💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
የታሪኩ ርዕስ
💁♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
#ክፍል ☞ አስራ ሶስት 1⃣3⃣
✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን
በISALMIC SCHOOL ቻናል የተዘጋጀ
ቀስ በቀስ ሁላችንም የየራሳችንን ጓደኞች አፈራን
ኬቢ(ኬብሮን) ራሄል የተባለች ጓደኛ ስታፈራ እኔ ደሞ ዘቢባ፣እየሩስ፣ትግስት፣ሰአዳ እና አሚራ የተባሉ ጓደኞችን አፍርቻለው። በባህሪዬ ሰው ለመግባባት ጊዜ ስለማይፈጅብኝ እነሱን ለመተዋወቅ አልተቸገርኩም።
...ሙስሊም ጓደኛ ኑሮኝ ስለማያውቅ አሚራን ሰአዳን እና ዘቢባን ከሌሎቹ በተለየ በጣም ነበር የምወዳቸው። በተለይ ደሞ ለዘቢባ ያለኝ ፍቅር ልዩ ነበር። ብዙ ነገሬን ቀይራዋለች አለባበሴን ስርአቴን እናም ሌሎች ባህሪዎቼን አስተካክላዋለች።
ቂርአቴ ላይ ጊዜ እንድወስድ ሶላት በሰአቱ እንድሰግድ ብዙ ነገር አስተምራኛለች።እኔ ዘቦ እና ሰአዳ ምሳ ይዘን ስለምንሄድ ምሳ ሰአታችንን ትምህርት ቤት ነው የምናሳልፈው አሚራ ምሳ ስለማትይዝ ወደ ቤትዋ እየሄደች ትመገባለች።እኔ ሰአዳና ዘቦ ምግቦቻችንን በየተራ ከተመገብን በኋላ ሶላት ለመስገድ ወደ ግቢያችን ጀመአ ቤት እናመራለን።
ትምህርት ቤታችን የሙስሊም ተማሪዎች ጀመአ እንዳለው የሰማሁት ከዘቦ ነው። ከዛን በፊት ጀመአ ምን እንደሆነ እራሱ በቅጡ አላውቅም ነበር። የትምህርት ቤቱ ጀመአ 14 አመት አስቆጥሯል። ብዙ ኡስታዞች መተው አስተምረውበታል ብዙ ዳእዋዎች ተደርገውበታል።ጀመአውን ትምህርት ቤቱ ስለማይፈቅደው ብዙ ተማሪዎች ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል።ከመባረር እስከ መታሰር ደርሰዋል።
ጀመአው በሊላሂ የተሰጠው አንድ ሰፋ ያለ ክፍል ቤት አለው።ምሳ ሰአት ላይ ሴቶች ይሰግዱበታል።በሳምንት ጁመአ ደግሞ አሚሮቹ ተሰብስበው ሹራ ያደርጉበታል።በየ ወሩ ደግሞ ሙሉ የጊቢው ሙስሊም ተማሪዎች ተጠርተው የዳእዋ ፕሮግራም ይሰጥበታል ። ከአሱር እስከ መግሪብ ደግሞ የሰፈሩ ህፃናት ቁራን ይቀሩበታል።ወንዶች ሰላት የሚሰግዱት መስጂድ ነው።የጀመአው ቤት ለሶላት ትንሽ ቢርቅም ሌላ አማራጭ ስለሌለ የግድ እንሄዳለን።
አልፎ አልፎም መንገዱ ሲሰለቸን እንዲሁም እየሩስ እና ትግስት አብራችሁን ዋሉ ብለው ሲለምኑን ክፍል ውስጥ የዩኒፎርም ሹራባችንን አንጥፈን አስተማሪ እንዳይደርስብን በሩን በውስጥ ቆልፈን እየሩስ እና ትግስት ከውጭ የሚመጣውን ሰው እየጠበቁልን እንሰግዳለን።
እየሩስ የምትኖረው ከአንዲት አሳዳጊዋ ጋር ነው እናትም አባትም የላትም ቢኖራትም የት እንደሚኖሩ ምን እንደሚመስሉ አታውቅም እነሱም ፈልገዋት አያውቁም። ለነገሩ እየፈለጓት ቢሆን እንኳን ያያቸው የለም። አሳዳጊዋ ያገኘቻት ቆሻሻ ውስጥ ተጥላ እንደሆነ ነግራታለች።የሰፈሩ ሰዎችም ይሄንን ታሪክ ስለሚያውቁ ምን በላሽ? ምን ጠጣሽ? የት ነሽ የት ዋልሽ? እያሉ ይንከባከብዋታል። በተለይ ደግሞ አሳዳጊዋ hiv ስላለባት እንድትጠነቀቅ ይመክሩዋታል።
ሌላኛው ከጎዳና አንስታ ያሳደገችው ልጅ ዳግምም ምንም እኳን አብረው ቢያድጉም ሴትነትዋን እንዳይነካ ያስጠነቅቁታል።ምክንያቱም ዳግም ብር ወዳድ እና ውለታ ቢስ ሰው ነው። አሳዳጊውንም መቃሚያ ብር ካልሰጠችው ይደበድባታል።
ትግስት ደግሞ የምትኖረው ከእናት እና አባትዋ ጋር ነው። ታላቅ ወንድም ቢኖራትም እስልምናን በመቀበሉ ምክንያት ከአባቱ ጋር ተጣልቶ ከሚሴ የምትባል ሀገር ሂዶ የራሱን ህይወት መኖር ጀምሯል። የትግስት እናት ዘይነባ ትባላለች የሙስሊም ልጅ ብትሆንም የትግስትን አባት ፍራኦልን በማፍቀሯ ምክንያት ሀይማኖቷን ቀይራ አግብታዋለች። የ ትግስት ታላቅ ወንድም መላኩ ከሰለመ በኋላ ስሙ አማር ሁኗል።
በመስለሙ ምክንያት ትግስትም በጣም ስለተበሳጨች ስሙን እንኳን መጥራት አትፈልግም።
Part 1⃣4⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል
🔻ክፍል 1️⃣4️⃣ ከ7️⃣0️⃣ 👍 በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍😀 ማድረግ አይርሱ
የፍቅር ቴሌግራም ቻናል
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!