ቅዳሜ ማለት ቀዳሚት ሰንበት (የመጀመሪያዋ ሰንበት) ማለት ነው
መጀመሪያነቷም ከሀዲስ ኪዳኗ ሰንበት ከእሁድ ነው
ይህችንም ቀዳሚት ሰንበትን እግዚአብሔር በመጀመሪያ፦ ዓለምን ፈጥሮ ጨርሶ አርፎባታል
ወአዕረፈ እግዚአብሔር እምኩሉ ግብሩ በሳብዕት እለት
እግዚአብሔርም በሰባተኛዋ ቀን ከስራው ሁሉ አረፈ
ዘፍ 2÷2
በሁለተኛ፦ በዚህ ምድር ሥጋ ለብሶ ሲመላለስ ሙታንን አስነስቶባታል ድውያንን ፈውሶባታል ለምጻሞችን አንጽቶባታል እውራንን አብርቶባታል
በሦስተኛ፦ ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በልብሰተ ሥጋ ከተመላለሰ በኋላ በተለይም ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ወንጌልን ካስተማረ በኋላ በዕደ አይሁድ ተይዞ ተሰቅሎ ተገርፎ ሞቶ በመቃብር አርፎባት ውሏል
በአራተኛ ፦ በዓለም ፍጻሜ (ምጽዐት) የሰው ልጅ ሞቶ የሚያልቀው ዓርብ ነው ቅዳሜ የሰው ልጅ ሁሉ ከድካመ ሥጋ አርፎ ይውላል መሬትም አርፋ ትውላለች።
ይህችም ቀዳሚት ሰንበት ቅዳም ሥዑር ትባላለች
ቅዳም ሥዑር ማለትም የተሻረች ቅዳሜ ማለት ነው
ይህንን በመያዝ አንዳንድ ሰዎች የተሻረች ማለት ከበዓልነቷ መስሏቸው የስራ መስሪያ እለት የሚያደርጓት አሉ ይህ ግን ፈጽሞ ስሕተት ነው።
የተሻረች ማለት ግን ከመበላት ነው ፍትሐ ነገሥት ፍትህ መንፈሳዊ ሰንበታትን የሚያፆም ካህን ቢኖር ከክህነቱ ይሻር ይላል አን 15÷551
ስለዚህ በመጾም የተሻረች አለመጾሟ የተሻረባት መብል መጠጥ የተከለከለባት ማለት ነው ።
አክፍሎት፦ አክፍሎት ማለት ማክፈል ማለት ነው
ከምግብ ከመጠጥ ተከልክሎ ሳይበሉ ሳይጠጡ መዋል ይህንንም የጀመሩት ሐዋርያት ናቸው ሐሙስ ምሽት ጀምረው የተበተኑ ሐዋርያት ጌታ ከተሰቀለና ከሞተ ወደመቃብርም ከወረደ በኋላ ተሰብስበዋል ከዚህ በኋላም ሊመገቡ ሲሉ ከመካከላቸው አንዱ ያዕቆብ ጌታየ እሞታለሁ በሦስተኛው ቀን እነሳለሁ ብሏልና ትንሳኤውን ሳላይ አልመገብም አለ እርሱን አብነት አድርገው ሁሉም ሐዋርያት አክፍለዋል
የአክፍሎት ጊዜ ፦ የተቻለው ከሐሙስ ጀምሮ ያከፍላል ምክንያቱም ሐዋርያት ሐሙስ ምሽት በግዐ ፋሲካውን ከተመገቡ በኋላ እሑድ ነውና የተመገቡ ያልተቻለው ግን ዓርብ ይመገባል ቅዳሜን አክፍሎ ውሎ እሑድ አስቀድሶ የተቻለው ሥጋውን ደሙን ተቀብሎ ያልተቻለው ጸበሉን ጠጥቶ ይሔዳል
ሥርዐተ ቄጤማ ፦ በዚህች ዕለት አንዱና ጎልቶ የሚታወቀው ካህናትና ዲያቆናት በየቤቱ እየዞሩ ቄጤማ ያድላሉ ሲያድሉም አዳም ተመረመረ ዲያብሎስ ታሰረ እያሉ ነው ይህም ማለት የአዳምን ነጻ መውጣት የዲያብሎስን መጋዝ የሚያመለክት ነው ጌታ ተመረመረ ዲያብሎስ ታሰረም ይባላል ይህም ክርስቶስ በሄሮድስና በጲላጦስ ፊት ቆሞ ተመርምሮ ምንም እንዳልተገኘበት ለማመልከት ነው
ቄጤማ ፦ በኦሪቱ ብዙ በጎ ትውፊት አለው በኖኅ ዘመን ርግቧ ኀጸ ማየ አይኅ ነትገ ማየ አይኅ የጥፋት ውሃ ጎደለ ስትል ለኖኅ በአፏ ቀጤማ ይዛ መጥታለች
ካህኑም (ዲያቆኑ) ሐጸ ማየ ኃጢት ነትገ ማየ ኃጢአት የኃጢአት ውሃ ጎደለ ሲል ለሕዝቡ የምሥራች የለመለመ ቄጤማ ያድላል ።