሁ የለበስኩትን ቱታ በጅንስ ቀየርኩት ከስክስ ጫማዬንም አደረኩኝ ወፈር ያለ ጃኬት ደረብኩኝ ለምግብ ማብሰያ ከያዝናቸው ዕቃዎች ውስጤ ቢላ አነሳሁ ከዛም ቀጥ ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁ ለመወሰን ወስኛለሁ "ጓደኞቼን አስበልቼ እኔ ቆሜ አልሄድም ወይ እሱ ቆሞ አይሄድም" ብዬ ራሴን የንዴቴ ጥግ ላይ አድርሼ የሚያሳድደኝን ማሳደድ ጀመርኩ የሚፈልገኝን መፈለግ ጀመርኩ የሚያስፈራራኝን ደፈርኩት የሚያስጨንቀኝ ተዳፈርኩት በአንድ ነፍሴ አንድ ጊዜ ማልኩኝ ፍራቻ ከውስጤ ተመንቅሮ ወጣ ደም እንደጠማው መንፈስ ያን ክፉ ሰው እስካገኘው ጊዜው ረዘመብኝ ሴት ነች ወንድን የምትወልደው ሴት ነች የወንድ ልክ ሴትነት ምን እንደሆነ አሳየዋለሁ....የሆስፒታሉ መብራት አሁንም መጣ ቀረት እያለ ነው ነገር ግን ለኔ ምንም ነበር ቀድሞ ጨለማው ያስፈራኝ ነበር አሁን ግን እሱ ከፈራ ይፍራኝ...ጉዞዬን ቀጥያለሁ ሁሉም ክፍሎች እየገባሁ ተመለከትኩኝ ማንም አልነበረም ከጓደኞቼ ጋ የነበርኩበት ክፍልም ገባሁ አሁንም ማንም የለም ነገር ግን አንድ ነገር ቀልቤን ያዘው "ያ ሰው ጓደኞቼ ላይ ጥቃት ካደረሰ እንዴት ደም አልፈሰሰም" ብዬ ራሴን ጠየኩኝ "አምልጠው ቢሆንስ" እያልኩም ከራሴ ጋ ማውራት ጀመርኩኝ ደግሞም ቢያመልጡ እንደዛ አይነት የዋይታ ድምፅ ለምን...ከዛም ከክፍሉ ወጣሁ ወደገባሁበትም ስፍራ ተመለከትኩ ምንም የለም ነገር ግን በተቃራኒው ጥግ ላይ........
Part "22".............ይቀጥላል
ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱