♥️ ተማሪዋ ♥️
...ክፍል 3...
Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው
አዘጋጅ እና አቅራቢ=- ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል ✍
መጣሁ ሽንቴን ልሽና ያው በዚህ ሰአት ጥብስ ነው የሚኖራቸው ሁለት ጥብስ እዘዥ" ብያት እሷ ወንበር ይዛ ቁጭ ስትል እኔ ወደወስጥ ገባሁ።
በልተን ልንጨርስ አከባቢ •••
" ስሚ እንጂ ተማሪዋ!"
"እንዴ ኪኪኪኪ ተማሪዋ ብለህ ከምጠራኝ ስሜን መጠየቅ አይቀልም!"
"እኔ አንቺ ጋር ያለኝን ብር እንጂ ስምሽ ምን ያደርግልኛል•••?"
"ኪኪኪኪ እንዴ አሁንም እዛው ላይ ነህ•••? የተውከው መስሎኝ ነበርኮ!"
"የተውኩት መሰለሽ አደል ደፋር ነሽ አቦ እውነቱን ልንገርሽ የተውኩት እየመሰልኩ ነው እንጂ በጭራሽ አልተውኩትም !"
"ምን ማለት ነው••• ?"
"ምን ማለት እንደሆነ ቀስ ብሎ ቢገባሽ ይሻላል ብዬኮነው ንገረኝ ካልሽ ልንገርሻ በቃ•••እኔ ሰው በምክር ሳይሆን በተግባር ማስተማር ነው የሚመቸኝ። እዚህ ያመጣሁሽም ምግቡን አንቺ እንድታዢ ያደረኩትም ሆን ብዬ ነው። አንቺ አዘዝሽ ማለት ከፋይ አንቺ ነሽ ማለት ነው።ለሰጠሁሽ የትራንስፖርት አገልግሎት በጥሬው ባትከፍይኝም በተዘዋዋሪ መንገድ በጥብስ ሂሳቤን አግኝቸዋለሁ።
በቃ እኔ እንዲህ ነኝ፣ ሰው ሲሸውደኝ ደስ አይለኝም። ሂሳቤን እንድትከፍይኝ ካንቺ ጋር ብጣላ ምን አተርፋለሁ ፣ከዛ ይልቅ ጭንቅላቴን ተጠቅሜ መላ ማፍለቅና እንደትከፍይኝ ማድረግ ነበረብኝ። እስቲ እኔ ጋር የለኝም አልከፍልም ያልሽውን ሂሳብ እዚህም እንደምትደግሚው አያለሁ። ያው ባይኖርሽም አንድ ሁለት ቀን እቃ ቢያሳጥቡሽ ነው ቻይው!"
"ካካካካካካ ኧረ በጌታ ሰዎቹ ወደኛ እያዩ ነው አታስቀኝ!"
"ይዩሽ ችግር የለውም በኋላ ስታለቅሺ ያዋጡልሻል፣ ባጭሩ ይህን የበላነውን ሁለት ጥብስ ከፋይዋ አንቺ ነሽ እኔ የምከፍለው አምስት ሳንቲም የለኝም!
"እህት ሂሳብ!" አለቻት። ዘወር ብዬ ሳያት ግራ ገብቷት አንዴ እኔን አንዴ አስተናጋጇን ትመለከታለች። ባጃጄ ውስጥ ገብቼ በማስነሳት ቁልቁል ስፈተለክ ባስተናጋጇ ክንዷን ተይዛ እንደቆመች ማመን አቅቷት አራት ጣቶቿን አፏ ላይ ጭና ትመለከተኝ ነበር••••
****
ብዙ መራቅ አልቻልኩም። ምን ያህል እንደምትጨነቅ ሳስበው አላስችልህ አለኝ። ከአይኗ እስክሰወር ትንሽ ሄደት ብዬ ዞሬ መመለስ ጀመርኩ፣ ተማሪዋ ሳታየኝ አስተናጋጇ ገና ከሩቁ እየተመለስኩ እንደሆነ አየት አደረገችና አፍና ያቆየችውን ሳቋን ለቀቀችው።
ተማሪዋ አስተናጓጇ ምን እንደሚያስቃት ግራ ገብቷት አይን አይኗን ከማየት ውጪ አጠገባቸው እስከምደርስ መመለሴን አላስተዋለችም። አምስት እርምጃ ያህል እስኪቀረኝ ድረስ ተጠግቼ ከጀርባዋ እንደቆምኩ ዘወር ብላ አየችኝና ••••
"በጣም ትገርማለህ እሺ ! ስታናድድ ደሞ ትስቃለህ እንዴ አናዳጅ !" አለችኝ ። ከተጨነቀው ፊቷ የከፋው ፈገግታ ፈገግ ብላ።
አስተናጋጇ ••••• "አስደነገጥኩሽ አደል የኔ ቆንጆ ! ኡፍፍፍ ኤፊ ግን ነብስህ አይማርም ! ስትርበተበት ቀላል አሳዘነችኝንዴ! ይቅርታ እሺ ማሬ የኔ ሳይሆን የሱ ተንኮል ነው ኪኪኪኪኪ በሉ እንኩ መልሳችሁን ገና ሳትበሉ እኮ ነው የከፈለው ኪኪኪኪ•••" እያለች ብሩን ፊቷ ሳይፈታ በንዴትም በጭንቀትም ቅጭም እንዳደረገችው በክፉ አይን ለምታያት ለተማሪዋ ሰጠቻትና እየሳቀች ወደ ውስጥ ገባች።
ተማሪዋ ካስተናጋጇ የተቀበለችውን መልስ ይዛ ወደኔ ተጠጋችና ታፋዬ ላይ ወርውራልኝ••••" ማሚ ትሙት እንደዛሬ ደንግጬ አላውቅም•••• አንተ ግን ምን አይነት ልጅ ነህ በጌታ••••? ክፉ ነህ እሺ!" አለችኝ።። ከመሳቅ ውጪ መልስ ልሰጣት አልቻልኩም።
"አናታም !" ብላኝ ቀስ እያለሽ ወደላይ መሄድ ጀመረች። ነፃነት እና ድፍረቷ ደስ ይላል። ክላክስ እያደረኩ ተከተልኳት። ዘወር ብላ አላየችኝም። የእግረኛ መንገድ ላይ ስለሆነች ባጃጇን ጥግ አስይዤ አቆምኩና በግሬ ተከተልኳት አጠገባ እንደደረስኩ•••
"ካሁን በኋላ አታውቀኝም አላውቅህም እሺ እንዳታናግረኝ!" አለችኝ። ክንዷን ያዝ ሳደርጋት ••••"ልቀቀኝ!" አለች ቆም ብላ።
"አለቅሽም !"አልኩ። ዝም አለች። ዝም ብዬ አየኋት እሷም አየችኝ ። ቃላት የማይገልፁት ልዩ ውበት ፣ ፈጣሪ የባረከሽ የቆንጆዋች መፍለቂያ የሆንሽው አገሬ ዘርሽ ብዝት ይበል አልኩ በልቤ። ዝም ብዬ ሳያት ዝም ብላ ታየኛለች።
"ስምሽ ማነው••••?" አልኳት።
"ሂድ ወደዛ! ጣጣህን ጨርሰህ ፣ የልብህን አድርሰህ ስታበቃ ነው እንዴ ስሜ ትዝ የሚልህ አልነግርህም!" በማለት እጇን አስለቅቃኝ ለመሄድ ስትሞክር ጠበቅ አድርጌ ያዝኳት።ቀና ብላ አየችኝ አይኗ ውስጥ በጥልቀት ተመለከትኳት ። አቀረቀረች። ከፍቷታል።
"ሀይ አቦ በቃ ትንሽ ላስጨንቅሽ ብዬ እንጂ ይሄን ያህል ይከፋሻል ብዬ መች ገመትኩ እና በዚህ ምክንያት ልታኮርፊኝ ነው?" ስላት እንደዛው እንደከፋት ቀና ብላ•••
"ደሞ የልጅቷ ይባስ ! ሁኔታዋ በጣም ነበር የሚያስጨንቀው ስትገርም ግን ! ቀልድ መሆኑን እያወቀች እንደዛ ምንጭቅጭቅ ስታደርገኝ ትንሽ እንኳን አይከብዳትም እንዴ? ደሞ ቀልድ ነው ምናምን እያለች ትገለፍጣለች ግልፍጥ ነገር ነች ! ድዳም !"አለች።በጣም እንደደበራት ይበልጥ ተገለጠልኝ።
"ኦኦኦኦ ይህን ያህል ተናደሻል እንዴ ተማሪዋ ! በእውነት በጣም ይቅርታ የማይሆን ቀልድ ነው ማለት ነው የቀለድኩት፣ ቶሎ የተመለስሉት እኮ ግን ብዙ እንዳትጨናነቂ በማስብ ነበር "
"ትንሽ ብትቆይ እማ ልጅቷ በቁሜ ልብሴን ከላዬ ላይ ከመግፈፍ የምትመለስም አይመስለኝ ፣ እንደዚህ አይነት ቀልድ አለ እንዴ •••? ሲጀመረ አንተ ብትቀልድ እንኳን እንዴት ከማላቃት ልጅ ጋር ታላትመኛልህ ?"
"አቦ አታካብጅዋ ይህን ያህል ቆይ ምን ብላሽ ነው•••?*
"ያለችው ምን ያደርግሀል•••? ልጅቷ ግን በጣም ችግር አለባት ! አላውቃት አታውቀኝ ፣ ቀልድ መሆኑን እያወቀች እንደዛ መንጣጣቷ ይገርማል! ነገሩ ተወው እኔ ሴት አይሆንልኝም ፣ እንኳን እሷ የኔ የቅርቤ ጋደኛዬ እህቴ የምላቸው ሴቶች እንኳን አንደበታቸውን እንጂ ልባቸውን ከፍተውልኝ አያውቁም !ለምን እንደሆነ እንጃ ብቻ ሴት አይወጣልኝም!"
አለች እንባ እምባ እያላት። በቀለድኩት አጉል ቀልድ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ። ተፀፀትኩ።
"በናትሽ በቃ እርሽው እኔ ነኝ ጥፋተኛው ማንም አይደለም!" አልኳት ዝም አለችኝ። ትግስቴ አለቀ።
"አቦ ተይና አንቺ ደሞ እኔም እኮ ቅድም እዛ ድረስ ወስጄሽ የምከፍለው የለኝም ስትይኝ ከዚህ በላይ ደንግጬ የለ እንዴ? በቃ ይቅርታ !" በማለት ትንሿን ጣቴን ወደሷ ቀሰርኩና" እንታረቅ!" አልኳት። ያንን ፍልቅልቅ ሳቋን አፍለቀለቀችው። እሳን ለማሳቅ ያደረኩት ሙከራ ተሳካ። ከዛ አስቀያሚ ስሜት በመውጣቷ ደስ አለኝ።
"አቦ እንደዚህ ስስቂ ብቻ ነው የሚያምርብሽ ሁለተኛ እንዳታኮርፊ እሺ! እዚሁ ጠብቂኝ ባጇጇን ይዜ ያበደ ጭፈራ ቤት ወስጄ ደስ ያለሽን እጋብዝሻለሁ፣ ስንቀውጠው ነው የምናድረው!"
"እንዴ አብደሀል እንዴ እራት በልተን እሸኝሻለሁ አላልክም?"
ይቀጥላል....
ከ 200 ላይክ በኋላ ክፍል 3 ይለቀቃል🌹