〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰
የታሪኩ ርዕስ
#SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
#ክፍል ☞ አራት 4
ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን
ከትምህርት ቤት እና ከመድረሳ ስወጣ እየጠበቀ ሰላምታ መስጠት ጀምሯል ለዛም ነው መሰለኝ አይኔ ያረፈበት።
እየሩስም መውጫ እና መግቢያችን ላይ ስንፋጠጥ እያሾፈችብኝ ማላገጥ ጀምራለች።እዩ ንግግርዋ ይማርከኛል እንኳን ወንድን ሴትን ያሳስታል።በተለይ ሙድ ስትይዝ እ አይደለም እንዴ ¡አሀ ነው¡ ተይ ባክሽ¡ ኡኡቴ እያለች ግንባርዋን ሸብሽባ ቅንድብዋን ላይ ታች ምታጫውተው ነገር ይበልጥ እወድላታለው።
በዚህ አመት ሁለት አዳዲስ ነገር ተፈጥሯል እዩ ሀይድ ማየት ጀምራለች ሌላው ደግሞ ኩረጃን ተምረናል። እንዳውም ኩረጃን እየተማመንን ማጥናቱን ዘንግተነዋል። የ እዩ ሀይድ መምጫ ሰአት ሲደርስ የምትሆነው ነገር በጣም ያስቀኛል። ሞዴሱን ከፓንትዋ ጋር አገናኝታ ከለበሰች በኋላ ሞዴሱ ሾልኮ ሚወድቅባት እየመሰላት ከፓንቱ ላይ ሌላ ሁለተኛ ፓንት ትደርብበታለች በመቀጠልም ታይት ታጠልቃለች።በ ታይቱ ላይ ሌላ ቁምጣ ትደርብበታለች።ይሄ ነገርዋ በጣም ያስቀኛል።
ሰው ሁሉ ሀይድ ላይ መሆንዋን የሚያውቅባት ይመስላታል። የደራረበችው ፓንት እና ታይት ሰውነት(ዳሌ ) ይሰጣታል ይሄ ነገር ደሞ ይበልጥ ያስቀኛል። ሀይድዋ ሲመጣ የምትለብሰው ዩኒፎርም እራሱ ይለያል። የሌላ ጊዜው ዩኒፎርም ጉርድዋ ከጉልበትዋ ልክ የሆነ ሽንሽን አጭር ቀሚስ ነው ሀይድ ላይ ስትሆን ግን እስከ ቁርጭምጭሚትዋ ድረስ የሚደርስ ሽንሽን ጉርድ ነው ምትለብሰው።በዚህ ሁኔታዋ ስለምስቅባት የኔ ሳቅ ይበልጥ ያበሽቃታል።
በዚህ አመት የትምህርት ውጤቴ እያሽቆለቆለ ስለመጣ አባቴ ከትምህርት ሰአት ውጪ የጥናት (ማጠናከሪዬ) ትምህርት እንድማር አመቻቸ። አዲስ አበባ ላይ ብዙዎቹ ትምህርት ቤት የትምህርት ሰአት ለቅድመ መደበኛ(ለ kg ) ትምህርት
ከ 2፡30 እስከ 9፡00 ሰአት ሲሆን.. የመጀመርያ ደረጃ (primery school) ከ 2፡30 እስከ 9፡30 ነው።
የ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት(secondery and priparatory school) ከ 2፡00 እስከ 9፡00 ሰአት ነው።
ስለሆነም የማጠናከርያ ትምህርቴን የምማረው ከ መደበኛው ሰአት በኋላ ማለትም ከ 9፡30 በኋላ ከ 10፡00 ሰአት እስከ 11፡00 ሰአት ነው። ይሁን እንጂ ማጠናከሪያ ትምህርቱ ለኔ ለውጥ የለውም ምክንያቱም አባቴ ብሩን በየወሩ ይክፈል እንጂ እኔና እየሩስ ሰአቱን የምናሳልፈው እንደለመድነው ለወንዶቹ ደብዳቤ እየፃፍን ቀጣይ የምናጠምደውን ወንድ እያቀድን እንዲሁም የማጠናከሪያ ሰአታችንን አከባቢያችንን እየዞርን እየተሽከረከርን ነው ምናሳልፈው።
ልክ 9፡30 እንደተለቀቅን ማጠናከሪያውን ሳንገባ ከትምህርት ቤት ወጥተን አዲስ ወደተገነባው እና በውበቱ ስለሚወራለት ልደታ ኮንዶሚኒየም ሄደን ሰአታችን እስኪደርስ በመናፈሻው ተናፍሰን በዛውም በመውጫችን ከድርን አይተን እንሄዳለን። ለከድር ያለኝ ስሜት ከእለት ወደየለት እየጨመረ መጥቷል። ይናፍቀኛል። አቋሙ ተክለ ሰውነቱ አይኑ የፀጉሩ እስታይል ድምፁ ባጠቃላይ ሁሉ ነገሩ ይማርከኛል። ካላየሁት ይጨንቀኛል።
እሱም ይሄንን ተረድቶ ነው መሰለኝ ከትምህርት ቤት ስወጣ አልያም ከመድረሳ ስወጣ ከቤታቸው ፊት ለፊት አስባልቱ ዳር ድቅን ብሎ ቁሟል፡ የቆመው በ ገመድ የተተበተበው ፖል ተደግፎ አይኑን አንዴ ወደላይ አንዴ ወደታች አንዴም ደሞ ወደጎን እያየ ይጠብቀኛል። ንግግሩ ቀልቤን ገዝቶታል።ባጭሩ ምን አለፋችሁ በሙሉ አፌ እመሰክራለሁ አፍቅሬዋለሁ ።አይኑን ሳላይ ማደር እያቃተኝ መጥቷል። እሱን ለማየት ስል የመድረሳ ትምህርቴን ማቀላጠፍ ጀምሬያለሁ። በስህተት እንኳን ታምሜም ቢሆን ከመሄድ አልቆጠብም። ሀይድ ላይም ብሆን ቁርአን ባልቀራም መድረሳ ሄጄ እቀመጣለው።
የአመቱ ማጠቃለያ ፈተና ወሰድን። ሰኔ ሰላሳም ደረሰ። ሰኔ ሰላሳ ካርድ የምንቀበልበት ነዉ የስድስተኛ ክፍል ውጤቴ አመርቂ አልነበረም ከነበረው ቀንሷል። ከ 45 ተማሪ በ 80 ነጥብ 15ተኛን ደረጃ ይዤ አጠናቅቄያለሁ። በዚህም ዉጤቴ አባቴ ደስተኛ አልነበረም።
በዚህም የተነሳ ሰፈሩ አስተዋፅኦ አድርጎባት ነው ጥሩ ነገር እየተማረች አይደለም በማለት ሰፈር እንድንቀይር አደረገ። በዚህም ምክንያት ሰባተኛ ወደተባለው መርካቶ አቅራቢያ ወዳለው ሰፈር ቤት ተከራየን።
ክፍል አምስት ከ60👍 በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍 ማድረግ አይርሱ
የፍቅር ቴሌግራም ቻናል
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!