♥️ ተማሪዋ ♥️
🌹...ክፍል 5...🌹
እንደገባን ከእቅፌ ውስጥ አፈትልካ ወጣችና ከአልጋው እራስጌ በስተግራ ባለ ወንበር ላይ ቁጭ አለች።
"እንዴ እዚህም ገብተሽ ቁጭ አይንሽ እኮ በእንቅልፍ ማጣት ደክሟል አተኝም እንዴ ተማሪዋ•••?
" ተማሪዋ አትበለኝ አትሰማም•••?" "ትትክክለኛ ስምሽን እስክትነግሪኝ አማራጭ የለኝም!" "ሰላም አልኩህ እኮ!"
"የስንቱን ሰላም በውበቷ የምትረብሽ ልጅ ሰላም ልትሆን አትችልም ! ውስጤ ነግሮኛል ፣ስምሽ ሰላም እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ!" "ትገርማለህ ግን ! ••ይሄው ስሜ!••• የዋሸሁክ መስሎህ ነው አደል•••? አለችና ከሞባይሏ ላይ ከቨሩን አንስታ በሞባይሏ ጀርባ ላይ ያስቀመጠቻትን የድሬ ዳዋ ዩንቨርስቲ ተማሪ መሆኗን የምትገልፅ መታወቂያዋን አንስታ ሰጠችኝ። " ካካካካካ እሄው እንደዋሸሽኝ መች አጣሁት •••ቃል ! ነው ስምሽ! ቃልኪዳን ሰመረ ! ካሁን በኋላ ተማሪዋ መባልሽ ይቆማል!•••••እና አሁን ከወንበሩ ላይ ተነስተሽ አተኝም ቃል!" አልኳት። ትከሻዋን ወደ ላይ ሰብቃ አልተኛም አለችኝ።
ነፃ ሆና ማውለቅ ያለባትን አውልቃ እንድትተኛ ብዬ ወደ መታጠቢያ ክፍሉ ገባሁላት። ከደቂቃዎች ቆይታ በኋላ ስመለስ ጭራሽ ጫማዋን አውልቃ እግሯን ወንበሩ ላይ ሰቅላ ተቀምጣለች።
ጉድ ፈላ እዚሁ ወንበሩ ላይ ነው የማድረው ልትለኝ ነው እንዴ•••? እያልኩ በሆዴ ጠጋ አልኩና•••" ቃልዬ አተኝም እንዴ•••?" አልኳት።"ቁጭ በል!" አለችኝ••• አልጋውን በአገጯ እያመላከተችኝ። ቁጭ አልኩ። ተፋጠጥን። የሆነ የሆነ ሰአት የምታየኝ አስተያየት ልቤን ስልብ ሲያደርገው ይታወቀኛል። ያ አስተያየት አልፎ አልፎ የሚመጣ መሆኑ በጀኝ እንጂ ዘለግ ላለ ደቂቃ እንደዛ ብታየኝ የልቤን ትርታ ታቆመው ነበር። "እእእ ••••እእእእ•••" እያለች ልትናገር ያሰበችውን አፏ ላይ አድርሳ መልሳ ትውጠው ይመስል ለመናገር ስታምጥ ቆየችና•••
"እእእእ እኔ በጣም የምታዘበው ባስ ሲልም የምጠላው ምን አይነት ባህሪ ያለው ወንድ እንደሆነ ታውቃለህ ኤፊ•••?" ስትለኝ ••••" አዎ አውቃለሁ ! በደንብ ነዋ የማውቀው!" አልኳት።
"ምን •••? እንዴት ልታውቅ ትችላለህ•••? አታውቅም!" አለችኝ ።
"አውቃለሁ ባክሽ •••አንቺ የምትጠይው ወንድ እንደኔ ገና ለገና መቶ ሀምሳ ብር ሂሳብ አልከፈልሽም ብሎ መቶ ሀምሳ ዘፈን ካልዘፈንኩብሽ ፣ የሀረርጌን ሸጎግን አትጥይኝ ባህርይ በፍፁም እንደዛ አይደለም። እውነቱን ለምናዘዝ እኔ ገና መጀመሪያ ላይ ቆመሽ እንዳየሁሽ ነው ደስ ያልሽኝ ••••" ብዬ ልቀጥል ስል በሳቅ አቃረጠችኝ ••••"ኪኪኪኪኪ ደስ ያልኩህ አደል በቃ ከዛ አያልፍም ኪኪኪ"
"አስጨርሽኛ ቆይ እና ባንዴ እንዳየሁሽ ነው ያፈቀርኩሽ ብልሽ ያንን ማለት ይቻል ይሆናል እኔ ግን በቃ እንድታምኝኝ ስለምፈልግ እውነቱን ነው የምነግርሽ ደስ አልሽኝ ወይም ወደድኩሽ በቃ በቃ ምንድነው ለማንኛውም መሄድ ጀምረን ግማሽ መንገድ ላይ ሂሳብ የለኝም ስትይኝ አንቺ እንደምታስቢው ወይም እኔ እዛ ጋር እንዳስመሰልኩት አልተናደድኩብሽም እንደውም አንቺን የምግባባበት አጋጣሚ ስለተፈጠረልኝ በጣም ነበር ደስ ያለኝ።
ባጭሩ እንደዛ ያካበድኩት እንደዚህ አሁን እንደተግባባነው እንድንግባባእንድንቀራረብ ነው። ብር የለኝም ስትይኝ ችግር የለውም ሲኖርሽ ትከፍያለሽ ብዬ ባደርስሽ እኔ እንኳን ባልረሳሽ አንቺ ሲነጋ ትረሽኛለሽ!"
"ገብቶኛል ኤፊ!••• አቋረጥከኝ እንጂ እኔም ጨቅጫቃ ወንድ ምናምን ልልህ አልነበረም። ይህን ሁሉ ከምትናገር እኔን ብታስጨርሰኝ ምን ነበረበት•••?"
"የቱጋ •••? እዛው ወንበሩ ላይ•••? "ስላት ••••"የምን ወንበር •••?" አለች ግር እያላት።
"የማስጨርስሽ ነዋ! ወንበር ላይ ነው እንዴ የሚመችሽ እኔ መች ገባኝ ••! አልገባኝም ነበር እኮ እያልኩ ከላይ የለበስኩትን ቲሸርት ሳወልቅ" "ካካካካካካካካ ••••ሂድ ወደዛ ! ሞዛዛ !! ሞዛዛ ነገር ነህ እሺ እንዴ ኪኪኪኪኪ ደሞ ፍጥነትህ ትገርማለህ እሺ! ፣ እኔ ወሬዬን እስክጨርስ ብትጠብቀኝ ምናለበት ነው ያልኩት ፣ ዝም ብልህ ነገር አታጣምም!"
"ግንኮ ከለሊቱ አስር ሰአት ሆኗል፣ በዚህ ሰአት ወሬ አይከብድም •••? ነገ ብናወራስ•••? አሁን እንተኛ ባክሽ ነገ እናወራለን !" "አአአ•••አሁን ከመተኛታችን በፊት ነዋ ማውራት ያለብን ኤፊ!"
"እህህ••••ገባኝ! አሁን እናውራ ፣ በቃ እናወራለና ምን ችግር አለው •••• እሺ ምንድን ነው•••?""እእእ••••እኔ የሚጫነኝ ወንድ አልወድም ኤፍ ••ማ•••ማ ማለት•••" "አቦ ተይው አታስረጂኝ በቃ ይበቃል! ፣ ይህን ምን ማብራራት ያስፈልገዋል! እንደገባኝ ያው የሚጫንሽን ወንድ ሳይሆን መጫኑን ነው የምትጠይው መፍትሄው ከላይ መሆን ነው አንቺ ከላይ ከሆንሽ ወዴት ይጫንሻል•••?"
"ኧረ በፈጠረህ••••! ላለማውራት ሆን ብልህ ነው አደል ነገር የምታምታታው አውርቼ እስክገላገለው ብጠብቀኝ ምናለበት•••?" ስትለኝ እስክገላገለው የሚለው ቃል ሰቀጠጠኝ። ምን ልታወራኝ ነው ይቺ ልጅ ••• አውርቼ እስክገላገለው ስትል ምን ማለት ነው•••? እያልኩ •••
"እሺ ምንድን ነው ንገሪኝ!" አልኳት።
"ኤፊ በቃ እኔ በጣም የሚያናድደኝ ወንድ የኔን መጥፎ አጋጣሚ ከፍላጎቴ ውጪ በሆነ መልኩ ለመጠቀም የሚፈልግ ወንድ ነው ! " ስትለኝ ምን አስባ እንደሆነ ገባኝ። ለምን እንደሆነ አላውም ውስጤ የንዴት እሳት ሲጫር ተሰማኝ። ብልጭ አለብኝ።
ወድያው ስሜታዊ ሆኜ ክፉ ነገር ልናገራት አልፈለኩም። ምክንያቱም ወድጃታለሁ። ግኑኝነታችን እንዲቀጥል እፈልጋለሁ ። ወደፊት የሚሰማኝን እና የሚሆነውን ባላውቅም አሁን ላይ ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገ ከነገወድያም ላገኛት እንደምፈልግ ነው የሚሰማኝ።ባዶው ወለል ላይ አፍጥጬ ዝም አልኩ። "ልልህ የፈለኩት ገብቶሀል አደል ኤፊዬ•••?"ገብቶኛ ቃል! •••በደምብ ገብቶኛል •••በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉም ግንኙነቶች በአጋጣሚ በተፈጠረ ቅፅበት የሚጀምሩ ናቸው !። ያ አጋጣሚ ደግሞ ጥሩም መጥፎም አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ አጋጣሚውን ተጠቅሞ መተዋወቅ ፣ መቀራረብና መግባባት አንዱ የህይወት ገፅታ ነው። ያ በራሱ ምንም ክፋት የለውም። የተቸገርሽበትን ወይም ጥሩ አጋጣሚ ላይ ያልሆንሽበትን ግዜ ተጠቅመው ችግርሽን ለመፍታት አልያም ከዛ መጥፎ አጋጣሚ ለመውጣት ያለሽ ብቸኛ አማራጭ እነሱ መሆናቸውን ሲያውቁ ያንን ክስተት አንቺን ያለፍላጎትሽ ያሻቸውን ለማድረግ የሚጠቀሙበት ወንዶች የሉም ብዬ አልልም። በሌላ መልኩ ሰው ስለሆንሽ ብቻ ካንቺ ምንም ሳይፈልጉ አንቺን በመርዳታቸው ብቻ ደስ የሚላቸው ወንዶችም ብዙ ናቸው። ሁሌም ረጂ ወንዶች ተረጂ ሴቶች ናቸው ብሎ ማሰብም ትልቅ ስህተት ነው ። ያው እንደየሁኔታው ይቀያየራል። እኔ ግን ቃል ኪዳንን ወይም አንቺን በመጥፎ አጋጣሚ የተዋወኩሽ መስሎ አልተሰማኝም ነበር። እኔና አንቺ የተዋወቅነው በመጥፎ አጋጣሚ ነው ብዬ በጭራሽ አላሰብኩም ነበር።
በርግጥ እኔ ሳላገኝሽ በፊት እዛ ብርድ ላይ በምን ምክንያት እንደቆምሽ በዝርዝር አላወራንም ። ንገሪኝ ብዬያልወተወትኩሽም አንቺን ማጨናነቅ ስላልፈለኩ ነው። ግቢ ያላደረስኩሽም በግድ ተጭኜሽ ነው ብዬ አላስብም። በቃ ደስ ስላልሽኝ ፍቃድሽ ከሆነ አብረሽኝ እንድትዝናኚ ስለፈለኩ ነው ያስቀረሁሽ