“በአስር ወራት ብቻ 20ሺ የሚሆኑ ኤርትራውያን ሀገራቸውን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዋል” - የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን
ከጥር ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት አስር ወራት 20ሺ የሚሆኑ ኤርትራውያን ሀገራቸውን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዋል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን አስታወቀ።ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ጥገኝነት በመጠየቅ የሚኖሩ ኤርትራውያን የተጠናከረ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጠይቋል።
"ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች በአፋር እና ትግራይ ክልሎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡት አለም አቀፍ ከለላ እና መሰረታዊ እርዳታ ለማግኘት ነው" ሲል ኮሚሽኑ ትላንት ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በአስር ወራቱ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ከተሰደዱ 20ሺ ኤርትራውያን በተጨማሪ በኢትዮጵያ ከ70 ሺ የሚበልጡ በኮሚሽኑ የተመዘገቡ ስደተኞች መኖራቸውንም የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን በመግለጫው አመላክቷል።
በስደት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ኤርትራውያኑ ስደተኞችን እንደደረሱ ድጋፍ መስጠት ያስፈልጋል ያለው ኮሚሽኑ ስደተኞቹን መመዝገብ እና ሰነድ እንዲዘጋጅላቸው ማድረግ ለሚሰጣቸው ከለላ የመጀመሪያው እና ወሳኙ እርምጃ ነው ሲል አሳስቧል።
ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ጥገኝነት የሚጠይቁ ኤርትራውያንን ለመመዝገብ የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን ጠቁሟል፤ ምዝገባ መካሄዱ ኤርትራውያን ስደተኞች ማግኘት የሚፈልጉትን የጤና፣ የትምህርት አገልግሎቶች፣ ከቤተሰብ ጋር የመገናኘት እድሎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ለመስራት የሚያስፈልጋቸውን ፈቃድ ለማግኘት መመዝገባቸው ወሳኝ ነው ሲልም አስታውቋል።ስደተኞቹ በአፋጣኝ እንዲመዘገቡ ማድረግ የህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል እጅግ አስፈላጊ ነው ሲልም አመላክቷል።
Via Addis Standard
@YeneTube