🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ጥቁር ልብ❤️
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ 💟
ክፍል 1️⃣5️⃣
በቃ ደግ አደረግሽ እንኳን መሬቱ ፆሙን አላደረ አልኳትና አመሰገንኳት።
አንዴ እንደናት አንጀት ሰጥቷት የሌ ስሄድ ሸኚ ስመለስ ተቀባይ ሆነች።
ተመልሼ ከሄድኩ ቡሀላ ከቤት ለመውጣትም አፍሬ ነበር ግን በቃ አልሞት ይሄን ያህል ብዬ መውጣት ጀመርኩ ደቦ ሲጠሩ መሄድ እና ያጎቴ ልጆችን ልክ እንደሱ ሆኜ አገዝኳቸው እህል አሰባሰብኳቸው።
የኔ ጣጣ እየተጎተተ ከጀርባዬ ተጠምጥሞ መከተሉን አላቆመም እና እህል ተሰብስቦ ሲያልቅ የእኩል የያዙት ሰዎች በየቤታችን የራሳቸውን እኩሌታ ወስደው የራሳችንን እህል መልሰው ይሰጡን ጀመር።
አንድኛው ሰውዬ ግን ቢጠበቅ ቢጠበቅ አልሰጥም አለ የእናቷ አጎት ነው ሰውዬው
ከዛ ሄዳ ጠየቀችው መልስ አልሰጣትም እኔም ሄጄ ጠየኩት በሷ መሬት አንተ ምናገባህ ብሎ መለሰኝ።
ሽማግሌ በተደጋጋሚ ስትልክበት የራሴን መሬት ነው መልሼ የወሰድኩት ከሰላሳ አመት በፊት የሷ አባት ከኔ ቀምቶኝ ነው አንዴ እጄ እስኪገባ ነበረ እንጂ አሁንማ ማን ይለቃል ብሎ ሽማግሌዎቹን መለሳቸው።
ባለቤቴ አልቅሳ ዝም አለች እኔ ጨነቀኝ ምን ላድርግ በጨለማ ተደብቄ አልመታው ነገር እንዳለ ዘመዶቹ ሽፍታ ስለሆኑ የነሱ ዘር የተፈራና የተከበረ ነው በቃ አርሴማ ቤቴክርስቲያን ሄጄ ድፍት ብዬ አልቅሼ ተመለስኩ።
እንግዲህ ይሄ ሁሉ ነገር የተፈጠረው እኔ ያቺን እናት ተብዬዋን ተከትዬ በመሄዴ ባለማገኔዘቤ ሚታረስበት ወቅት ነው ባለቤቴ ምን ትሆናለች ምን ታደርገዋለች ብዬ ሁለቴ ቆም ብዬ ባለማሰቤ ጥያት ስሄድ ሲጨንቃት ለሱ በመስጠቷ ነው እንግዲህ ይሄን መሬት የተቀማችው።
ግን ያንተ ጥፋት ነው ሳትለኝ ሳትወቅሰኝ ዝም አለች።
በገጠር በጋውን ሁሉም ሰው ቤት ነው አረም የለ እርሻ የለ አጨዳ የለ በቃ በክረምት የዘራውን በበጋ ቁጭ ብሎ መብላት ነው።
እኛም ከደረሰን እህል ላይ የተወሰነውን ሸጥንና አህያ ገዛን።
እህል ማመላለሻም ሆነ ለማንኛውም ነገር ያገለግለናል ብለን አስበን ነው የገዛነው።
ያው ጊዜው ይሮጥ የለ ድጋሜ የእህል መዝሪያ ጊዜ ደረሰና እህል ለመዝራት ሁሉም ጉድ ጉድ ማለት ጀመረ እኔም አንዴ የእኛ እርሻ አንዴ ያጎቴ እርሻ ካጎቴ ልጆችጋ እየሆንኩ መዝራት ጀመርን።
በዛውም ሰውዬው የቀማትን መሬት ለማረስ ስሄድ ከገዛ መሬታችን አባረረኝ
ባለቤቴ ዝም አለች ዝምታዋ አስፈራኝ ቢሆንም ነገሩን ለማብረድ ሞከርኩ ሰውዬው ከሌላው መሬት በተለየ የኛን መሬት መንከባከቡን የኛ መሬት ላይ ፍግ ማፍሰሱን ተያያዘው ምንም ሳያፍር ጭራሽ የማሽላ ዘር ዘራው የሀገሬው ሰው እንዴት ዝም አለች ብሎ እስኪገረም ድረስ ለኔም ለማንም ቃል ሳትተነፍስ ዝምም አለች በቃ።
ከዛ የተዘራው እህል ማሽላ ከሆነ ቶሎ ነው ሚበቅለውና በደንብ ስለተንከባከበው በሚያምር መልኩ ብቅ ብቅ ብሎ እድገት ማሳየት ሲጀምር ባለቤቴ ቀጥ ብላ ወጥታ ፖሊስና ታጣቂዎች ይዛ ቤቱ ግልብጥ ብለው ባላሰበበት ሁኔታ ከበቡትና ይዘውት ወደፍርድ ቤት ወጡ።
ፍርድ ቤት ቀረቡና ተካሰሱ እሱም የራሱን ምክንያት አቀረበ እሷም እንዴት ደም ተፍታ ኦንዳገኘችው ያሳለፈችውን እንግልትና ያባቷ ድርሻ እንደሆነ ተናገረች።
ዳኛው በጣም ተናደደ ሰውዬው ላይ አምና ከመሬቷ ያስቀረኽባትን እህል ሁለት እጥፍ አድርገኽ መልስላት።
ከዛም ተጨማሪ አሁን የዘራኸውን እህል ፖሊሶቹና ታጣቂዎች ባሉበት ቀጥ ብለህ ውረድና እራስህ ብቻህን አንድ ባንድ የበቀለውና ማሽላ ከመሬቷ ላይ በእጅህ ነቅለህ ጨርስ ካልሆነም እሷ ከነዘራኸው እህል መሬቷን ትውስድ አለ።
ባለቤቴ ግን የሱን ዘር እህል አልፈልግም ባዶ መሬቴን ያስረክበኝ ብላ ተከራከረች እንደዛ እየፎከረ ያረሰውን መሬት በፖሊስ እየተጠበቀ አንድ ባንድ እህሉን ነቅሎ ጨረሰ።
ከዛን ቡሀላ በሀገሬው ተዋረደ የዘራውን እህል አስነቀለችው ወንድ ናት እሱ ግን ድሮስ ማንእሷን ንካ አለው እያሉ ፈረዱበት።
እሱ ባገኛት ቁጥር አንቺንማ ደፍቼሽ ካልሄድኩ እያለ መዛት ጀመረ ።
እኔንም እሷንም ባገኘን ቁጥር የማስፈራሪያ አይነት ይወርድባት ጀመር እሷ ደንገጥ ሳትል ቀረች።
ይቀጥላል .....
🔻ክፍል1️⃣6️⃣ ከ 1️⃣0️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet💔
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔