❤️ ተማሪዋ ❤️
❤️….. ክፍል 49 …….❤️
"ምን እሚሉት ጥያቄ ነው እስከዛሬ ምን ያህል እንደማፈቅርህ አታውቅም እና ነው ቆይ ምንድን ነው የሆንከው ፊትህ እኮ ልክ አይደለም?"
"ፉቴ ብቻ አይደለም ሁሉ ነገሬ ልክ አይደለም ቃል እባክሽ ለምጠይቅሽ ጥያቄ ብቻ መልስ ስጪኝ አንቺ ምንም ነገር አትጠይቂኝ"
"እሺ"
"ታፈቅሪኛለሽ ቃል"
"አዎ ኤፍዬ አፈቅርሀለሁ"
"ዛኪንስ ታፈቅሪዋለሽ ቃል?" ስላት ፊቷ ላይ ያየሁት ድንጋጤ እኔኑ አስደነገጠኝ።
ያ ድንጋጤዋ ነበር የመጨረሻውን መርዶ ያረዳኝ። በቃ የቃልዬን መልስ ድንጋጤዋ ውስጥ አየሁት።
ቃልዬ ብዬ ጠራሁዋት አይን አኗን እየተመለከትኩ።
ወዬ ማለት አልቻለችም። በቃ አቃታት። የኔም የሷም አይኖች እኩል እንባ አቀረሩ።
" ቃልዬ!" ብዬ ደግሜ ጠራኋት።
አይን አይኔን ከማየት ውጪ አቤትም ወዬም ማለት ተሳናት ቃል አፏ ተለጎመ። የስረኛው ከንፈሯ ይንቀጠቀጥ ጀመር።
ጣቴቻን በጣቶቿ እያፍተለተለች ተለጎመች የኔ ቃል።
ሁሉን ነገር እንደደረስኩበት ውስጧ ነግሯታል።
ይህን ሳስብ አመመኝ ።
ቃልዬ ሁኔታዋ አንጀት ይበላል።
የሚታዘንልኝ እኔ ሆኜ ሳለሁ ቃልዬ በዛ ልክ ጭንቅ ጥብብ ሲላት ሳይ አሳዘነችኝ።
ያን ሲተናነቀኝ የነበረውን እውነት መናገር ጀመርኩ•••
ቃልዬ አውቃለሁ ሁሉን አውቃለሁ። ከቀናት በፊት ሀረር እስከሄዳችሁባት አስቀያሚ ቀን ድረስ ይቺ ቅፅበት በኔና ባንቺ መሀል እንዳትፈጠር ስሸሻት ኖሪያለሁ።
ነገር ግን እውነትን መሸሽ ከሞት እንደማያድነኝ ተረዳሁ። አዎ ቃልዬ አንቺን ከማጣ ሞቴን እመርጣለሁ፣ መሞት አልፈልግምና አንቺን ማጣት እፈራለሁ።
እኔ ስለፈራሁት እኔ ስለሸሸሁት የሚቀር ነገር የለም።
ሁሌም አፈቅርሻለሁ። ምንም ብትበድይኝ ምንም ብትጎጂኝ አንቺን አለማፍቀር እስክችል ድረስ አፈቅርሻለሁና ዛሬም ቢሆን አንቺን ክፉ የምናገርበት አንደበት የለኝም።
ክፉ ይናገረኛል አልያም ይጎዳኛል ብለሽ እንዳታስቢ እሺ? ፣ እኔ አንቺን የማፈቅርሽ የእውነት ነው ፣ የማፈቅርሽ ግን የኔ ስለሆንሽ ብቻ አይደለም።
ዛሬም የማልፈልገው አንቺን አለማፍቀር ሳይሆን እየታመምኩ፣ እየተረበሽኩ፣ እንቅልፍ እያጣሁ፣ የተበዳይነት፣ የተገፊነት ስሜት እያንገላታኝ ማፍቀርን ነው።
ነገ ከነገ ወድያ ላጣሽ ልትለይኝ እንደምትችይ እያሰብኩ ማፍቀር ደከመኝ ቃልዬ።
አብሬሽ ሆኜ የተሰቃየሁት ስቃይ አጥቼሽ ከምሰቃየው ጠናብኝ ቃልዬ ።
ሀለቱም ለኔ ህመም ቢሆንም ከእውነት ጋር መታመም ይሻላል እውነትን ሸሽቼ የማላመልጥበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁና የምደበቅበት የምሸሽበት የለኝም እውነቱን ልጋፈጠው የተገደድኩት ሁሉ ነገ ካቅሜ በላይ እስከሚሆን ታግሼ ነውና በውሳኔሽም በውሳኔዬም እንደማልፀፀት ተስፋ አደርጋለሁ።
አንድም ቀን በዚህ ልክ ትጎጂኛለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ቃልዬ።
ዛሬ እውነቱን ካንቺ አንደበት ሰምቼ ሀቁን ልጋፈጠው ወስኛለሁ። ስለትናንት አልወቅስሽም፣ ስለነገም አላውቅም አሁን የምፈልገው በራስሽ አንደበት እውነቱን እንድትነግሪኝ ብቻ ነው ቃልዬ።
" ዛኪን ታፈቅሪዋለሽ አደል ቃል?"
"እ ቃል እባክሽ ንገሪኝ ዛኪን ታፈቅሪዋለሽ አደል?"
ቃልዬ መልሷ ማልቀስ ብቻ ሆነ። ከጎኔ ቁጭ ብላ ስታለቅስ ሰውነቴ መንቀጥቀጥ ጀመረ። እራሴን ፈራሁት። ስሜታዊ ሆኜ ቃልዬ ላይ እጄን እንደማልሰነዝር ባውቀውም እራሴን ፈራሁት ከአጠገቧ ተነስቼ በመራቅ ፊት ለፉቷ ተቀመጥኩ።
አቀርቅራ ስታለቅስ ቆየችና ድንገት ቀና ብላ
"ኤፍዬ ይቅርታ!" አለችኝ። ሰማይ ተደፋብኝ። ቤቱ የሚሽከረከር መሰለኝ። ከተቀመጥከበት እንዳልወድቅ አይኔን ጨፍኜ ግርግዳውን ተደገፍኩ።
"ኤፍዬ ይቅርታ !" አለች በድጋሚ። መልስ አልሰጠኋትም።
ቃልዬ ቀጠለች ••••
"እኔና ዛኪ እዚህ ግቢ ትምህርት እንደጀመርኩ የዛሬ ሶስት አመት ነው በፍቅር አብረን የሆነው ፣ " ስትል ገና ከግር ጥፍሬ ጀምሮ ሁለመናዬን ወረረኝ። እያየኋት ልሰማት አቅም አጣሁ። ጭንቅላቴን ጉልበቶቼ መሀል ደፍቼ አቀረቀርኩ ። ቃልዬ ቀጠለች...
"ፍቅር ጀምረን ወራት ያህል እንደቆየን ስለሱ ብዙ ነገር እሰማ ጀመር ከብዙ ሴት ጋር እንደሚቀራረብ ባውቅም አምነው ነበር። ሁሉንም ነገር የምሰማው በውሬ ነው። ስጠይቀው ይክደኛል ። ያን ቀን አንተና እኔ በተገናኘንበት ምሽት አንዷ ሴት ጋደኛዬ ዛኪ ከሌላ የግቢ ሴት ጋር የለበትን ሆቴል ነግራኝ ነበር ሳንቲም እንኳን ሳልይዝ አለ ወደተባለበት በርሬ የሄድኩት።
ግን አጣሁት መመለሻ ሳንቲም እንኳን ልነበረኝም ። ዛኪን ከዛ በኋላ አብሬው ላልቀጥል ወስኜ ነበር። ለምን በዛ ሰአት እዛ ሆቴል በር ላይ እንደቆምኩ አንተ ስጠይቀኝ ሌላ ግዜ እነግርሀለሁ ነበር ያልኩህ። ዛኪን አየሁት ብላ የደወለችልኝ ሴት ያንን አጋጣሚ ተጠቅማ አብረዋት ከነበሩ ሁለት ወንዶች መሀል ከአንደኛው ጋር ልታቀራርበኝ ስትሞክር ተናግሪያት ወጣሁ። በዛ ሰአት ነበር አንተ መጥተህ ፊት ለፉቴ የቆመከው ። ይህንን ደሞ በመጠኑም ቢሆን ነግሬሀለሁ። ኤፍዬ የኔና ያንተ ነገር ከተዋወቅንባት ምሽት ጀምሮ መቀራረባችን እና ወደ ፍቅር መግባታችን እንዴት እንዴት እንደፈጠነ ታውቃለህ።
እኔና አንተ ወደፍቅር በገባንባት ሁለት ወር ውስጥ ከዛኪ ጋር ተኮራርፈን ነበር ።ድጋሚ የምታረቀውም አልመሰለኝም ነበር።
ነገር ግን ልጅቷ ሆን ብላ እኔን ለሌላ ወንድ ለማጣበስ ስለሱ መጥፎ እያወራች እንዳጣላችን በየቀኑ እየመጣ ይነግረኝ ነበር። መውጫ መግቢ መቆሚያ መቀመጫ አሳጣኝ። ካንተ ጋር ሆኜ እንኳን ስንቴ እንደሚደውልና ስንቴ ተነስቼ ካጠገብህ እየሄድኩ እንደማዋራው ታስታውሳለህ።
በቃ ታረቅን። እኔና እሱ ስንታረቅ በጣም ተጨነቅኩ። ዛኪን የታረቅኩት ትምህርቴን ተረጋግቼ ለመጨረስ ብቻ ነበር።
አንተን ልጎዳ ብዬ ያደረኩት ምንም ነገር የለም ። ከዛኪ ጋር እዛ ግቢ ውስጥ እስካለሁ ድረስ መውጫ መግቢያ ስለሚያሳጣኝ መለያየት ከባድ ቢሆንም አብረን እንደማንዘልቅና ከተመረቅን በኋላ እንደምንለያይ እርግጠኛ ነኝ። አንተን •••ብላ ልትቀጥል ስትል መስማት አቅለሸለሸኝ።
የመጨረሻ ክፍል ረቡዕ ማታ 2:00 ላይ ❤️🙏🏻
https://www.instagram.com/reel/DD6fkUSu_mv/?igsh=MWRkNjA2dWFvMzg1eg==