💧〰〰〰አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰💧
የታሪኩ ርዕስ
💁♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
#ክፍል ☞ አስራ ስድስት 1⃣6⃣
✍ ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን
የአባትዋ ሞት ተከትሎ ወንድምዋ እናቱን እና ብቸኛ እህቱን ትግስትን ለመውሰድ ወደ አዲስ አበባ መጥቷል
ነገር ግን ትግስት ወደ ከሚሴ የመሄድ ሀሳብም ፍላጎትም አልነበራትም ከናንተ ጋር መኖር አልፈልግም ከሀዲዎች ናቹ የአባቴ ሞት ተጠቀማቹበት። አልወዳችሁም እያለች ብትጮህባቸውም እነሱ ሊተዋት አልቻሉም።በተለይ እናትዋ ዘይነባን እስከዛሬ ድረስ አባቴን ስትደልዪ ኖረሻል አፈቅርሀለው ብለሽ አታለሽዋል አባቴን ክደሽዋል ገና ከመሞቱ ሙስሊም ሆንሽ እያለች ነጋ ጠባ ትሰድባታለች።
ወንድሟም ወደ ከሚሴ ልውሰዳቹ ትምህርትሽን እዛ መቀጠል ትችያለሽ አሪፍ ሀገር ነው ለሙስሊምም ለክርስትያንም የሚሆን ሀገር ነው።ሁሉ ነገር አስተካክያለው የራሴንም ቤት ገዝቻለው ቢላትም አሻፈረኝ አላችው።
ትምህርት በጀመርንበት ወር አዲስ ለገቡት ለዘጠነኛ ክፍሎች የ well come ( የ እንኳን ደህና መጣቹ ) ፕሮግራም አዘጋጀን። well come ፕሮግራም አላማው ለአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ ጀመአውን እና የመስገጃው ቤት ማስተዋወቅ ነው። ያለንን አዋጥተን ኩኪስ እና ለስላሳ እንዲሁም ቴምር ገዝተን የ ዌልካም ፕሮግራሙን አዘጋጀን። አልሀምዱሊላህ ብዙ ተማሪዎች ተገኝተዋል።ትግስትንም የተለየ ነገር የለውም ብለን አባብለን ወደ ጀመአው ወሰድናት። ብቸኛዋ ሂጃብ ያለበሰች ሴት ስለነበረች የተማሪዎቹ አይን ቢያስፈራትም ተቋቁማው ፕሮግራሙን ከኛ እኩል ተካፍላለች። ሀዲስ ከሰማን በኋላ የጀመአው ጄነራል አሚር አቡበከር ትንሽ ንግግር አድርጎ ፕሮግራሙ ተቋጨ።
እኔና ዘቦም የጀመአው (የዳእዋ) ጥርያችንን እያቀላጠፍን ነው።በየክፍሉ እየዞርን የማይሰግዱትን ተማሪዎች እንዲሰግዱ የጀመአውን ቤት የማያውቁትን እያሳየን ጥሪ እናስተላልፍለን። ሂክማ(የፍይናንስ ዘትፍ አሚር) ለጀሙአው እርዳታ የሚያደርግ ሰው ልታገኝ ባለመቻልዋ አዝናለች። የምታውዋቸው የጠየቀቻቸው ሀብታም ናቸው ያለቻቸው ሰዎች ነገ ነይ ሳምንት ነይ እያሉ ያመላልሱዋታል እንጂ አይስጥዋትም።እኔም ላግዛት በማሰብ የማውቃቸውን ሰዎች ስጠይቅ አንዴ ደብዳቤ ፃፊ ይሉኛል ደብዳቤውን ፅፌ ስመለስ ደሞ ማህተም የለውም ይሄ የውሸት ጀመአ ነው ይሉኛል።
እኛ ደሞ ጀመአችን ከትምህርት ቤቱ እውቅና ውጪ ስለሆነ በትምህርት ቤቱ ስም ማህተም መጠቀም አንችልም። የሂክማ ስራ ከባድ እንደሆነ ስሰራው ነው የተረዳሁት። ግን ወላሂ ከሁሉም ስራ ተማሪን ወደ ጀመአው መጥራት ይከብዳል።ከ ሀ እስከ ፐ ማንነታችንን ያውቃሉ። እነዚህ ጨቅጫቃዎች መጡ እያሉ ይጠሩናል።አሰላሙ አለይኩም ስንላቸው የሚያፌዙብን ሴቶች ቁጥራቸው ብዙ ነው።ወአለይኩም ሰላም ከማለት ወአለይኩም ኩርኩም እያሉ ያላግጡብናል።አንዳንዶቹም ሰላም ይንሳቹ ሳይሉን አይቀሩም። አስተያየታቸው ግልምጫቸው ተስፋ ያስቆርጣል ሆኖም ግን የተሰጠን ሀላፊነት ከባድ ስለሆነ ፊታቸው እየገረፈን እየተመላለስን እንዲሰግዱ እንማፀናለን። እሺ ኢንሻ አላህ ነገ እመጣለሁ፤ሀይድ ላይ ነኝ፤ወደ ቤት ልሄድ ነው ፤እዚህ ነው የምሰግደው .......እያሉ የሚዋሹን ብዙዎች ናቸው።
የጊቢው ሰቃይ ተማሪም ሙስሊም ናት ሀናን ትባላለች። ውሎዋ ጊቢ ውስጥ ነው።ሶላት እንድትሰግድ ጥሪ ባደረግንላት ጊዜም እኔ ከትምህርት ከወጣሁ በኋላ ቤቴ ነው የምሰግደው አለችን።ከዚህ እስክትሄጂ አሱር ያዝናል እኮ ለምን እዚህ ከኛጋ አትሰግጂም ??ስንላት
..... እኔ ቀስሬ ነው ምሰግደው ምሳ ሰአቴን ላይብረሪ ነው ማሳልፈው ብላ በፈጣጣ መልሳልናለች።ከኛ ድክመት ይሁን ከተማሪው ስንፈት ባላውቅም ከለት ወደየ እለት ጀመአው ቤት እየሄዱ የሚሰግዱት ሴቶች ቁጥር በጣም ቀንሷል። ቤቱ ጠቦን ምንሰግድበት ቦታ አጥተን ለሁለት ጀመአ ተከፋፍለን በየተራ እንዳልሰገድን አሁን አሁን ቤቱም እየሞላ አይደለም።እንዳውም አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰልፍ ሰጋጆች ብቻ የሚኖሩበት ጊዜ አለ። ወላሂ እኛ የጀመአው አባላት ወደዛች ቤት ለመሄድ ምክንያት አንፈልግም ነበር ጁምአ ጁመአ ቅዳሜ እና እሁድ አልፎ ሰኞ እስኪደርስ እንጓጓለን። እርስ በራሳችን እንዋደዳለን ። ሀይድ ላይ ብንሆንም ባንሆንም ወደዛች ቤት መሄዳችንን አናቆምም ይናፍቀናል።
ምሳ የያዝን ምሳችንን ካልያዙት ጋር ተካፍለን ነው የምንበላው። ከ እህትማማቾች በላይ ነው ፍቅራችን።አንዳንዶቹ እዛች ቤት ላለመሄድ ስበብ ይደረድራሉ። ሰአዳም እንዲህ እንዲህ እያለች ነው የጀመአው ቤት መሄድ ያቆመችው። ውሎዋ ከነ እየሩስ እና ትግስት ጋር ነው። አሚራ ድሮውንም የምትሰግደው ቤትዋ ነው።በነገራችን ላይ 10 ክፍል ከገባሁ በኋላ አንዲት አዲስ ልጅ ክፍላችን ገብታለች መርየም ትባላለች ሲበዛ እብድ ናት።
#Part 1⃣7⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል
🔻ክፍል 1️⃣7️⃣ ከ7️⃣0️⃣ 👍 በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍😀 ማድረግ አይርሱ
የፍቅር ቴሌግራም ቻናል
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!