♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
.
.
🌹...ክፍል 33...🌹
.
.
አጥብቄ አቀፍኳት።ሀረር መሀል ከተማ አላፊ አግዳሚው ሳያስጨንቀን እኔም በሷ ጉያ እሳም በኔ ጉያ ውስጥ ተጣብቀን ቀረን።
" እና እሺ አሁን ወዴት እንሂድ ?" አለችኝ ከቅፌ ሳትወጣ።
እና አሁን የት እንሂድ
"እኔ እንጃ ቃልዬ"
"እንዴ እኔ እ ን ጃ እና እንዲሁ መንገድ ለመንገድ እየዞርን እንደር?"
"እሺ የት እንሂድ እዛው የነበርንበት እንመለስ ቤቱን ወደሽዋል ነው እንቀይር ?"
"ኧረ እዛው ይሻላል ፀጥታው ደስ ይላል'
" ነይ በቃ አልጋ እንያዝና ቦርሳሽን አስቀምጠሽ እንወጣለን"
ተያይዘን ሄድን ።
ልክ ቃልዬ አዋክቤ ከመኪናው ላይ ሳወርዳት እቃ የረሳሁ እንደመሰላት ሁሉ የቤቱ ጥበቃ የሆኑት ጠና የሉ ሰውም እንዳዩን እቃ ረስተን የተመለስን መስሏቸው"
"ምነው ልጆቼ ምን ዘንጋታችሁ ወጣችሁ?" አሉን።
"አይ ምንም አረሳን አባቴ የመሄድ ሀሳባችንን ለነገ አሻገርነው ና ተመለስን" አለቻቸው ቃልዬ።
"ይሁን ከመሸ መሄዱም ደግ አደለም ነገ ብትሄዱ ይሻላል ግቡ ግቡ ልጆቼ " አሉን።
"አየሽ እኔም ታውቆኝ ነበር እኮ ለ አዛውንት እና ለህፃን ልጅ እኮ ይታየዋል "አልኳት የክፍላችንን ቁልፍ ተረክበን ትናንት ከነበርንባት በተቃራኒው በኩል ጥግ ላይ ያለችን ክፍል ውስጥ ከፍተን እንደገባን።
"ምኑ ነው የሚታየው ኤፍዬ?"
"በማታ ሲጓዝ መንገድ ላይ ምን እንደሚያጋጥመው ነዋ"
"ኪኪኪ እና እሺ አዛውንቱ እሳቸው ናቸው እንበል ህፃኑ ታድያ ማነው ኤፍዬ?"
"እኔ ነኛ "
"ማመንህም ደስ ይላል"
"ምኑን?"
"ህፃንነትህን ነዋ"
"ማነው ህፃን?"
"ኪኪኪ እንዴ ትቆጣለህ እንዴ ? አንተው እኮ ነህ ያልከው"
"እሺ እኔ ለማለት ያህል ልበል አንቺ ግን አጋጣሚውን ተጠቅመሽ የልብሽን መተንፈስሽ ይገርማል"
"ይሄኔ ነው መሸሽ አለ መሸሻ" አለች እየሳቀች።
"ማነው ደሞ መሸሻ"
"የድሬ ዩንቨርስቲ ጥበቃ"
"እሱ ደሞ ጥበቃ ሆኖ ማባረር ሲገባው ጭራሽ ይሸሻል እንዴ? ፈሪ በይው ፣ ለማንኛውም የልብሽን ተናግረሽ በመሸሻ ማምለጥ እይቻልም ማብራሪያ እፈልጋለሁ ቃልዬ ሙች አለቅሽም "
አልኳት አንገቷን አንቄ አልጋው ላይ በጀርባዋ እያንጋለልኳት።
"ታድያ ማብራሪያውን የምትፈልገው በተግባር ነው በአንደበት" አለችኝ በታነቀ ድምፅ።
"እንዴት?"
"አንገቴን አንቀኸኝ እንዴት ላብራራልህ?
" በተግባር ብልሽስ እንዴት ልታብራሪው ነው?" አልኳት አንገቷን ለቀቅ አድርጌ ፀጉሯን እየነካካሁ።
"እንደትናንት ማታው ነዋ" ስትለኝ ህፃን ተባልኩ ብዬ ኮስተር ለማለት የሞከርኩት ሙከራ መክኖ ሳቅ አፈነኝ።
"ምን ያስቅሀል?" አለችኝ እራሷ እየሳቀች።።
"እሺ በአንደበት ይብራራልኝ"
"ምነው የተግባር ማብራሪያውን ፈራኸው እንዴ?"
"አልፈራሁትም ፣ ለምንድን ነው የምፈራው ዛሬ ከድሬ ያስቀረሁሽ ለምን ሆነና እልህ ስለያዘኝ አይደል እንዴ"
"የምን አልህ ኤፍዬ?"
"ትናንት በመበለጤ ነዋ!"
"ኪኪኪ እና ምን ልትሆን?"
"ምን ልትሆን አልሽ ቃል ? ዛሬ አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጌ በመስራት ልክሽን ላሳይሽ ነዋ"
"ኪኪኪ ምንድን ነው ደሞ አቅም ግንባታ ?"
"አሁን ከዚህ ስንወጣ የሀረርን ሰንጋ ጥሬ ስጋ ነው የምበላው ከዛ ወንዱና ሴቱ ይለያል እንግዲህ"
ስላት ጥበቃው " አቤት ጠራችሁኝ እንዴ ልጆች?" ብሎ ክፍላችን ድረስ እስኪመጣ ነበር ሳቋን ጥበቃው ቤት ድረስ እስኪሰማ የለቀቀችው።
ጥበቃውን ነገሩ ወዲህ ብዬ በሩን ዘግቼ ስመለስም እየሳቀች ነው።
"ኪኪኪ አይ ኤፍዬ •••ኤፍዬ ሙት ጫወታህ እኮ አይጠገብም ።
" የምን ጫወታ ? አዎ ላንቺ ጫወታ ነው ዛሬ ልክሽን ካላሳየሁሽ ወንድ ያባቱ ልጅ አይደለሁማ"
"በ. ም. ን በ ጥሬ. ስጋ ?" እያለች በሳቅ ስትንከተከት እኔም አብሩያት ስንተከተክ ቆየሁና•••
ቃልዬ ሙች ትናንትም እኮ መብላት የፈለኩት ጥሬ ስጋ ነበር ግን ያንቺ ምርጫ ስላልነበር ነው የተውኩት"
"እና ዛሬም የኔ ምርጫ ጥሬ ስጋ መብላት ባይሆንስ?"
"ብቻሽን ትበያታለሻ ቀልድ የለም ፣ ከጥሬ ስጋ ውጪ ወይፍንክች ብያለሁ ወይ ፍንክች"
"ቆይ ቆይ ጥሬ ስጋ ወንድ ያደርጋል እንዴ?"
"ይሄኔ ነው መሸሽ ማለት ያለበት አሁን ነው መሻሻ! እንዴ ቃልዬ እንደቀልድ እያዋዛሽ ሞራሌ ላይ ታንክ መንዳት ጀመርሽ አደል?"
"እንዴ እንዴት ስለምን ታንክ ነው የምታወራው?"
"ከዚህ በላይ የሰውን ሞራል በታንክ መደፍጠጥ አለ እንዴ የምን ታንክ ትያለሽ እንዴ ደሞ? ጥሬ ስጋ ወንድ ያደርጋል እንዴ ? ማለትሽ ትናንትና ወንድ አልነበርክም ዛሬ ጥሬ ስጋ በልተህ ወንድ ልትሆን ነው ወይ? ማለትሽ አይደል እንዴ?"
"ጫ. ን. ያ. ለ. ው መጣ" አለች ቃልዬ ጋደም ካለችበት ቀና እያለች።
"ማን ነው ጫንያለው? የጥበቃው ስም ጫን ያለው ነው እንዴ?" አልኳት ወደ በሩን አየት አድርጌ።
"ኤፍዬ ሙት አንዳንዴ እየቀለድክ ይሁን እያመረርክ ይምታታብኛልኮ ለማንኛውም ኤፍዬ እኔ እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም ወንድማ ወንድ ነህ ሊያውም መለሎ ቁመት፣ ጠይም ፊት ፣ ያልወፈረ ም ቀጭን የማይባልም ተክለሰውነት ያለው ፣ ፊቱ ላይ ያለው የደስደስ ወደሌላው የሚጋባ ደስ የሚል የሀበሻ ወንድ!" አለችኝ።
የሰውነቴ ሙቀት በአንድ ግዜ እጥፍ ሲሆን ተሰማኝ። የድሬ ከተማ ህዝብ በሙሉ ተሰብስቦ ቃልዬ አሁን ያለችኝን ቢለኝ እንካን ይህን ያህል ሙቀቴ የሚጨምር አይመስለኝምበሚያፈቅሩት ሰው መሞካሸት የሚፈጥረው የደስታ ስሜት ልዩ ነው።
"አመሰግናለሁ ቃልዬ!" አልኳት። ከሰከንዶች ዝምታ በኃላ•••
"ኤፍዬ "
"ወዬ ቃል"
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 34 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMhu2unUT/