የቅዱሳን ታሪካቸው ህይወታቸው ትምህርቶች


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


⛪️1ኛ ቆሮንቶስ 6÷2፤ቅዱሳን፡በዓለም፡ላይ፡እንዲፈርዱ፡አታውቁምን፧በዓለምስ፡ላይ፡ብትፈርዱ፡ከዅሉ፡ይልቅ፡ትንሽ፡
ስለሚኾን፡ነገር፡ልትፈርዱ፡አትበቁምን፧
@Brkeyazew
https://t.me/yekidusantarikachewhiywetachew

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




ነፍሳችን ወደዚያኛው ዓለም ስትሻገር ለዚህ ዓለም በነበራት ፍቅር ትስቃለች::

(ቅዱስ ባስልዮስ )


ጥበብ ግን ማናት ? የሆነች ሰው ናትን?ወይንስ እንዲሁ ምግብ ናት ? ወይንስ የየአኗኗራችን ስልት ናት ? ወይስ የፈላስፎች መራቀቅ ናትን? የሚሉ ጥያቄዎችን ይነሣሉ ። ስለዚህ መልሱን የሚለውን የጥበብ ሀገርዋ ወዴት ነው የሚለውን ጥያቄ ያነሳው ሊቁ ቅዱስ ኢጲፋንዮስ ይመልስልናል ፤እንዲህ ሲል "ጥበብ መድኃኒነ ውእቱ ወቤዘወነ በጥብሐ  ሥጋሁ ወተሣየጠነ በንዝኅተ ደሙ ወኅረየነ ለመንግስት "" ¶ ጥበብ ያልኩት ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ የሰጠን ከመከራ ያዳነን  መንግስቱን ለመውረስ የመረጠን መድኃኒታችን ክርስቶስ ነው ። ¶

   ስለ
ዚህ ጥበብ የተባለ ቤዛችን ጌታችን አምላካችን  ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ከእርሱ ያገኘናቸው  ትሕትና ፤ሃይማኖት ፤ጸሎት ፤ፍቅር ፤ብሉያትና ሓዲሳት ፤ሕገጋት፤ሥርዓታት፤ድርሳናት ፤ገድላት፤ትርጓሜያት ፤ሚሥጥራት ምንኩስና ክርስትያናዊነትንና በጎ አእምሮታት ክፉና ደጉን መለየት ሁሉ በእግዚአብሔር ተመሥርቶ ወደ እግዚአብሔር በሚያደርስ መንገድ የሚፈፀም ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ መራቀቆች ጥበባት ተብለው ይጠራሉ ማለት ነው ። አስቀድመን ጥበብ ክርስቶስ ነው ብለናል ።ከእርሱ የሚገኝ ሁሉም ጥበባት ይባላሉ ።

     መፅሐፈ ወግሪስ ገፅ 12~13


ቀዳሚት ሰንበት -ቅዱሳት አንስት

"ደግሞም ከእኛ ውስጥ ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን"

"ወቦ አንስትኒ እለ አንከራ ወነገራነ ለነ እለ ጌሳ ኀበ መቃብር "

(ሉቃስ 24:22)


ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ፤ ፀሐይን ተጎናጽፋ፤ ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ያላት፣ በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። እርስዋም ፀንሳ ነበር፣ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች /ራእየ ዮሐንስ 12:1-2/



ታላቅ ምልክት: ምልክት የሚለው ቃል በግሪኩ ሲመዮን (σημεῖον μέγα – a great sign) የሚለው ነው:: በግሪኩ አንዳች ለየት ያለ ትርጉም ያለውን ምልክት የሚያመለክት ነው:: በማቴዎስ ወንጌል 24፥30 ላይ በመጨረሻው ዘመን «የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል» ሲል ይህንን ነው የተጠቀመው::

ይህች ሴት ማን ናት?

ቀደምት አበው ይህችን ሴት በተመለከተ እርስ በእርሳቸው የተያያዙ ሁለት ዓይነት ትርጓሜዎችን ትተውልናል፡፡

1ይህች ሴት #ቤተ_ክርስቲያን_ናት፡፡ ክርስቶስን የወለደችው የምእመናን ቤተ ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን ናት። በዘመነ ኦሪት የሚታደጋት አጥታ፣ ከአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመናት ምጥ በኋላ ወንድ ልጅ የወለደችው ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያን በብሉይ ታስባ በሐዲስ የተገለጠች፣ በኦሪት ተወጥና በወንጌል የተፈጸመች፣ የብሉይ አበው ሊያዩዋት ተመኝተው የሐዲስ አበው ያገኟት ናት:: ጌታችን በወንጌል «አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሀሴት አደረገ አየም ደስም አለው /ዮሐንስ 8:56/ በማለት አስተምሯል::
አብርሃም በሕገ ልቡና የተጀመረው ፅድቁ ፍፁም የሆነው በዘመነ ሐዲስ ነው:: ቅዱስ ጳውሎስ የብሉይን አበው ዘርዝሮ «እነዚህ ሁሉ በእምነታቸው መስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፤ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ እንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና >> ብሏል / ዕብ 11:39 /::

ቪክቶርያኖስ ስለዚህ ጉዳይ ሲገልጥ «እርሷ የአበው ቀደምት የነቢያት፡ የቅዱሳን እና የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ናት። በምሳሌያቸው እና በመከራቸው የልጆቿ ፍሬ ሆኖ በሥጋ የሚገለጠውን ክርስቶስን በመጠ ባበቃቸው ይታወቃሉና፡፡ ለእነርሱም ከብዙ ዘመናት በፊት ቃል ተገብቶላቸው ነበር:: እርሱም ከእነዚሁ ሕዝቦች ነው ሥጋን የማው:: ፀሐይን መጎናጸፍዋ የተስፋውን ቃል ክብር እና የትንሣኤ ሙታንን ተስፋ ያመለክታል:: በእግሮቿ በታች ያለችው ጨረቃም የእነዚህ ቅዱሳን ሥጋ ግዴታ በሆነው እና በማያልቀው ሞት መውደቁን ያሳያል። እነርሱ በጨለማው ውስጥ እንደ ጨረቃ ደምቀዋል። በእራስዋ ላይ የሚታዩት አሥራ ሁለት ከዋክብትም ለእነርሱ ሲል ጌታችን በሥጋ የተወለደላቸው የአሥራ ሁለቱ አርእስተ አበው ምሳሌዎች ናቸው::» ብሏል:: (victorianus 12:1)

አቡሊዲስ ዘሮም ይህንን ሲተነትን ፀሐይ የተጎናፀፈችው ሴት አብ ቃሉን ወደ እርሷ የላከው ቤተ ክርስቲያንን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም ውበትዋ ከፀሐይ ብርሃን ይበልጣል፡፡ ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ናት ሲልም አርሷ ሰማያዊ ክብር ያላት መሆንዋን ገለጠ፡፡ ከጨረቃ ትበልጣለችና፡፡ በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል መታየቱ ቤተ ክርስቲያንን የመሠረቱ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ናቸው:: ልጅን ለመውለድ በምጥ መያዝዋም ቤተ ክርስቲያን መቼም ቢሆን በልቡናዋ አካላዊ ቃልን ከማሰብ እና ስለ እርሱም በአሕዛብ ዘንድ መከራን ከመቀበል እንደማታቋርጥ ሲገልጥ ነው» ብሏል::

ፀሐይን መጎናጸፍዋ ልብስዋ የክርስቶስ ክብር መሆኑን ያሳያል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ልብስዋ ጽድቅ ነውና። ጨረቃም ከእግሮቿ በታች መሆናቸው ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ ብትሆንም ከዚህ ዓለም (ሴኩላር) ሐሳብና ፍልስፍና የራቀች መሆንዋን ያመለክታል።

ታድያ «በቤተ ክርስቲያን» ውስጥ ለምን ከዓለማውያን የባሰ በደል፣ ክፋት፣ ስሕተትና ጥፋት ይታያል? ስለ ቤተ ክርስቲያን ስናስብ ሁለት ነገሮችን አብረን እናስብ። የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሕይወት፣ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች:: ቤተ ክርስቲያን ስንል የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሕይወት፣ በዚያ ላይም የበቀሉ ክርስቲያኖች ማለታችን ነው:: ጌታችን «እኔ የወይን ግንድ ነኝ፣ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ» ሲል አስተምሮናል። ወይን የሚባለው የወይኑ ግንድ፣ ቅርንጫፎቹና ፍሬዎቹ ናቸው:: ወይኑ ጌታችን፣ ቅርንጫፎቹ ክርስቲያኖች፣ ፍሬዎቹም የክርስቲያኖቹ ክርስቲያናዊ ሕይወት ነው:: በዚሁ ትምህርት ላይ «ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለው ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል» ብሏል። «ተቆርጦም ወደ ውጭ ይጣላል»፡፡ ምንም እንኳ መልኩ የወይን ቢሆንም ተቆርጦ ደርቆ የተቆረጠ የወይን ቅርንጫፍ ግን የወይኑ አካል አይደለም::

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ የሚመስላቸው ነገር ግን የደረቁ የወይን ቅርንጫፎች አሉ:: የእነዚህ የደረቁ ቅርንጫፎች እና የሚያፈሩት ቅርንጫፎች ሕይወት ይለያል፡፡ ጌታችን በዚህ ትምህርቱ «ፍሬ የሚያፈራውን ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ይጠራዋል» ሲል «በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል፤ ይደርቅማል» ብሏል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጉዞ ውስጥ የደረቁ ቅርንጫፎች የሚሠሩት ስሕተት የቤተ ክርስቲያን ስሕተት አይደለም፡፡ እነርሱ ከቤተ ክርስቲያን ጋር እንጂ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሉምና። የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሕይወት ክፋት ጥፋት፣ እንከን ስሕተት የለበትም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚበቅሉ ቅርንጫፍ ምእመናን ግን ፍሬ የሚያፈሩ አሉ፤ የደረቁም አሉ፡፡ የወይኑ አካል የሚባሉት ፍሬ የሚያፈሩት ናቸው ::

ክፍል 2
#ይህች ሴት እመቤታችን ናት... ይቀጥላል


© #ከእመቤታችን_ተወልዶ

ከእመቤታችን ተወልዶ /ሥጋን የለበሰው/(፪)
እኛን ሊያድነን ነው (፪)ከሞት እኛን ሊያድነን ነው
በቀራንዮ ተሰቅሎ /ደሙን ያፈሰሰው/(፪)
እኛን ሊያድነን ነው (፪)ከሞት እኛን ሊያድነን ነው
በሦስተኛው ቀን ተነስቶ /ሞትን ድል ያረገው/(፪)
እኛን ሊያድነን ነው (፪)ከሞት እኛን ሊያድነን ነው

ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን እህታችን👏👏❤️


https://www.facebook.com/share/18jcHzAH1L/


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አመ ፲ወ፯ ለሚያዝያ በዛቲ ዕለት ኮነ ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ ሰማዕተ ዘውእቱ እኁሁ ለዮሐንስ ወንጌላዊ።

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን የዘብዴዎስ ልጅ የወንጌላዊ ዮሐንስ ወንድም ሐዋርያው ያዕቆብ በሰማዕትነት አረፈ ።



ሰላም እብል ሐዋርያ ፍንወ፤
እኀወ ወንጌላዊ ዮሐንስ እንተ ይሄሊ ሕያወ፤
አህጉራተ ይስብክ ጊዜ አንሶሰወ፤
ድምፀ አራዊት ወዘአዕዋፍ ንቃወ፤
በመንፈስ ቅዱስ ያዕቆብ ለበወ።

(አርኬ )

ሰላም ለክሙ ጽጉባነ ምዑዝ ጽጌረዳ
ዘረከበክሙ ክርስቶስ ለባህረ ገሊላ በዐውዳ
አመ ሰዓተ ደይን ያዕቆብ ወዮሐንስ በዕለተ ፍዳ
በሉኒ ሊተ ዘዚአነ ወለትምህርትነ ወልዳ
እንዘ ትእኅዙ ለነፍስየ እዳ

(መልካም መዓዛ ያለውን ጽጌረዳ ለጠገባችሁት ለእናንተ ሰላም እላለሁ። ክርስቶስን በገሊላ ባህር አጠገብ ያገኛችሁት ቅዱስ ያዕቆብና ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ በቁርጥ የቅጣት ሠዓትና በፍርድ ቀን  ነፍሴን በእዳ ይዛችሁ እርሱ እኮ የእኛ ነው የትምህርታችን ልጅ ነው በሉልኝ። )

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን የሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብድዮስ በረከቱ ትደርብን ::

እንዲሁም ዛሬ የቅድስት ቤተክርስቲያን እና የነፍሳተ ብሉይ መታሰቢያ ነው ::

መሐሪ ይቅርታው የበዛ አምላክ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን ::


አንድ ለመሆን ቸኩሉ በአንድ መሰዊያ ላይ ተሰባስባችሁ የፍቅር አገልግሎትን የምታቀርቡ እናንተ የእግዚአብሔር ተወዳጅ ልጆች ልዩ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ጣፋጭ የሆነች ትዕግስትን ታጠቁ በእምነት ላይ አድስ ሰው ሁኑ እግዚአብሔር አድስ በሆነ ተፈጥሮ የፈጠረን ባልተከፋፈለ ፍጹም ክርስቲያናዊ በሆነ ልብ እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ነው ::

(ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ )


⛪️ የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ከሌሎች ልዮ
    የሚያደርገው......


  🍃በዲ/ን ጥበቡ ማሞ🍃

🌹መልካም ቆይታ አድምጡ 👂🥀


@yekidusantarikachewhiywetachew


ሴቶች ጥበብን ለመያዝ ከወንዶች ባላነሰ ይተጋሉ ::በዲያብሎስ እና በኃይሉ ላይ የሚካሄደው ጦርነት በሁሉም ዘንድ እኩል ነው ::ከተጋድሎ ጋር በተያያዘ ሕይወት ውስጥ የሴትነታቸው ልስላሴና ይሉኝተኝነት በምንም መንገድ እንቅፋት አይሆንባቸውም :: ምክንያቱም መንፈሳዊ ሕይወት የሚወጠነው በሥጋዊ ሕግ ሳይሆን በሕሊና ፈቃድ እና ውሳኔ በመሆኑ ነው ::ሴቶች በብዙ መንገድ ከወንዶች ጋር ሲነጻጸሩ ወይም ሲወዳደሩ መሪነቱን ስለሚይዙ የሰማያዊው እንቁ ጽዋ (አክሊል )ተሸላሚዎች ይሆናሉ ::


Saint. Johan chrysostom, homily viii mathew 2:2 in N.p...

ሴቶች ከወንዶች እኩል በአርአያ ቅድስት ሥላሴ ተፈጥረዋል ::በወንድ ባለው ሥጋ እና አጥንት ሴትም ተፈጥራለች ::ከእምነት ጋር በተያያዘ ጉዳይ ፈጣሪ ለሴቶች ከወንድ እኩል ጥንካሬና ችሎታን ሰጥቶናል ::ስለዚህ ጽናት, ንቃት, ትዕግስት እና አልበገር ባይነት ለሴትም ለወንድም እኩል የሆኑ ባሕርያት ናቸው ::

(St. Basil The Great P. G 31.624 C.)

"ወንድ የሚያሰኝ ገድል ያላቸው ብዙ በረሃውያት "ሴቶች አቅመ ቢስ ናቸው " የሚለውን ደካማ አስተሳሰብ ውድቅ አድርገው አሳይተዋል "

(ታሪክ ጸሐፊው ጰላድዮስ )


✝እንኳን አደረሳችሁ!

"" ነጻነትን ሰበከላቸው! "" (፩ኛ ጴጥ. ፫:፲፱)

"የበዓለ ትንሣዔ ትምህርት"

(ሚያዝያ 12 - 2017)

https://t.me/zikirekdusn


"የዚህ ዓለም ርኩሰት ያላገኛት የሙሽርነት አክሊል ይህች ናት፡፡ የኃሣር ያይደለች የክብር አክሊል ይህች ናት፡፡ ለርጉማን የማትገባቸው የበረከት አክሊል ይህች ናት፡፡የዓለም መድኃኒት በሚሆን ልጅዋ ስም ላልተጠቀሙት የምታደርሳቸው የመሃይምናን ጌጽ የምትሆን የጽድቅ አክሊል ይህች ናት የመለኮት የዕንቁ ሣፅን ለነዳያንም ሀብት ባለጸግነት የምትሆን የወርቅ ሙዳይ ይህች ናት፡፡

በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጽሽ እመቤቴ ማርያም ሆይ መሰንቆ ልቡናዬን ፍቅርሽን አነሣሣው የትንቢት መንፈስ ሆዴን አወከው ሰውነቴም ከምስጋናሽ መታገስ ተሳናት፡፡ልቡናዬም አንደበቴን ዘበዘበችው ምስጋና የመላውን ክብርሽንም እንዲናገር የግድ አለችው፡፡ በከንፈሮቼም የመንፈስ ቅዱስ ትንፋሽ ተሰማ፡፡"


(አርጋኖነ ድንግል ዘኃሙስ )




ለእግዚአብሔር የገባሁት ቃል ኪዳን የመረጋጋት እና የዝምታ ሕይወት ነበር ::እንደ ቃሌ ይህንን ሕይወት እየተለማመድኩ ሕሊናየ ከፍ ያለውን ነገር በሚመለከትበትና የሕይወት ፍልስፍናዬ ትክክል እንደሆነ እያመንኩ በመጣሁበት በዚህ ወራት ባልጠበቅኩት ጊዜና አጋጣሚ የተጫነብኝን ቀንበር ልሸከምበት የምችለውትከሻ አልነበረኝም :: ለእኔ አስፈላጊ የነበረው ነገር የስሜት ሕዋሳቶቼን በር ዘግቼ ከሥጋዊ እና ዓለማዊ ነገር ሁሉ ሸሽቼ ከራሴ ጋር ብቻ መሆንን ነው ::  ከራስ ጋ ከመነጋገር የበለጠ ደስታን የሚሰጥ ምን ነገር አለና ከማውቀው ከራሴ ጋር መወሰንን ወደድኩ :: ለራሴ እና ለእግዚአብሔር ነገርን እየተናገርኩ ከሚታይ እና ከሚዳሰሱ ነገሮች ሁሉ በላይ ትልቅ የሆነ ሕይወትን መኖርን ወደድኩ በልቡናዬ ውስጥ የምጫረውን ሰማያዊ ነገር ::

ከምድራዊ ሐሳብ ጋር ሳልቀላቅል መንፈሳዊ የሆነ ነገር በውስጤ እንዲያድር ማድረግ የዘወትር ፍላጎቴ ነበር  ይህ ሐሳብ ንጹሕ መስታወት የሰውን መልክ እንዲያሳይ እግዚአብሔርን እንድንመለከት የሚያደርግ የልቡና መስታወት ነው ::በብርሃን ላይ ብርሃንን የሚጨምር በእውቀት ላይ እውቀትን የሚጨምር በተስፋ የሚጠብቁት የሚደሰቱበት ከቅዱሳን መላእክት ጋር ሆነው እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት ስሜት ነው ::

"ከራስ ጋ ከመነጋገር የበለጠ ደስታን የሚሰጥ ምን ነገር አለና ከማውቀው ከራሴ ጋር መወሰንን ወደድኩ ::"

(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ )




#እመቤታችን_ቤዛዊተ_ኩሉ_ዓለም_ናት!!!

በማኅበራዊ ሚድያ ሲዘዋወር አንድ አባት የተናገሩት ቢድዮ አየሁት፡፡ጥቂት ነገር ልበል፡፡
          ቤዛ ምንድን ነው???
#ቤዛ፣ቤዛነት ማለት ስለ አንድ ነገር ምትክ መሆን ነው፡፡እመቤታችን ቤዛ ናት ማለት እግዚአብሔር ቃል ሰው እንዲሆን ከሰው ልጅ የሚጠበቅ ነገር አለ ይህም መርገመ አዳም ወሄዋን ያልወደቀበት ንጹሕ ዘርእ ነው፡፡
እመቤታችን ቤዛ የሆነችው ደቂቀ አዳም ይጠብቁት የነበረውን ንጽሕና ይዞ መገኘት ነው፡፡ስለዚህ እመቤታችን ቤዛ ናት ማለት የደቂቀ አዳምን ግብር ወክላ የተገኘች ስለደቂቀ አዳም ፋንታ በንጽሕና በቅድስና ቤዛ ሆነች ማለት ነው፡፡
#ቤዜነቷም፦
የንጽህና የቅድስና ቤዛነት
የድንግልና ቤዛነት
የመጽነስ ቤዛነት
የመውለድ ቤዛነት
የማሳደግ ቤዛነት
የመሰደድ ቤዛነት 
የርሀብ የጽምእ ቤዛነት
የሕማም የመከራ ቤዛነት
የአቂበ ህግ ቤዛነት ከፍላለች፡፡
ቤዛ አበው ነቢያት
ቤዛ ጻድቃን ነገሥት 
ቤዛ ንጹሃን ደናግል
ቤዛ ፍንዋን ሐዋርያት 
ቤዛ ግፉዓን ጽድቃን 
ቤዛ ከዓውያነ ደም ሰማዕት 
ቤዛ ስዱዳን ባሕታውያን
ቤዛ ተላውያን ፸ አርድእት ናት፡፡
እኒህ ሁሉ አበው በእመቤታችን ቤዛነት የዳኑ ናቸው እንጂ በእነርሱ ሥራ አይደለም የእነርሱ መከራ ሰውነታቸውን እንደ ወርቅ ቢያጸራውም አምላክን ለመወሰን አለበቁም የእመቤታችን የንጽሕና ቤዛ ግን በማሕፀኑዋ እንድትወስነው አድርጉዋታል፡፡

"እውነት እላችኋለሁ፥ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።
            ማቴ13:17::
"ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
                   ትን.ኢሳ.64:6
ነቢያት ሁሉ የአዳም መርገም ወድቆባቸው ሥራቸው ሁሉ ለጽድቅ አላበቃቸው ብሎ ኑረዋል፡፡ እመቤታችን ግን የአበውን ሁሉ ጩኸት የፈጸመች የጩኸታቸው ቤዛ ሆነችላቸው ማለት ነው፡፡
እመቤታችን ቤዛዊተ ዓለም ማለት ከዓለም የሚያስፈልገውን ሥራ ይዞ መገኘት ነው፡፡
ይህን ቤዛነት አለመረዳት እጅግ አደጋ ነው፡፡

"ንትፌሣሕ ኩልነ በዝክረ ስምኪ ጥዑም ወበደመ ዮሐንስ መአድም ቅድስት ማርያም ቤዛዊተኩሉ ዓለም"        ቅዱስ ያሬድ
"ኢትኅፈር ልደቶ እም ብእሲት እስመ ይእቲ ኮነተነ ምክንያተ ሕይወት  አስተጋበአተነ ቅድስት ማርያም ዘይእቲ ንዋየ ድንግልና ዘአልቦ ሙስና ወይእቲ ዘዳግም አዳም ገነት እንተ መንፈስ ወይእቲ ጽምርተ ህላዌ ወይእቲ በዓለ መድኃኒት እንተ ተቤዘወነ ጽርኅ ንጽሕት እንተ ባቲ ተመርዐወ ቃል"
         ተረ ቄር 18፡5
"ዮም ፍሥሓ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም እምሐና ወኢያቄም ከመ ተቤዙ ነቢያተ ወጸድቃነ አማን ተወልደት እመ ብርሃን"
                ቅዱስ ያሬድ
"መጽአ ዐቃቤ ሥራይ እም ኀበ አብ እምጽርሐ አርያም መድኃኒት ተረክበት በሀገረ ዳዊት እንተ ስማ ጽዮን ወተፈጸመ ዘተብህለ መኑ ይሁብ መድኃኒተ እም ጽዮን"
                       መጽ ምሥ 20፡11:
#ቅዱስ ያሬድ፣አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ቅዱስ ቄርሎስ ቤዛዊተ ዓለም ካሏት እነዚህ አባት ቤዛዊተ ዓለም የማይሎት ከማን ወገን ሆነው ነው??
መልሱ ከንስጥሮስ ወገን መሆናቸው ነው፡፡

#እመቤታችን ለዓለም ሁሉ ብቸኛ ንጽሕት ዘርዕ ሆና ከጥፋት በመታደግ ለሁሉም ቤዛ ሆናለች፡፡
ጠቅለል ሲል እመቤታችን ንጹሕ አካሏን ለዓለም ቤዛ አድርጋ ለእግዚአብሔር አቅርባለች ነው፡፡
"የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር::
              ትን. ኢሳ. 1:9::
#እሰግድ ለንጽሕናኪ ወአስተበርክ ለድንግልናኪ ማርያም ድንግል ቤዛዊተ ነፍስየ ዘኮንኪ!!!

❖እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው እንላለን!!!
             ❖አ.ዘ.ያዕቆብ፡፡
   ©ጌዴዎን ዘለዓለም::




" ተዝካረ ሰማዕታት ንጹሐን "

በሊብያ ምድር የተሰዉ ሰማዕታት ወንድሞቻችን ፱ኛ ዓመት መታሰቢያ!

2016

https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

https://t.me/zikirekdusn


መከራዬ በበዛ መጠን የጣዕመ ፍቅርህ ብርሃን በእኔ ላይ ያጽደለድላል ያረጋጋኛልም ::ራሱን ስለ አንተ ፍቅር አሳልፎ ለመስጠት በቁርጥ ሕሊና ለተዘጋጀ ሰው መከራው ከመጠን እስክያልፍም ድርስ ምሕረትህን አታዘገይም ::

ከዚህች ከመራራይቱ መከራ ጥዑም ጸጋ ይፈልቃልና ስለ ፍቅርህ ብሎ መከራ መስቀልን ለሚሸከም ሰው በመከራው ሁሉ አንተ አብረህው ካለህ ስቃዮቹ ሁሉ የተድላ ደስታ ምንጮች እና ፏፏቴዎች ይሆኑለታል ::ሊጠግባቸው የሚመኛቸው የጣዕመ ጸጋ እና ተድላ ደስታ መፍለቂያ ይሆኑለታል :: ስለ ፍቅሩ ሰውነታቸውን በመከራ የሚያስጨንቁትን በልቡናቸው ተገልጦ ያዘኑትን ለሚያረጋጋ መሥተፍሥሂ ለሚሆን ለእርሱ ምስጋና ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን በእውነት ያለ ሐሰት ይደረግ ::


(ቅዱስ ወቅሪስ )


🎁የበዓል ስጦታ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.