♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
.
.
🌹...ክፍል 11...🌹
.
.
Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው!
ነፍሷን ይማረው እና እማዬ•••••" ኪኪኪኪ ኤፊዬ ቅናተኛ ነው። ልጅ እያለም መሽቶ በተኛን ቁጥር አባቱን ተነስ ከማዬ አጠገብ! •••• እማ ከኔ ጋር ብቻ ነው የምትተኛው! ••• ውረድ ካልጋው ላይ እያለ ይጎትተው ነበር!" እያለች ብዙ ግዜ ታወራ ነበር ።
"አቦ ተያ እማዬ ደሞ!" አላለሁ እቤት ውስጥ ያለውን እንግዳ፣ ታላቅ እህቴን እና አባዬን በፈረቃ እየተመለከትኩ።
ኤፍዬ ሙት እውነቴን እኮ ነው ኪኪኪኪኪ ለብዙ ግዜ አባትህ አንተ ካልተኛህ በቀር አጥገቤ ድርሽ አይልም ነበር ኪኪኪኪ ይህ የሁሉም ልጅ ባህሪ እኮ ነው ኤፍዬ ያንተ ግን ጫን ያለ ነበር ትልቅ ሆነህም ላንተ ሳይገዛ ለህትህ ልብስም ጫማም ከተገዛ መች ታስደርጋታለህ አይ ኤፍሬሜ !" ትላለች።
አንድ እህት ነው ያለኝ። በሰባት አመት ትበልጠኛለች። እማ ልክ ነች እቀናለሁ ቃልዬ ለምን ታስቀናኛለች ••••? ለምንድን ነው ሁሉንም የሚደወሉላትን ስልኮች አጠገቤ እያናገረች ከሁሉም በተለየ ሁኔታ እኔ አጠገብ ሆና የማታወራው አንድ ስልክ የኖራት•••። የደዋዩን ስም አይቼዋለሁ። ዛኪ ብላ ነው የመዘገበችው።
ዛኪ በሚል ስም የሚደወልላትን ስልክ አንድም ቀን አጠገቤ ሆና አናግራ አታውቅም። አጠገቤ ሆና አለማናገሯ ብቻ አይደለም ያንን ስልክ ካወራች በኋላ እንደምትቀየረም አስተውያለሁ። እየሳቀች የነበረችው ልጅ ያንን ስልክ
አናግራ ስትመለስ ሳቋ ብቻ ሳይሆን መረጋጋቷም ጠፍቶ ድውክውክ ትላለች። ምነው ስላት መልሷ ምንም••• ምን ሆንኩ? ነው። ምን ሆንሽ እንደምላት ግራ ይገባኝና ዝም እላለሁ። መጀመሪያ የመሄድ ሀሰብ ያልነበራት ልጅ አብረን ልናመሽ ከተነጋገርን በኋላ ያ ዛኪ የተባለ ሰው ከደወለ በቅፅበት ውስጥ ልሂድ በቃ ኤፍዬ ብላ ለመሄድ የምትነሳው ነገር ደግሞ ይበልጥ ያናድደኛል።ቢሆንም ቃልዬን አፈቅራታለሁ።
ቀኑ እሁድ ነው። የተኛሁበት ክፍል ገና በጥዋት ሲንኳኳ ነበር እህቴ እንደሆነች ያወቅኩት። በባጃጅ ስራው በየሳምንቱ የሚጣል እቁብ አለ። ከቃልዬ ጋር ከመተዋወቃችን በፊት አንድ ቀንም አጉድዬ አላውቅም እንደውም ከሚፈለገው በላይ አጠራቅሜ በየሳምንቱ ቅዳሜ ማታ ወስጄ ለህቴ እሰጣታለሁ ። ወላጆቻችን በሂወት ስለለሉ ከህቴ ጋር ነበር የምኖረው ይህን ስራ ስጀምር ነው አንድ ክፍል እዛው ሰፈር ውስጥ ተከራይተን ከጋደኛዬ ጋር አብረን መኖር የጀመርነው። አስራ ሁለተኛ ክፍል ተፈትኜ ውጤቴ ዩንቨርስቲ ለመግባት ባያስችለኝም በማታው መርሀ ግብር እዛው ድሬ ዩንቨርስቲ ከፍዬ ላስተምርህ ስትለኝ አልፈልግም ባጃጅ ግዢልኝ ብዬ ነው ያስገዛኋት።
ቅዳሜ ማታ ከኔ ብሩን ትቀበል እና እሁድ ጥዋት ወስዳ ትጥላለች። ትናንትና ፣ ቅዳሜ ማታ ግን አልሄድኩም ብሩንም አልሰጠኋትም። ትናንት ብቻ አይደለም ለተከታታይ አራት ሳምንታት የቁቡን ብር እየናድኩት ስለሚጎድል እህቴ ጋር ሳልሄድ ድምፄን አጥፍቼ ገባና ተኛለሁ። እሁድ ጥዋት ትመጣለች ።
"ስላልሞላልኝ እኮ ነው ዝም ያልኩሽ እቴትዬ!" ስላት•••
"ምነው ኤፍዬ •••? ሰሞኑን ስራ የለም•••? ነው ባጃጇ ረብሻህ ለገራዥ ወጪ አወጣህ•••?" ትለኛለች ።
"አዎ እቴትዬ " እላታለሁ። ያለውን ትቀበለኝ እና ከራሷ ሞልታ እቁቡን ትጥላለች። እውነቱ ግን ባጃጇ ምንም አለመሆኗ ገራዥም አለመግባቷ ነው። የታመምኩት እኔ ነኝ። ከህመሜ የምትፈውሰኝ መካኒኳ ደግሞ ቃልዬ ናት።
እሷን ሳገኛት አይደለም የእቁቡን ብር ባጃጇንስ ባጠፋት መች ልክ ያልሆንኩ መች ያጠፋሁ ይመስለኛል •••? ብዬ ለ እቴትዬ አልነግራት ነገር የማይባል የማይነገር ሆነብኝ።
ዛሬም በጥዋት የመጣችው ያንኑ መከረኛ የቁብ ብር ልጠይቀኝ ነው። ኪሴ ውስጥ ያለው ከሚያስፈልገው ግማሹ ነው። በሩን ደጋግማ ስታንኳኳ እንዳልሰማሁ ሆኜ ተኛሁ። ከተኛ የማይሰማው ጓደኛ እንዴት ዛሬ እንደሰማ እንጃለት ብቻ ተነስቶ ከፈተላት።
"ተኝቷል እንዴ•••? ቀስቅሰው እና የቁቡን ብር ይዞልኝ ይምጣ እሺ ኪያዬ ድስት ጥጃለሁ አሁኑኑ ቀስቅሰው!" ብላው ሄደች።
" እሺ!" ብሏት ዘወር ሲል ተነስቼ ፍራሼ ላይ ቁጭ ማለቴን ተመለከተ።
"እንዴ •••••? እየሰማህ ነው እንዴ ዝም ያልካት ኤፊ••••?"
"እንኳን እኔ አንተም ሰምተሀል እንቅልፎ! " አልኩትና ቀጠል አድርጌ " ባክህ የቁቡን ብር ረሚም አድርጌዋለሁ ለዛ ነው " አልኩት።
"አንተ ልጅ ግን ምን ጀመርክ ስራ ለጉድ እየሰራህ ነው ባጇጇ ለስከንድ ገራጅ ገብታ የማታውቀውን ገራጅ ገባች ምናምን እያልካት ነው ኧረ ይደብራል ኤፊ !"
"ዝም በል ወደዛ ! ወሬህን ተውና ይልቅ ብር ካለህ አበድረኝ ሞልቼ ልስጣት!" አልኩት ። ሰጠኝ ። ሰጠኋት።
ከቃልዬ ጋር ሰኞም ማክሰኛም ተገናኝተናል ። ዛሬም ምርጥ ቦታ ወስጄ ምሳ ልጋብዛት ተቀጣጥረናል። እየመጣች ነው ። እኔም ወደዛው እየሄድኩ ነው።
ተገናኝተን ምሳ እየበላን እኔ የባጥ የቆጡን ሳወራ እሷ እንደሁልግዜው ስትስቅ ቆየንና በመሀል ••••
"ቃልዬ !" አልኳት።
"ወዬ ኤፊ!"
"አንድ ነገር ልጠይቅሽ•••?"
"ለምን አንድ ብቻ ••••? ሁሌ አንድ አንድ እያልክ ከምጠይቀኝ ሰብሰብ አርገህ በጅምላ ብጠይቀኝ አይሻልም ኤፊዬ••••?"
"እባክሽ አትቀልጂ ቃል•••?"
"እሺ ምንድን ነው•••?"
"ምኑ•••?"
"ጥያቄህ ነዋ!"
"እ•••••ማለት •••? ቃዬ ምን መሰለሽ ••••እኔን የሚሰሙኝን ስሜቶች ማለት እኔ ስላንቺ የሚሰሙኝን ስሜቶች አንቺ ጋር በከፊል እንኳን ያሉ ይመስልሻል•••?"
"ሰው እንዴት አንድ አይነት ስሜት ይሰማዋል አንተም የራስህ እኔም የራሴ!"
"እኔማ የኔ አይደለሁም!"
"እና የማን ነህ?"
"ያንቺ!"
"ኪኪኪኪ እኮ አንተ ለኔ የሚሰማህ ስሜት እኔ ላንተ ከሚሰማኝ ስሜት ጋር አንድ መሆን አለበት•••?"
"እንዴት ምን ለማለት ፈልገሽ ነው?"
"እኔ እንጃ!"
"እሺ እሱን ተይው ቆይ ትወጂኛለሽ •••? ማለት ታፈቅሪኛለሽ•••?"
"ኪኪኪኪኪ•••••"እየፈጩ ጥሬ!" አለች አያቴ!"
"አያትሽ ደሞ ምን ነካቸው"
"ምንም!"
"እቦ ታድያ እየፈጩ እንዴት ጥሬ ይሆናል•••••? ከተፈጨ ዱቄት አይደል እንዴ የሚሆነው!"
"ኪኪኪ •••ጥሬው ያንተ ቢጤ ሆኖ ይሆናላ!"
"ቢጤ••••! ምንድን ነው ደሞ ቢጤ••••?"
"ካካካካካካካካ ኧረ በጌታ አታዝገኝ ኤፊዬ!"
"አንዴ ጥሬ አንዴ ቢጤ እያልሽ እየተሳደብሽ ያለሽው እኮ አንቺ ነሽ ቃልዬ!"
"ለምን ሰድብሃለሁ ኤፍዬ በጭራሽ አልሰደብኩህም ግን ኤፊ እኔ ካንተ ጋር ሁሌ የምገናኘው እና አብሬክ የማሳልፈው ምንህ ስለሆንኩ ነው•••? ከአንደበት በላይ እኮ ተግባር ነው ለእውነቱ የሚቀርበው አይደለም እንዴ ኤፍዬ•••? ካልነገርኩህ አታምንም•••?"
"ብትነግሪኝስ ምን አለበት አያስከፍል ቃልዬ! "
"እሺ ወድሃለሁ!"
"እሺ ወድሀለሁ አልሽ እህህ በጣም ደስ ይላል!"
"እንዴ እጠላሃለሁ አላልኩህ ለምን ደስ አይልም•••?"
"አይ አባባልሽ ከውስጥ ተቀድቶ በወጣ ስሜት ሳይሆን ለጥያቄዬ መልስ ለመስጠት ያህል የተባለ መስሎ ስለተሰማኝ ነው!" ስላት ፊቷን ቅጭም አርጋው ትክ ብላ ስትመለከተኝ ቆየችና •••
"ኤፊዬ!"
"ወዬ ቃል!"
"ምንድን ነው ማወቅ የፈለከው•••?"
"እኔን የሚሰማኝ ሁሉ አንቺን እንደሚሰማሽ?
" ለምሳሌ ምን•••?"
ከ 20 ላይክ ቡኋላ ክፍል 12 ይለቀቃል