❤️❤️ተማሪዋ❤️❤️
.
🌹🌹…….ክፍል 48 ……🌹🌹
.
አላወቅኩም ቆይ እስቲ ጥበቃውን ልጠይቅልሽ " ብያት ወደ ጥበቃው ስመለስ አሁንም እማርኛ እና የነጮቹን አፍ እየቀላቀለች ስላስቸገርኩህ ይቅርታ አይነት ነገር አለች ። መልስ ሳልሰጣት ሄጄ ጥበቃውን...
"አባባ የሚላላከው ልጅ አለ እንዴ ? ዲያስቦራዋ ፈልጋው ነበር?'' አልኳቸው።
"ውይ ፈለገችው እሱማ መሄጃ ሰአቱ ደርሶ ወጣኮ ምሽት ሁለት ሰአት ወደ ቤቱ ሄደ። ምን ፈልጋ ይሆን ?" እያሉ አብረውኝ ተመለሱና ልጁ እንደለለ ነገሯት።
እዛው ቆም ብዬ እኔ ከወጣሁ በኋላ የተያዙና መብራት የበራባቸውን ክፍሎች ገልመጥ ገልመጥ እያልኩ ስቃኝ። ዲያስቦራዋ ልጁን የፈለገችው ቢራ ከውጪ ገዝቶ እንዲያመጣላት እንደነበር ስትነግራቸው ጥበቃው አንዴ እሷን
አንዴ እኔን አንዴ በሩን በየተራ እየተመለከቱ።
"አይይይ ግድ ከሆነና ካስፈለገሽ እኔው ሄጄ ላምጣልሽ ይሆን የኔ ልጅ?••• ልጁማ ሰአቱ ደርሶ ወጣኮ ቀደም ብትይ ደግ ነበር?'' አሏት። አሳዘኑኝ። ለሷ ሳይሆን ለሳቸው ስል አንዳፍታ ገዝቼ ላቀብላትና ገብቼ ልተኛ አሰብኩና
"ችግር የለውም አባቴ እርሶ ከሚሄዱ እኔ አመጣላታለሁ"
ስላቸው ገና መርቀውኝ ሳይጨርሱ ለሳቸው ጉርሻ መቶ ብር ጨምራ የቢራ መግዣውን ብር ሰጠቻቸው ።
የሳቸውን ለሳቸው ሰጥቼ ቢራውን ልገዛላት ስንቀሳቀስ ከዳግም ምርቃታቸው አስከትለው ቆይ የኔ ልጅ ጠርሙስ ካልያዝክ ማስያዣ ይጠይቁሀል ጠብቀኝ ጠርሙስ ላምጣ ብለውኝ ግቢ ውስጥ ወዳለ አንድ ክፍል አምርተው አራት የቢራ ጠርሙስ ይዘውልኝ መጡ።
ተቀብያቸው ልወጣ በሩን ከከፈትኩ በኃላ እዛ አከባቢ በግራም በቀኝም ሆቴል አለማየቴን አሰብ አድርጌ••••
"እታች ወርጄ ነው የምገዛው አደል አባባ እዚህ አከባቢ በቅርብ ሆቴል የለም አደል?" ስላቸው •
"ውይ የኔ ነገር የምትገዛበትን ሳላመላክትህ ሰደድኩህ አደል የኔ ልጅ ፣ ለካ አታውቀውም እያሉ ከግቢ ወጡና ካለንበት በቀኝ በኩል ትንሽ ሄደት ብዩ ወደ ግራ ቁልቁል የምትወስድ ቀጭን
መንገድ እንዳለችና ገባ እንዳልኩ ሆቴል እንደማገኝ ነገሩኝ። ከዚህ በፊት አላውቀውም ሆቴሉን ምናልባት በቅርብ የተከፈተ ይሆናል እያልኩ ወደ ሆቴሉ አቅንቼ ግቢ ውስጥ ስገባ ግቢው ጭር ያለ ነው ። ወደ ሆቴሉ ከሩቅ ሳማትር አለፍ አለፍ ብለው ወንበር ይዘው በተከፈተው ለስላሳ ሙዚቃ የሚዝናኑ ውስን ሰዎች ይታያሉ።
ራመድ ራመድ እያልኩ ወደሆቴሉ ዘው ብዬ እንደገባሁ ፊት ለፊት ባየሁት ነገር ልቤ ስንጥቅ አለች። ወይኔ አምላኬ ምንድን
ነው የማየው ? ጭራሽ እኔ የገዛሁላትን አዲሷን ልብስ••• እያልኩ በሁለቱም እጆቼ ሁለት ሁለት ባዶ የቢራ ጠርሙዝ እንዳንጠለጠልኩ ድንጋጤዬ አብረክርኮት አልራመድ ያለኝን እግሬን በግድ እየጎተትኩ በቀስታ ወደ ተቀመጡበት ወንበር ተጠጋሁ በሆቴሉ ውስጥ ጭልም ደሞ ብርት የሚሉ ሲበሩም ደብዛዛ ብርሀን የሚፈነጥቁ ጌጣማ አንፖሎች እዛም እዛም ተሰቅለዋል ፣
ቀረብ ስል ግራ ገባኽ አብሯት ያለው ወንድ ፊቱ በደንብ ታየኝ። ዛኪ አይደለም።ገዘፍ ያለ ነው። አስተያየቱ ደሞ ያስፈራል። ገልመጥመጥ ሲያደርገኝ እነሱን እያየሁ በቀጥታ ወደነሱ መሄዴን ቀየር አደረኩና እንደማለፍ ብዬ አየት ሳደርግ ልጅቷም ቃልዬ አይደለችም። ቀሚሱዋም ዲዛይኗ የቃልዬ አይነት ቢሆንም ' ከለሯ 'በተወሰነ መልኩ ይለያል።
የስራሽን ይስጥሽ ቃልዬ፣ ግራ የገባኝ ደግሞ ተከትያት ሀረር ከመጣሁ በሁዋላ የተጠናወተኝ በቅርብ ርቀት ያየኋት ሴት ሁሉ ቃልዬን የምትመስለኝ በሽታ ነው ፣ ይሄ መታመም ካልሆነ ምን ይሆናል ? እያልኩ ቢራውን ገዝቼ ተመለስኩ።
የግቢው ጥበቃ የቀራቸውን ምርቃት ሁሉ አሟጠው መረቁኝ።
"የእኔን እድሜ ያድለህ ፣ ጧሪ አያሰጣህ፣ የማታ እንጀራ ይስጥህ፣ የልጅ ልጅ ያሳይህ•••••" ሌላም ሌላም ብዙ ምርቃቶች።
"አባባ " አልኳቸው እንደጨረሱ።
"ወዬ የኔ ልጅ"
"ፍቅር ይዝለቅልህ!" ብለው ይመርቁኝ አልኳቸው እንባ እየተናነቀኝ።
"ፍቅር ይዝለቅልህ ፣ የወድድካትን ያፈቀርከትን ክፉ አይይብህ ፣ ትዳርህን ይባርክልህ !
" አሜን አሜን አሜን አባቴ" አልኳቸው ዋናው እሱ ነው ። እኔ የልጅ ልጅ ማየት የምፈልገው ከቃልዬ ነው። ከቃልዬ ከነጠለኝ በሁዋላ ረጅም እድሜ ምን ሊጠቅመኝ። እያልኩ ቢራውን ሰጥቻት ወደ ክፍሌ ገባሁ።
ቃልዬ ከዛኪ ጋር ማደሯን ማሰብ አስፈሪ እንደሆነብኝ ድካምና ረሀቡ ነው መሰለኝ የወደቅኩበትን ሳላውቅ ነጋ።
ጥዋት ወደ ድሬ ዳዋ ስመለስ ቃልዬ እራሷ እስክትደውል ላልደውልላት በናቴ ማልኩ።
ሳትደዉል መሸ፣ ሳትደውል ነጋ ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ቀንም እንደዛው ልደውል ስልኬን ካወጣሁ በሁዋላ በናቴ መማሌ ትዝ ሲለኝ ስልኬን ወደ ኪሴ እመልሰዋለሁ።
በአራተኛው ቀን ደወለች ።
"ይቅርታ ኤፍዬ በዚህ ምርቃት ሰበብ ተዋክቤ፣ ቻርጀሬ ጠፍቶ ፣ ባትሪ ዘግቶ••••" ብዙ ብዙ አለች ፣ ለመጥፋቷ ብዙ ምክንያት ብዙ ሰበብ ተናገረች ቃል። ዝም ብዬ ሰማኋት።
ስትጨርስ አንድ ነገር ብቻ ተናገርኩ ። አንድና አንድ ነገር ብቻ አልኳት።
"ችግር የለውም ቃልዬ በጣም ላገኝሽ እፈልጋለሁ መች ይመችሻል?" የሚል ጥያቄ ብቻ ሰነዘርኩላት። ድምፄ መሰባበሩ ለኔ ቢታወቀኝም ለሷ አላታወቃትም አልያም አላስተዋለችውም።
"ኤፍዬ አብረን ለመዋል ከሆነ ነገ ፣ ለማደር ከሆነ ግን ከነገ ወድያ"
"አይ ችግር የለውም አብረን ውለን ትሄጃለሽ"
"በቃ ነገ ከሰአት ደውልልኝ "
የቃልን ስልክ እንደዘጋሁ ጌትነት ስልክ ላይ ደወልኩ።
እቤቱን ለአንድ ቀን እንደምፈልገው ነገርኩት።
"ችግር የለውም ኤፍዬ ማደርም ትችላለህ እኔ ጀለሶቼ ጋር እሄዳለሁ" አለኝ።
ቃልዬን ላመጣት ስሄድ ለጌትነት ደውዬ ልመጣ ነውና ቁልፉን አስቀምጠህልኝ ሂድ አልኩት።
ደረስኩ ተገናኘን ። ስማኝ ከጀርባ ገባች። ደንዝዣለሁ። ምንም አላወራም ቃልዬ ግን ምን ያህል እንደናፈቅኳት ፣ ስለሰሞኑ የምርቃታቸው ወከባ ምን ያህል ግዜ እንዳሳጣት እያወራችልኝ የማውራት እድል ሳትሰጠኝ እነ ጌትነት ቤት ደረስን።የማውራት እድል ብትሰጠኝ ምን እንደማውራ አላውቅም።
ገብተን ትንሽ እንደቆየን ከምን እንደምጀምር ምን እንደምላት ጨነቀኝ።
ካንድም ሁለት ሶስቴ ልጀምር እልና የሆነ የሚረብሽ ስሜት እየተናነቀኝ አቋርጠዋለሁ። ተነስቼ ወደ መታጠቢያ ቤት እሄድና በቀዝቃዛ ውሃ ፊቴን ታጥቤ እመለሳለሁ።
ቃልዬ ቡና ለማፍላት እየተንጎዳጎደች ሁኔታዬን ማስተዋል አልቻለችም።
አቦሉን እንደጠጣን •••
"በቃ ሁለተኛውን አታፍይ ይቅር " አልኳት።
"ለምን ኤፍዬ?" አለችኝ ፊት ፊቴን እያየች።ፊቴ ልክ እንዳልሆነ ያስተዋለችው ያኔ ነበር። መጥታ አጠገቤ ተቀመጠች።
"ምን ሆነሃል ኤፍዬ ችግር አለ?" አለችኝ አገጬን ይዛ ወደግራም ወደቀኝም ገልበጥ ገልበጥ እያደረችኝ።
"አዎ ችግር አለ ቃል"አልኳት አገጬ ላይ ያለውን እጇን ይዤ ከአገጬ ላይ እያወረድኩት።
"ምንድን ነው እሱ?" አለችኝ ልቧን በግራ እጇ ደገፍ አድርጋ እየተመለከተችኝ። ልቧ ነገራት ብዬ በውስጤ እያሰብኩ ዝም አልኩ።
"ኤፊዬ!" ብላ ተጣራች።
"ወዬ ቃል"
"ምን ሆነሀል ?" ምን ሆንኩ እንደምላት ቸገረኝ።
"ቃልዬ" አልኳት።
"ውዬ"
"ታፈቅሪኛለሽ?"
.
.
ክፍል 49 ከ150 ላይክ ቡሀላ ይቀጥላል
https://t.me/saloda_trading