♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 2...🌹
Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው
"እሺ የቱጋ ይዤ ልዘቅዝቅሽ••••? ነይ ውረጃ ባጃጇ ውስጥ ዘቅዝቆ ለማራገፍ አይመች!የቱጋ ቆሜ አንቺን ተሸክሜ አራግፋለሁ! ስለዚህ ነይ ውረጅ " ብያት የባጇጇን የሁዋላም የፊትም መብራት አጠፋፍቼ ስወርድ•••
"እንዴ ኧረ በፈጠረህ?" አለች ጭራሽ ከተቀመጠችበት ወደጥግ ተጠግታ እየተቁለጨለጨች
"የፈጠረኝማ ሰርተህ ብላ ነው ያለኝ ፣ለስራ አደል እንዴ የወጣሁት!•••? ቀልድ የለም! ቀጥታ ፖሊስ ጣብያ፣ ዘቅዝቀህ ብታራግፈኝ ትላለች እንዴ ቀላል አራግፍሻለሁ፣ ገንዘብማ ይዘሻል፣ ባይኖርሽማ እዚህ ደርሰሽ የለኝም እንደምትይኝ ስለምታውቂ አትከራከሪም ነበር። ቆይ ስታይኝ ሞኝ እመስልሻለሁ•••? ምንም ገንዘብ የለለው ሰው ቀንስልኝ ብሎ ይከራከራል•••? በለው በለው ቆይ እናንተ ሴቶች በሌላ በስንተ መንገድ የምታራቁቱን አነሰና ጭራሽ ተሳፍራችሁ አልከፍልም ማለትን ሙድ አደረጋችሁት እንዴ•••? ቆይ ማነው አደራጅቶ የለቀቃችሁ•••? ነው ወይስ ወንድ ልጅ ሴት ልጅ ላይ አይጨክንም ብላችሁ ስለምታስቡ ነው እንዲህ እየተፈራረቃችሁ ጢባጥቤ የምትጫወቱብን•••?" አልኳት ፊቴን ከስክሼ የባጇጁን የኋላ በር ከፍቼ እየገባሁ።
"እእእ•••• እነማን•••? " አለች። ግራ ገብቷታል። ድምጿም ሳስቷል።
"አንቺ !•••እነሱ•••ሁላችሁም ። ያው አንድ ናቹሁ።
በተለይ ቆንጆ ነሽ፣ ታምሪያለሽ፣ የሚል ወንድ በዙርያችሁ ሲበዛ •••የፈለጋችሁትን ብታደርጉን ፣ ስጋችንን ግጣችሁ ባጥንታችን ብታስኬዱን ፣ የሚናገር አፍ የሚሰነዝር እጅ ቢያንስ ሮጦ እሚያመልጥ እግር የለለን ነው አደል የሚመስላችሁ•••ንገሪኝ አንቺም እንደዛ ነው አደል የምታስቢው•••?"
"እባክህ ይሄ እኮ ጓደኞቼን አምኜ ምንም ሳልይዝ ስለወጣሁና እኔ ያላሰብኩት ሙድ ውስጥ ሲገቡና ከማላውቀው ሰው ጋር ምንም ማድረግም ፣ ምንም ነገር ውስጥ መግባትም ስለማልፈልግ ከነሱ ስለይ የተፈጠረ አጋጣሚ እንጂ እኔ ሆን ብዬ ያደረኩት ነገር አደለም፣ ግቢ ስደርስ ቆይ ከክፍሌ ይዤልህ ልምጣ ብዬ ልሸውድህም አልፈልግም፣ በቃ የለኝም !። ለምንድን ነው ከሌሎቹ ጋር አንድ ላይ የምትወቅሰኝ•••? በቃ ይቅርታ!"
"የምን ይቅርታ! ይቅርታ እራት ይሆናል እንዴ•••? ቆይ ይቅርታ ነዳጅ ይሞላል•••? አሁን ይቅርታውን ተይውና እንዴት አድርጌ ዘቅዝቄ እንደማራግፍሽ ብቻ ንገሪኝ ግን ባትነግሪኝም ችግር የለውም ፣ፍላጎትሽን ለማወቅ እንጂ ምን እንደማደርግ አልጠፋኝም!"
" ምኑን •••? የምን ፍላጎት•••? እኔኮ ተጫወቺ ምናምን ስትል እና ወሬ ስንጀምር በቃ ብዙ ሳናወራና ሳንቀራረብ ልንገርህ ብዬ ነው። ዘቅዝቀህ ብታራግፈኝ ያልኩትም ያው እንድታምነኝ ያህል ነው እንጂ •••"
"ካካካካ ነው እንዴ••••? አቦ መች ገባኝ እኔ ካወራን ሂሰብ አልከፍልም ማለትሽ ነው ለካ ••••? አሁን ገባኝ ፣እኔ ለወሬ እንደምታስከፍይ መች አወቅኩኝና ፣ በቃ ዩንቨርስቲ ደርሰሽ እስክትወርጂ ምንም አታውሪኝ፣ እንደዛው መጀመሪያ ላይ ዝም ብለሽ እንደነበረው ዝም በይ፣ እኔም ተጫወቺ ምናምን እያልኩ አላስቸግርሽም፣ጭራሽ ትንፍሽ አልልም ፣ይቅርብኝ ፣ ብቻ ሂሰቤን ስጪኝ፣ ሁለት መቶ ብር ነበር አደል ያልኩት•••? ሀምሳውን ትቼልሻለሁ መቶ ሀምሳ ብሩን ክፈይና እንሂድ" ብዬ እጄን ስዘረጋላት•••
"በማዬ ሞት ! አለመንከኝም እንዴ ቆይ አንተ ግን የድሬ ልጅ ነህ አደል•••?"
"እና ብሆንስ•••! የድሬ ልጅ ፍቅር እንጂ፣ አሽከር ነው ያለሽ ማነው•••? ገና ለገና የድሬ ልጅ ነው ጣጣ የለውም ብለሽ ነው እንዴ ? በውድቅት ለሊት ጣጣ ውስጥ የከተትሽኝ?"
"የምን ጣጣ?"
"አቦ አለመክፈልሽ ሳያንስ የጥያቄሽ ብዛት፣ አላመንከኝም እንዴ? ትላለች እንዴ አዋ አላማንኩሽም ! ዘቅዝቄ ሳላራግፍሽማ መቼም አላምንሽም ! ዛሬ አንላቀቅም!" እያልኳት ወደ ጋቢና ገብቼ፣ ባጃጇን አስነስቼ ፣ በፍጥነት እሷ መሄድ ወደምትፈልግበት ሳይሆን ወደመጣንበት አቅጣጫ አዙሬ መብረር ስጀምር ክፉኛ ደነገጠች።
ከጀርባዬ በሁለቱም እጆቿ ትከሻዬ አከባቢ ያዝ አድርጋ ወደ ጆሬዬ በመጠጋት ፊት ለፊት እየተመለከተች•••
" ኧረ በጌታ ወዴት ነው የምትወስደኝ•••?"
"አንቺን ዘቅዝቄ ወደ ማራግፍበት ምቹ ቦታ!"
"ኧረ በናትህ ቆይ አንተ ግን እህት የለህም••••?"
"እህትማ አለኝ! ሊያውም በጣም የምወዳት! አንዲት ብቸኛ እህት አለችኝ፣ ይህንን ባጃጅ የገዛችልኝም እሷ ነች። ነገር ግን ሰርተህ ዋጋውን መልስ ከዛ ባጃጁን ትወስደዋለህ ነው እንጂ ሴት በነፃ አመላልስበት አላለችኝም ገባሽ!"
"እሺ የማታደርሰኝ ከሆነ በቃ አውርደኝ ያለበለዝያ ልጮህ ነው !!!!••••!"አለች እንባ እንባ በሚል ድምፅ። ታደርገዋለች ። በእርግጠኝነት ከዛ በላይ ባስጨንቃት ትጮኽ ነበር ። ሳቄን መቆጣጠር አልቻልኩም።
"ካካካካካካካ••••" ባጃጇን ጥግ አስይዤ ትንሽ ሳቅኩባት። ከባጃጁ ውስጥ ወረደች። ግን አልሄደችኝ ግራ በተጋባ ስሜት ቆማ ስታየኝ አሳዘነችኝ።
"ተማሪዋ ! ለምን ወረድሽ •••? ካካካካ በግርሽ ልትሄጂ ወሰንሽ በቃ••• ?" አልኳት። መልስ አልሰጠችኝም።
"ሰአትሽን አይተሽዋል ሰባት ሰአት ሊሆን ነው ? ነይ ግቢ እነዛ እዛ ጋር የቆሙት ሰዎች ታክሲ ፈልገው ነው ፣እንጠይቃቸውና ባንቺ መስመር ከሆኑ ይዘናቸው እንሄዳለን፣ ነይ አንቺ እዚህ እኔ ጋር ጋቢና ሆኚ!" አልኳት። አላመነችኝም። ፈራች።
" ነይ ግቢ አቦ ደሞ ባንቺም ብሶ እንድለማማጥሽ ትፈልጊያለሽ እንዴ?" ስላት ገባች። ሰዎቹ ጋር ደርሰን ስንጠይቃቸው እሷ ወደምትሄድበት ሳይሆን ሌላ መስመር ናቸው።
" ክፍያው ዘጭ ነው! እንሸቅላ በቃ ! አንዴ ጣል አድርገናቸው እንመለስ•••?" ስላት••• "
"ወይኔ ጉዴ መሽቷል እኮ!"
"ካካካካካ•••• ኧረ ባክሽ መሽቷል ትላለች እንዴ! የመሸውማ ገና እኔን ሳታገኝኝ ነው። አሁን ሊነጋኮ ነው፣ ደሞ ቢመሽስ ግቢያችሁ እንደሆነ አጥር የለው ፣ አደርስሽለሁ !" አልኳትና " ግቡ እንሂድ" አልኳቸው እነሱንም ። ገቡ፣ ጉዞ እንደጀመርን የባጇጇን ፍጥነት ስጨምር እኔ ላይ ልጥፍ አለች። ከጀርባ ወገቤ ላይ ልብሴን ጨምድዳ ይዛኛለች።
" ልቀቂኝ ባክሽ ! ሂሳብ ሳትከፍይ ደሞ የድሃ ልብሴን ልቀጂ ነው እንዴ•••?"
"ካካካካካ! ኧረ ምን ይሻለኛል!"
"ምንም አይሻልሽም መክፈል ብቻ ቆይ የየት አገር ልጅ ነሽ?"
"የ አዲስ አበባ"
"እህህህም አጅሪት ከቀለጠው መንደር መጥተሽ ነዋ ይህንን የድሬዳዋ ሙቀጥ ልቡን ያሳሳውን ልጅ በውበቴ አቅልጬው ሳልከፍል እብስ እላለሁ ብለሽ ምንም ብር ሳትይዢ ዋጋ ተከራክረሽ የገባሽው! እኔ ግርም ያለኝ አለመክፈልሽን እያወቅሽው ዋጋ መከራከርሽ"
"ኪኪኪ ኧረ ተወኝ በፈጠረህ! በብዙ ብር ከተስማማሁ ያው አልከፍልም ስልህ ብዙ ትናደዳለህ ብዬ ነዋ "
"ካካካካካካካ አቦ ይመችሽ ! አይ የገባሽ ነሽ ግን ባጃጁን ሳዞረው የምሬን መስሏት እርርይ ብላ ጉድ እንዳታደርገኝ ብዬ ፈርቼ ነበር የምር!" አልኳት።
እኔ ሳወራ መልስ ከመስጠት ይልቅ መሳቅ ይቀናታል።ሳቋ ደሞ ዜማ አለው የዘመኑን ዘፈን ከመስማት የሷ ሳቅ በስንት ጣእሙ።
ሰዎቹን አድርሰን ስንመለስ •••" በጣም ርቦኛል ነይ እራት እንብላና ሸኝሻለሁ !" አልኳት ትንሽ አቅማማች። ጫን ስላት ተስማማች ።አንድ ብዙ ግዜ ምግብ የምበላበት ሆቴል ይዣት ገባሁ...
ከ 200 ላይክ በኋላ ክፍል 3 ይለቀቃል🌹