🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ ሀና ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 1️⃣
በጠዋት ከእንቅልፌ ተነሳሁ።
ወደባለቤቴ ፊቴን ሳላዞር ከአልጋ ወርጄ ከክፍሉ ወጣሁ።
እንደተለመደው ታጥቤ ልብሴን ለባብሼ ወደስራ ቦታዬ አመራሁ። ሀና በጠዋት ሱቃችንን ከፍታ የተስተካከለውን እቃ ደግማ እያስተካከለች ጠበቀችኝ ሰላምታ ተቀያይረን ወደ ሱቁ ገብቼ አረፍ አልኩ ዛሬ ቁርስ ምን ልዘዝልህ ምንድነው ምትበላው አለችኝ፡፡ የተለመደውን እዘዢልኝ ዛሬ ደሞ ገና ሳይነጋ ነው የራበኝ አልኳት፡፡
ከኛ ሱቅ ቀጥሎ ወዳለው ምግብ ቤት አመራችና ምግቡን አዛልኝ መጣች፡፡
ሲደርስ እራሳቸው ሱቅ ይዘውልኝ መጡና ቁርሴን ጥርግ አድርጌ በልቼ በጥሩ ሞራል ጥሩ ቀናችንን ጀመርን። ቤቱ ከስተመር በጣም አለው፡፡
እኔን የሚያስገርመኝ ግን የከስተመሩ መብዛት ሳይሆን የሀኒ ቅልጥፍና ነው።
አንዱን ከስተመር መቼ ሸኝታ ሌላኛውን ከመቼው አስተናግዳ እንደምትጨርስ ሳይ ይቺ ልጅ ግን ውስጧ ሌላ አንድ ሰው አለ እንዴ እላለሁ።
የዛን ምሽት ተመሳሳይ ውሎ አሳለፍንና እሷን ወደቤት ሸኝቼ እኔ ወደመጠጥ ቤት ሄድኩኝ አንድ ቢራ አዝዤ ቢያንስ ለአንድ ሰአት ያህል ብቻዬን ቁጭ አልኩኝ። ከመጀመሪያውም መጠጥ ቤት ምሄደው የመጠጣት ሱስ
ኖሮብኝ ሳይሆን ሰአቴን ለመግደል ያህል ነው።
ወደቤቴ ቶሎ እንዳልገባ ወድጃት አፍቅሪያት ያገባኋትን ሚስቴን ላለማየት ነው።
በስራ ስደክም ውዬ ማታ ልክ 2.3ዐ ሲሆን ሱቅ ልንዘጋ ስንል እኔ ቀድሞ ጭንቅ ይለኛል ወደቤት ስለመሄድ ሳስብ
ያንገሸግሸኛል ። ያዘዝኳትን ቢራ ጠጣሁና 3.30 ሲሆን ወደቤቴ ሄድኩኝ ።
ባለቤቴ (ያው ለኔ ግን እስር ቤቴ) ብላት ይሻለኛል ሶፋ ላይ ጋለል ብላ ፎጣዋን ተከናንባ ለብሳ ፊልሟን ትኮመኩማለች ቤቱን ሲኒማ ቤት ለማስመሰል አስባ መሰለኝ መብራቱንም አጥፍታዋለች፡
ልክ እኔ ስገባ ጠላት ከውጪ የመጣባት ይመስል ምንቅር ምንቅር እያለች ባጠገቤ አልፋኝ ወደመኝታ ቤት
ገባች፡፡ ምናልባት እራት ከሰራች ለማየት ወደ ኪችን ጎራ አልኩኝ ሰርታ የበላችበትይ ብረድስት እንኳን አላጠበችው እቃው ሲንኩ ላይ ተከምሯል ፍሪጅ ከፈትኩኝ ሚላስ ሚቀመስ የለም ሁሉንም እቃ አንድ ባንድ እየከፈትኩ አየሁ የለም፡፡ ውስጤ ቅጥል እያለ እንቁላል ለመስራት ተሰነዳዳሁ ወደመኝታ ቤት ገብቼ ልብስ ለመቀየር ሁላ እሷ እዛ እንዳለች ሳስብ ዘገነነኝ፡፡እንቁላሌ እስኪደርስ የከመረችውን እቃ ማጣጠብ ጀመርኩ።
ገረመኝ መቼ መቼ ነው ይሄን ሁሉ ምግብ ሰርታ
ምትበላው ሁሉም እቃ የተለያየ ምግብ እንደተሰራበትና እንደተበላበት ያስታውቃል ታዲያ እኔ ያባቷ ገዳይ አደለሁ እንደዚህ ምግብ መስራት ከቻለች ለኔ ብታስቀምጥልኝ ምናለበት ደክሞኝ ነው ምመጣው አደል ቀኑን ሙሉ ቤት ውላ ማታ ገብቼ ምግብ ሰርቼ ለመብላት የሚያደርሰኝን ግፍ ሰርቻለሁ እንዴ ለነገሩ እንደንፁህ ሰው መመፃደቅ አያስፈልግም ይበለኝ ስራዬ ነው ።
እቃዬን አጣጥቤ ስጨርስ እንቁላሌን አቀረብኩና ጥርግ አድርጌ በላሁ ወደሲኦል ለመሄድ ዝግጅቱን እንደጨረሰ ሰው እየሆንኩ ወደመኝታ ቤቴ አመራሁ ሳሎን ያቆመችውን ፊልም መኝታ ቤት ገብታ ቀጥላዋለች በድጋሜ እኔ ወደመኝታ ቤት ስገባ ፊልሙን ዝግትግት አድርጋ ጥቅልል ብላ ፊቷን አዙራ ተኛች ። ስለደከመኝ እኔም የራሴን ብርድልብስ ለብሼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ።
በነጋታው ስነሳ ከጎኔ የለችም ተጣጥቤ ልብሴን ቀያይሬ ወደሳሎን ስሄድ ጠረጴዛውን በምግብ አሰማምራ ጠበቀችኝ የመጣ ሰው ካለ ቤቱን ቃኘት ቃኘት አደረኩ ማንም የለም ወዲያው ከኩሽና ወጥታ መጣችና እቅፍ አድርጋ ሳመችኝ በል ቁርስ ደርሷል ብላ ግራ ገባኝ ትናት ማታ አይንህ ላፈር ያለችኝ ሚስቴ አዳሯን የትኛው መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ሰላም ሰቷት ነው እንደዚህ ተቀይራ የተነሳችው ግራ ቢገባኝም ወደጠረጴዛዬ ሄጄ ቁጭ አልኩኝና ቁርሴን በላሁ ከመቼውተነስታ ይሄንን ሁሉ ምግብ እንዳዘጋጀችው ገረመኝ ።
ከቤት ወጥቼ እስኪሄድ ድረስ በአይኗ ሸኝታኝ ተመለሰችትንሽ እንደነዳሁ ደወለችና ድንገት ወደቤት ከመጣሁ ቀድመህ ደውልልኝ አለችኝ እሺ አልኳት።ሱቅ ስደርስ ሀና ከፋፍታ ውስጡን እያስተካከለች ነበር።
እንደወትሮው ዘርፋፋ ቀሚሷን ለበስ አድርጋ ዝንጥ ብላለች።ሰላምታ አቅርቤላቸው ወደውስጥ ገባሁ በሚስቴ ድርጊት ብቻዬን ፈገግ እያልኩ ድጋሜ ስልኬ ጠራ ሚስቴ ነበረች አነሳሁት
እኔ ምልህ ለምሳ ቤት ትመጣለህ እንዴ??
አይ አልመጣም ምነው ልምጣ እንዴ?
አይ እንደሱ ለማለት ሳይሆን ድንገት ከመጣህ ብዬ ነው እዛው ብላ ነዳጅ ምን አስጨረሰህ ሰላም ዋል በቃ !! ስልኩ ተዘጋ፡፡ ማታ ጠዋት በሰላም ትቻት የወጣሁት ሚስቴን ደሞ አምሽቼ እንዳላንድዳት ብዬ በጊዜ ወደቤቴ አመራሁ ::
በር ላይ ቆሜ እረጅም ሰአት ክላክስ ባደርግ ሚከፍትልኝ አጣሁ እራሴ ወርጄ ከፍቼ ወደውስጥ ስገባ ሚስቴ ሴጣኖቿ በሙሉ ተነስተውባት ገና ከውጭ በነገር ጀመረችኝ አንዴ ክላክስ አድርገህ ካልከፈትኩልህ ይሄን ያህል ሰአት ምንድነው ምታጮህብኝ አለችኝ
ይቀጥላል...
🔻ክፍል2️⃣ከ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔