የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አዲሱን የመቐለ ከንቲባ ከስራ አገዱ።
ፕሬዝደንቱ ዜዳንት " ለዶ/ር ረዳኢ በርሀ " በትላንትናው እለት ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ፤ አዲሱ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ ህጋዊ ያልሆነ ተግባራቸውን እንዲያቆሙ አሳስበዋል።"የመቐለ ከተማ ምክር ቤት መጠቀምያ በማድረግ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራ የሚፃረር ተግባር መፈፀም አይቻልም " ያለው የፕሬዝደንቱ ደብዳቤ የአዲሱ ከንቲባ ሹመት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ተቀባይነት እንደሌለው አስረድቷል።
አቶ ጌታቸው " የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚፃረር አቋም በመያዝ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር ያለን መዋቅር መምራት አትችሉም ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩም ከእርስዎ ጋር መሰራት አይችልም " ብለዋል።በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች " ህጋዊ አይደሉም " የተባሉት ከንቲባ የሚሰጡዋቸው አመራሮች እና ትእዛዞች ተቀብለው እንዳይፈፅሙ ፕሬዝዳንቱ አስጠንቅቀዋል።አዲሱ የመቐለ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ ፤ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት ህወሓት የስራ አስፈፃሚ ሆነው የተመረጡ መሆናቸው ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa