❤️ተማሪዋ❤️
❤️….ክፍል 38 ….❤️
.
በመሀላችሁ ያለው ፍቅር ነዋ አሁንም እንደሞቀ ነው?"
"ጭራሽ ብሶበት እየተንቀለቀለ ነው"ስለው አስቀያሚ ፈገግታ ከንፈሩን ወደ ጎን ለጥጦ ፈገግ ይልና
" ለማንኛውም በረድ ቀዝቀዝ ማለቱ ጥሩ ነው የተንቀለቀለን ነገር በቀላሉ ማጥፋት ከባድ ነው"ይላል። ዝም ብለውም ሲደጋገም
"ሁሌም እንዲህ ትላለህ ኪያ ቆይ ምን ልትለኝ እየሞከርክ ነው?••••
በክፋት አትየው ኤፊ ጋደኛዬ ሁሉም የመጀመሪያ ፍቅር አይሳካም በቃ እንከን አያጣውም አብዛኛው ሰው መጀመሪያ የፈቀራትን ወይ የፈቀረችውን አያገባም መጀመሪያ ከፈቀሩት ጋር የተጋቡ በጣም ጥቂቶች እንደሆኑ ደሞ እኔ ሳልሆን ያለው ሀቅ ነው የሚያረጋግጠው ። ቢሳካልህ እና ከቃልኪዳን ጋር ብትዘልቁ እኔም ደስ ይለኛል። ምናልባት ባይሳካ ግን በጣም እንድትጎዳ አልፈልግም ። እና በረድ አርገው የምልህ ለዛ ነው በሌላ አትየው"
ይለኛል።
"እባክህ ኪያ እኔ በቃ ምንም ልልህ አልፈልግም። ለምን እንዲህ አልክ ምን አየህ ምን ሰማህም አልልህም። ነገር ግን ፍቅር ስትፈልግ እምታነደው ስትፈልግ ውሃ አርከፍክፈህ የምታጠፋው የምድጃ ፍም አይደለምና ይህንን ብቻ ተረድተህ እኔን ተወኝ። በቃ እኔና አንተ ማውራት ካለብን ከኔና ከቃልዬ ውጪ በሆነ ነገር ላይ ብቻ እናውራ ካልሆነ ዝም ማለቱ ይሻላል" አለዋለሁ ኪያ ግን በሆነ ሰበብ ስቦ እንደዚህ አይነት ነገር እንድናወራ ከመወትወት ታቅቦ አያውቅም።
አንዳንዴ ንድድ ብዬ መልስ አልሰጥ ስለው ዝም ይላል፣ በሌላ ወሬ መሀል ሲያነሰብኝ እንዳልሰማሁ ሆኜ አልፈዋለሁ አልያም በቀጥታ ወደሌላ ርእስ በመሄድ አጨናግፍበታለሁ።
በዚህ ሁኔታ እኔና ቃልዬ ፍቅራችንን እያጣጣምን ቀጠልን። ከሀረር በመጣን ሁለት ወር እንደሞላን አከባቢ ስራ ላይ እያለሁ ድሬ ዳዋ ያለወትሮዋ ሰማዩዋ ጭፍግግ ብላል፣ አየሯም ይበርዳ፣ ባልተለመደ ሰአት ቀን አስራ አንድ ሰአት አከባቢ ጃኬት ልወስድ ወደቤት እየሄድኩ ከዋናው አስፋልት ወደኛ ሰፈር መግቢያው ጫፍ ላይ ኪያ ከቶማስ ጋር ቆሞ እያወራ ከሩቁ አየሁት።
ሳልጠጋ ባጃጇን አዙሬ በሌላ መንገድ ወደ ቤት ገባሁና ጃኬት ደርቤ ወደስራዬ ወጣሁ።
ከምሽቱ አምስት ሰአት አከባቢ ወደ ቤት ስገባ ኪያ ገነት ሱቅ በር ላይ ቁጭ ብሎ እየጠጣ ነው።
"ገኒ ሰላም ነው ? ኪያ እንዴት ነህ? ቀዝቀዝ ያለ ገኒዬ " አልኳትና ሄጄ አጠገቡ ተቀመጥኩ።
በሌላ ርእስ ላይ ስንጨዋወት ቆየንና በመሀል
"ዛሬ ከቶማስ ጋር ቆመህ አየሁህ ልበል እላይ መግቢያው አከባቢ?" አልኩት።
"ምነው?" አለኝ።
"አይ ምንም ከሩቁ ስለሆነ ያየኋችሁ ለማረጋገጥ ነው"
"አዎ ቆመን ነበር ድንገት ተገናኘንና ቆመን ሰላም ተባብልን ምነው እኔና ቶማስ ካንተ ጉዳይ ውጪ ሌላ ነገር ማውራት አንችልም እንዴ?"
"ቆማችሁ ነበር ወይ አልኩህ አዎ አልክ አደል አበቃ ትርፍ ነገር ማውራት አያስፈልግም ስለኔ ምን ታወራላችሁ አንተ ነህ እንጂ እዛው ላይ የተቸነከርከው እኔ ከረሳሁት ቆየሁ እኮ ምን ያለበት ምን አይችልም አሉ " ብዬው በመነሳት ወደቤት ስሄድ።
"አይ እንደዛ መስሎህ ከሆነ ብዬ ነዋ ግን እርግጠኛ ነህ ኤፊ ረስተኸዋል? አለኝ።
መልስ ሳልሰጠው ወደቤት ገባሁ። ከቶማስ ጋር ባየሁት በሳምንቱ ስራ ላይ ሆኜ ምስ ሰአት ላይ ስልኬ ጠራ። አውጥቼ ተመለከትኩት ኪያ ነው። የጫንኳቸው ሰዎች መውረጃቸው ተቃርበው ስለነበር ዝም አልኩት ። ወድያው ደግሞ ደወለ፣ አላነሳሁትም። ሰዎቹን አድርሼ ሂሳቤን ከተቀበልኩ በኋላ እዛው እንደቆምኩ ደወልኩለት።
" ሄሎ ኤፊ"
"እ ኪያ አማን ነው"
"አማን ነኝ የት ነህ?"
"የት ነህ ማለት? ስራ ላይ ነኛ"
"እርግጠኛ ነህ ? ተው ባክህ ስራ ላይማ አይደለህም"
"ምን ማለት ነው ስራ ላይ አይደለህም ማለት?"
"አሁን ኮኔል መለዋወጫ ገዝቼ ስመለስ ያየሁት እናንተን አይደለም እንዴ?"
"እናንተን ማለት?"
"በርግጥ እሷን ነው እንጂ በደንብ ያየኋት አብሯት ያለው ወንድ አንተ ሁን አትሁን መለየት አልቻልኩም"
"ምን እያወራህ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም ኪያ ለምን በግልፅ አትናገርም?"
"አሁን ከአንድ ከአስር ደቂቃ በፊት ከቃልኪዳን ጋር ምሳ ልትበሉ ወደ ሆቴል ስትገቡ አልነበር?"
"እንደዚህ አይነት ቀልድ ያስጠላኛል ስራዬን ልስራበት እሺ"
"በእውነት እየቀለድኩ አይደለም ቃል ኪዳንን በደንብ አይቻታለሁ የተሳፈርኩበት ባጃጅ ፍጥነር ስለነበረው እልፍ ስንል አብሯት የነበረውን ወንድ በጨረፍታ ስላየሁት ነው እርግጠኛ ያልሆንኩት "
እሄ ልጅ ከኔና ከቃልዬ አናት ላይ አለመውረዱን ሳስብ ውስጤ ሲነድ ተሰማኝ።
"የት ሆቴል ነው ስንገባ ያየኸው?" አልኩት የሆቴሉን ስም ነገረኝ። ቻው በቃ አልኩትና ወደሆቴሉ በረርኩ። እሄ ልጅ የምሩን አይቷት ይሆን እንዴ ? በፍፁም ሊያያት አይችልም ። በዛው በቶማስ በኩል የማጣራት ስራውን እንደቀጠለበት እርግጠኛ ሆንኩ።
ሆቴሉ አብዛኛውን ደንበኛቹን የሚያስተናግደው እቤት ውስጥ ሳይሆን ሰፋ ባለው ነፋሻማ ግቢው ውስጥ ነው። ከውጪ ወደ ግቢው በደንብ ስለሚታይ ወደ ውስጥ መግባት አያስፈልገኝም።
ባጃጄን ጠጋ አድርጌ አቆምኩና ሳልወርድ እዛው ባጃጄ ውስጥ ሆኜ ወደ ውስጥ አማተርኩ። ከሆቴሉ በር በስተቀኝ በኩል ካሉት ተስተናጋጆች መሀል ቃልዬ የለችም።
ትንሽ ዝቅ ብዬ አየት ሳደርግ ከሆቴሉ መግቢያ በር በስተግራ ባለች አንዲት ዛፍ ስር ባለ ወንበር ላይ ቃልዬን አየሁዋት።እየበሉ ነው። አጠገቧ ያለው ዛኪ ነው። ጠቅልሎ ሲያጎርሳት አብሪያት አፌን ከፈትኩ።
ምን ሆኖ ነው ለሴት ልጅ ይህንን የሚያህል ጉርሻ ፣ የሚሰፋ ይስፋው እና አፏን ሊያሰፋው ነው እንዴ?••••
እያልኩ ወጥተው ወዴት እንደሚያመሩ ብቻ ለመመልከት ራቅ ብዬ አደፈጥኩ።
ቃልዬ ከዛኪ ጋር ምሳ መብላቷ ሳይሆን የኪያ ቃልዬን መከታተል አንጀቴን አሳረረው። ደሞ ሳልፍ አየኋችሁ ሲል አያፍርም እንዴ ገገማ!" እያልኩ እነቃልዬ ከሆቴሉ ወጥተው ወደግቢ ስሄዱ ከጀርባ ሆኜ ሸኘኋቸውና ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከኔና ከቃልዬ መሀል እንዲወጣ ላስጠነቅቀው ኪያ ወደሚሰራበት ገራዥ በደም ፍላት እየተንተከተኩ ባጃጄንም እያንተከተኩ ሄድኩ።
ገራዥ አብረውት የሚሰሩ ጓደኛቹ ኪያ የለም እቃ ሊገዛ ወጥቷል ቢሉኝም አልተዋጠልኝም። ደወልኩለት አያነሳም ። እዛው ገራዥ ውስጥ ሆኖ የለም እንዳስባለ እርግጠኛ ነበርኩ።
ወደስራዬ ብመለስም ቀልቤን ሰብስቤ መስራት አልቻልኩም። እርብሽብሽ አልኩ። ለቃልዬ ደወልኩላት፣ እንደሁልግዜው በፍቅር አወራችኝ። ከዛኪ ጋር ምሳ ስትበይ አየሁሽ አላየሁሽ ልላት ባልፈልግም እኔ ባልጠይቃትም ብትነግረኝ ግን ደስ ይለኝ ነበር። ባለመናገሯ ቅር አለኝ።
ኤፉዬ ዛሬኮ ከአክስቴ ልጅ ጋር ምሳ ልበላ ወጣ ብዬ ነበር ብላ ብትነግረኝ ሲሆን ሲሆን ዛሬ ከዛኪ ጋር ወጣ ብለን ምሳ ልንበላ ነው ብላ ብትነግረኝ ምናለበት? ቆይ ምናለበት? ምንም በቃ ምንም የለበትም። ምሳ ከሱ ጋር መብላቷ እኔን አያስከፋኝ።
እሷ ያን ያህል ግልፅ ብትሆን ግን ኪያን ከመሳሰሉ ፀረ ፍቅር ሰላዬች አትጋለጥም ነበር። እኔንም ከመረበሽ ታድነኛለች። ግን እሷ ምን ታድርግ እራሴው አይደለሁ እንዴ ለኩያ የቀባጠርኩት?። ኡፍፍፍፍ ።
.
.
.
https://vm.tiktok.com/ZMhgxmFMK/

Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
TikTok · salodatrading
76 likes, 2 comments. “#cornerclamp #habesha #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ethiopiafurniture #salodatrading #የፈርኒቸር #የፈርኒቸር_ጨረታ #የፈርኒቸርገበያማእከል #liqfurniture #ertirantiktoka🇪🇷 #eastafricantiktoks #viralvideo #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ሀገሬ #legsofa #passyourwavytalk ”