"ዓለምን ሁሉ የመላ እርሱንም ዘጠኝ ወር ካምስት ቀን በተሸከመው ማኅፀንሽ እማፀናለሁ፡፡ በመውለድም ማኅተሙ ባልተለወጠ የድንግልናሽ ኃይል ሥጋ የለበሰውን ፍጥረት ሁሉ የሚያሳድገውን እርሱን ባሳደገ ጡትሽ ወተት እማለድሻለሁ፡፡ፈረሶቹዋን የሚያደላድል የሕይወት እሳት ሠረገላውንም የእሳት ነበልባል አደረገ እርሱን ባቀፉት ጉልበቶችሽ፡፡ የማይዳሰሰውን እሳት ያለ ጉጠት በዳሰሱት ቅዱሳት እጆችሽ እማልዳለሁ፡፡
ከገሊላው ንጉሥ ከሄሮድስ ፊት ከልጅሽ ከወዳጅሽ ጋራ ስትሸሺ መንገድ በመሄድ በደከሙት ቡሩካት እግሮችሽ በአዳም በፊቱ የሕይወት መንፈስ ያሳደረባት እርሱን በሳሙት ከንፈሮችሽ እማልዳለሁ፡፡ ልጅሽን ወስደው እንዳይገሉት ከሄሮድስ ሠራዊት ፈርተሽ ስለ ልጅሽ መራራ ልቅሶ ባለቀሱ ዓይኖችሽ እናቴ እማማ በማለት በታናሽ ብላቴና አንደበት፡፡ (በሕፃን አንደበት) ሲያጫውትሽ የሚጣፍጠውን ነገሩን በሰሙት ጆሮችሽ እማልዳለሁ፡፡"
(አርጋኖነ ድንግል ዘዓርብ )
እንኳን ለቊስቋም ማርያም ኅዳር 6 በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ::