ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ፤ ፀሐይን ተጎናጽፋ፤ ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ያላት፣ በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። እርስዋም ፀንሳ ነበር፣ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች /ራእየ ዮሐንስ 12:1-2/
ታላቅ ምልክት: ምልክት የሚለው ቃል በግሪኩ ሲመዮን (σημεῖον μέγα – a great sign) የሚለው ነው:: በግሪኩ አንዳች ለየት ያለ ትርጉም ያለውን ምልክት የሚያመለክት ነው:: በማቴዎስ ወንጌል 24፥30 ላይ በመጨረሻው ዘመን «የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል» ሲል ይህንን ነው የተጠቀመው::
ይህች ሴት ማን ናት?
ቀደምት አበው ይህችን ሴት በተመለከተ እርስ በእርሳቸው የተያያዙ ሁለት ዓይነት ትርጓሜዎችን ትተውልናል፡፡
1ይህች ሴት #ቤተ_ክርስቲያን_ናት፡፡ ክርስቶስን የወለደችው የምእመናን ቤተ ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን ናት። በዘመነ ኦሪት የሚታደጋት አጥታ፣ ከአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመናት ምጥ በኋላ ወንድ ልጅ የወለደችው ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያን በብሉይ ታስባ በሐዲስ የተገለጠች፣ በኦሪት ተወጥና በወንጌል የተፈጸመች፣ የብሉይ አበው ሊያዩዋት ተመኝተው የሐዲስ አበው ያገኟት ናት:: ጌታችን በወንጌል «አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሀሴት አደረገ አየም ደስም አለው /ዮሐንስ 8:56/ በማለት አስተምሯል::
አብርሃም በሕገ ልቡና የተጀመረው ፅድቁ ፍፁም የሆነው በዘመነ ሐዲስ ነው:: ቅዱስ ጳውሎስ የብሉይን አበው ዘርዝሮ «እነዚህ ሁሉ በእምነታቸው መስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፤ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ እንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና >> ብሏል / ዕብ 11:39 /::
ቪክቶርያኖስ ስለዚህ ጉዳይ ሲገልጥ «እርሷ የአበው ቀደምት የነቢያት፡ የቅዱሳን እና የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ናት። በምሳሌያቸው እና በመከራቸው የልጆቿ ፍሬ ሆኖ በሥጋ የሚገለጠውን ክርስቶስን በመጠ ባበቃቸው ይታወቃሉና፡፡ ለእነርሱም ከብዙ ዘመናት በፊት ቃል ተገብቶላቸው ነበር:: እርሱም ከእነዚሁ ሕዝቦች ነው ሥጋን የማው:: ፀሐይን መጎናጸፍዋ የተስፋውን ቃል ክብር እና የትንሣኤ ሙታንን ተስፋ ያመለክታል:: በእግሮቿ በታች ያለችው ጨረቃም የእነዚህ ቅዱሳን ሥጋ ግዴታ በሆነው እና በማያልቀው ሞት መውደቁን ያሳያል። እነርሱ በጨለማው ውስጥ እንደ ጨረቃ ደምቀዋል። በእራስዋ ላይ የሚታዩት አሥራ ሁለት ከዋክብትም ለእነርሱ ሲል ጌታችን በሥጋ የተወለደላቸው የአሥራ ሁለቱ አርእስተ አበው ምሳሌዎች ናቸው::» ብሏል:: (victorianus 12:1)
አቡሊዲስ ዘሮም ይህንን ሲተነትን ፀሐይ የተጎናፀፈችው ሴት አብ ቃሉን ወደ እርሷ የላከው ቤተ ክርስቲያንን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም ውበትዋ ከፀሐይ ብርሃን ይበልጣል፡፡ ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ናት ሲልም አርሷ ሰማያዊ ክብር ያላት መሆንዋን ገለጠ፡፡ ከጨረቃ ትበልጣለችና፡፡ በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል መታየቱ ቤተ ክርስቲያንን የመሠረቱ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ናቸው:: ልጅን ለመውለድ በምጥ መያዝዋም ቤተ ክርስቲያን መቼም ቢሆን በልቡናዋ አካላዊ ቃልን ከማሰብ እና ስለ እርሱም በአሕዛብ ዘንድ መከራን ከመቀበል እንደማታቋርጥ ሲገልጥ ነው» ብሏል::
ፀሐይን መጎናጸፍዋ ልብስዋ የክርስቶስ ክብር መሆኑን ያሳያል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ልብስዋ ጽድቅ ነውና። ጨረቃም ከእግሮቿ በታች መሆናቸው ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ ብትሆንም ከዚህ ዓለም (ሴኩላር) ሐሳብና ፍልስፍና የራቀች መሆንዋን ያመለክታል።
ታድያ «በቤተ ክርስቲያን» ውስጥ ለምን ከዓለማውያን የባሰ በደል፣ ክፋት፣ ስሕተትና ጥፋት ይታያል? ስለ ቤተ ክርስቲያን ስናስብ ሁለት ነገሮችን አብረን እናስብ። የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሕይወት፣ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች:: ቤተ ክርስቲያን ስንል የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሕይወት፣ በዚያ ላይም የበቀሉ ክርስቲያኖች ማለታችን ነው:: ጌታችን «እኔ የወይን ግንድ ነኝ፣ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ» ሲል አስተምሮናል። ወይን የሚባለው የወይኑ ግንድ፣ ቅርንጫፎቹና ፍሬዎቹ ናቸው:: ወይኑ ጌታችን፣ ቅርንጫፎቹ ክርስቲያኖች፣ ፍሬዎቹም የክርስቲያኖቹ ክርስቲያናዊ ሕይወት ነው:: በዚሁ ትምህርት ላይ «ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለው ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል» ብሏል። «ተቆርጦም ወደ ውጭ ይጣላል»፡፡ ምንም እንኳ መልኩ የወይን ቢሆንም ተቆርጦ ደርቆ የተቆረጠ የወይን ቅርንጫፍ ግን የወይኑ አካል አይደለም::
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ የሚመስላቸው ነገር ግን የደረቁ የወይን ቅርንጫፎች አሉ:: የእነዚህ የደረቁ ቅርንጫፎች እና የሚያፈሩት ቅርንጫፎች ሕይወት ይለያል፡፡ ጌታችን በዚህ ትምህርቱ «ፍሬ የሚያፈራውን ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ይጠራዋል» ሲል «በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል፤ ይደርቅማል» ብሏል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጉዞ ውስጥ የደረቁ ቅርንጫፎች የሚሠሩት ስሕተት የቤተ ክርስቲያን ስሕተት አይደለም፡፡ እነርሱ ከቤተ ክርስቲያን ጋር እንጂ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሉምና። የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሕይወት ክፋት ጥፋት፣ እንከን ስሕተት የለበትም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚበቅሉ ቅርንጫፍ ምእመናን ግን ፍሬ የሚያፈሩ አሉ፤ የደረቁም አሉ፡፡ የወይኑ አካል የሚባሉት ፍሬ የሚያፈሩት ናቸው ::
ክፍል 2
#ይህች ሴት እመቤታችን ናት... ይቀጥላል