በጥንት ግዜ ነው አሉ እንደ አቅምህ ሁለትም ሦስትም ማግባት በሚቻልበት ግዜ አንዱ ጎልማሳ ወጣትና ዕድሜዋ ገፋ ያለችዋን አግብቶ ይኖር ነበር።
ሁለቱም ሚስቶቹ ይወዱት ነበር። ሁን ያሉትንም የሚሆን ታዛዥም ባል ነበር።የሚወዱት መንገድ ግን ይለያያል። ወጣቷ እሷን እንዲመስልላት ዕድሜዋ ገፋ ያለችዋም እሷን እንዲመስልላት ነበርና ፍላጎታቸው።
ሰውየው ጎልማሳ ስለነበረ ፀጉሩ መሸበት ጀመረ።
ወጣቷ ሽበቱ ባሏን ያስረጀባት ስለመሰላት ውስጣ ሰላም አጣ ስለዚህ ማታ ማታ ደረቷ ላይ ጋደም እያደረገች ሽበቶችን መንቀል ስራዋ አደረገችው።
አሮጊቷ ደሞ የባሏ መሸበት ቆንጆ እና በሳል ሆኖ ስለታያት ሙሉ በሙሉ ነጭ ቢሆንልኝ የሚልም ፍላጎት ስለ ነበራት ጠዋት ጠዋት ፀጉሩ ላይ ያለውን ጥቁር ጥቁሩን እየመረጠች መንቀል ስራዋ አደረገችው።
ይህ የሁለቱ ሴቶች " ትግል" ግን ሰውየውን መጨረሻ "መላጣ"አድርጎት አረፈው።😁
"ሁሉንም ማስደሰት መሞከር ሁሉንም ማስከፋት ነውና"
ትሩጓሜው ራሳችሁ ተርጉሙት ✌
መልካም ቀን