💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
የታሪኩ ርዕስ
💁♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
#ክፍል ☞ ሁለት 2⃣
✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን
አንደኛ ክፍልን ካራማራ የተባለች እዛው ሰፈራችን ልደታ አካባቢ ያለች ትምህርት ቤት ገባሁ።
ከማይረሱ የትምህርት ቤት ትዝታዎቼ መካከል ዋነኛው ነው። የፍቅርን ትርጉም ሰው ማለት ምን እንደሆነ የተማርኩት እዛ ነው። ደሀ ሆነን እንደ ድህነታችን ሳይቸግረን ልብሳችን ቆሽሾ እንደቆሸሸ ሳይሰማን እከሌ ከኔ ይበልጣል እከሌ ከኔ ያንሳል ሳንል እንደ አህያ መሬት ላይ እየተንከባለልን እንደ ዶሮ መሬት እየጫርን አፈር እያቦካን ጭቃ እየጋገርን ውሀን ሻይ እያልን ቆሻሻ እየበላን አፈር እየላስን አልፈናል።
1 ብር ለወር ወጪያችን እየተጠቀምን በአምስት ሳንቲም እንደልብ አውላን 10 ሳንቲም እስከ ጓደኞቻችን ፈታ ታደርገናለች። በ አምስት ሳንቲም በረዶ(ጀላቲ) ገዝተናል ፤ በአምስት ሳንቲም አንድ እፍኝ ጋባ ገዝተን ተመግበናል፤ በአምስት ሳንቲም አንድ ፍሬ አካት ገዝተን ስንግጥ ውለናል፤በአምስት ሳንቲም 2 ናና ከረሜላ ገዝተን ከ ጓደኛችን ጋር ተካፍለን በልተናል። ሳንቲምም ከሌለን ሻጮቹን በአሳዛኝ የልጅነት ፊታችን እባክህ አንድ ፍሬ ስጠኝ እያልን እየለመንን ተመግበናል። በየመንደሩም ዞረን ካዝሚር እና አቦካዶ ያለበት ቤት አንኳክተን ለምነል በልተናል። ኩረጃ ምን እንደሆነ ሳናውቅ ትምርትን አጣጥመን በራሳችን ሰርተን አልፈናል።
እርስ በርሳችንም ፍቅር አለን ለብቻ መብላት እና መጠጣት አናውቅም ።አስተማሪዎቹም ፉንጋ እንሁን መልከ መልካም ሳያማርጡ ግንባር ግንባራችንን ጉንጭ ጉንጫችንን ይስሙናል። ሁሉም አስተማሪ ልጆቼ እንጂ ተማሪዎቼ አይሉንም ።እንዲህ እንዲህ እያልን አመቱ አለቀና ከ 50 ተማሪ አስራ አንደኛ በ 70 ነጥብ አምጥቼ ወደ ሁለተኛ ክፍል ተዘዋወርኩ።
ሁለተኛ ክፍል የገባሁት የግል ትምህርት ቤት ነው።አባቴ ለትምህርት ያለው ፍቅር እጅግ በጣም ልዩ ነው። እሱ እናት እና አባቱ ስላላስተማሩት እኛን እንደሱ እንዳንሆን ይጥራል ለትምህርትም ያለውን ሁሉ ያወጣል።ለዛም ነው ያለ አቅሙ የባለስልጣን ልጆች የሚማሩበትን የሀብታም ልጆች የሚቀማጠሉበትን ትምህርት ቤት ከለት ጉርስ ወጪው ቀንሶ ያስተማረኝ።ሰፈርም ቀይረናል ወደ ተወዳጁ ሰፈር አብነት ገብተናል። መቼስ የዱንያ ነገር የኪራይ ቤት ኑሮ ነውና በቤት ኪራይ ምክንያት
እንከራተታለን።የተወለድኩት ኮልፌ ያደኩት ልደታ አሁን ያለሁት አብነት የነገውን ደሞ አላህ ያውቃል።
አዲሱ ትምህርት ቤቴ ያሉት ተማሪዎች አለባበሳቸው እና ፀባያቸው እንዲሁም ንግግራቸው ሁሉ ነገራቸው ይለያል። የቄስ ትምህርት ቤት ተምሮ ያደገን ልጅ ወደግል ትምህርት ቤት ማምራት ይከብዳል ብቻ የአላህ ውሳኔ ሆኖ ገብቻለው።
ከሀብታም ልጆች ጋር ለመልመድ እጅግ በጣም ብቸገርም ጋደኞች ለማፍራት ብቸገርም ቀስ በቀስ እየለመድኩት መጥቻለው።የምማረው የፕሮቴስታንት ትምህርት ቤት እንደመሆኑ መጠን ሙስሊም ተማሪ እኔ ብቻ ነኝ ።ለዚህም ነበር ጓደኛ ለማፍራት ብዙ የተቸገርኩት።እያደር እያደር ከክፍላችን ተማሪዎች መካከል አንድዋ የሆነችው እየሩስን ተዋወኩ።
እዩ በጣም ልዩ የሆነች ልጅ ናት ከነ ማንነቴ ተቀብላኛለች። ሌሎች ተማሪዎች በሙስሊምነቴ ብዙም ባይቀርቡኝም እዩ ግን ልትርቀኝ አልቻለችም። አንድ ሁለት እያልን አመታት አለፈ 5ተኛ ክፍል ደረስኩ። ሁሉም የክፍላችን ልጆች እንደ ብርቅዬ ነው የሚያዩኝ። ዘቢ እንጂ ዘቢባ ብሎ ሚጠራኝ የለም።ወንድ ሴት ብሎ ልዩነት የለም ወንዱ ከሴት ጋር ተቃቅፎ ይጫወታል ግን ፆታዊ ልዩነት የለም ፍቅርም የለም።ቢሆንም ልዩነታችን የሰፋ ነው።
እኔ እዛ ትምህርት ቤት ከገባሁ ጀምሮ ዩኒፎርም የተገዛልኝ አንድ ጊዜ ነው እነሱ ሰኞ ማክሰኞ እና እሮብ ሀሙስ እና ጁመአ የሚለብሱት ዩኒፎርም የተለያየ ነው። እኔ ጫማ የማደርገው ከአመት አመት አንድ ሸራ እያጠብኩ ነው።ጫማውም እየጠበበኝ በመምጣቱ ምክንያት የእግሬ ጥፍሮች እና ጣቶች ታጥፈው አጎርብበዋል።እናቱ ቀርታበት ተደፍቶ እንደሚያለቅስ ህፃን እጥፍጥፍ ብለዋል። ጫማው እራሱ እንዲ እየዘለልኩበት እየተራገጥኩበት ሲያሻኝ ሱዚ ሲያሻኝ ደሞ እግር ኳስ ከወንዶች ጋር እየተራገጥኩበት አለመቀደዱ ይገርመኛል። አንዳንዴም ምነው በተቀደደ እና በስበቡ አዲስ በተገዛልኝ ብዬ ዱአ አደርጋለው።
ኑሮ ከባድ ነው አባቴን ግዛልኝ ከነሱ እኩል አድርገኝ ማለት አልችልም ብልም አይደረግልኝም።
በእርግጥ አሁን ላይ ጥሩ ስራ አለው ቸግሮት አያውቅም።እኔን የሚቸግረኝ የሱ ድጋፍ በማጣቴ እንጂ በእርሱ ብር ማጣት ምክንያት አይደለም።አባቴ እንድማር እንጂ የነሱ አለባበስ እና ኑሮ እንድለምድ አይፈልግም እኔ ግን ሰፊውን ጊዜዬ ማሳልፈው ከነሱጋር ስለሆነ ሳልፈልግ ለምጄዋለው። ጫማቸው እና የፀጉር ጌጣቸው ያምረኛል ይማርከኛል ያስቀናኛል። እንዲህ እንዲህ እያለ የአምስተኛ ክፍል የመጀመርያ መንፈቅ አመት ማጠቃለያ ፈተና ምንፈተንበት ጊዜ ደረሰ።
የመጀመርያው ቀን እለተ ሰኞ አማርኛ እና እንግሊዝኛ ተፈትነን አለፍን ሁለተኛው ቀን እለተ እሮብ ሂሳብ እና ስነዜጋ እየተፈተንን እንዳለ ፈተናዬን ሰጥቼ ልወጣ ስል አንዳች ነገር ተከሰተ። ምድር ተከፍላ ብትዉጠኝ ደስታዬ ነበር። ምነው ይሄ ቀን ባልተፈጠረ ወይም ጥዋት ሳልነሳ በዛው ሞቼ በነበረ ብዬ ተመኘሁ ..
Part 3⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል ከ60👍 በኋላ ይለቀቃል ቶሎ ቶሎ ተጫኑት እንዲለቀቅ አንብባቹ ከጨረሳቹ በኋላ👍