በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተደረሰው ስምምነት “አይመለከተኝም” ስትል ሶማሊላንድ ገለጸች!
በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና በሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ መካከል ቱርክ ውስጥ የተደረሰውን ስምምነት በሚመለከት ሶማሊላንድ አቋማን አስታወቀች።የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ ዋዳኒ ፓርቲ ቃል አቀባይ ሞሐመድ ፋራህ አብዲ በሁለቱ አገራት ስምምነት ላይ የመንግሥታቸውን አቋም ለቢቢሲ ሶማሊኛ ተናግረዋል።
ስምምነቱን በተመለከተ በሶማሊላንድ በኩል ያለውን አስተያየት ቃል አቀባዩ እንደተናገሩት በሁለቱ አገራት መካከል አንካራ ላይ የተደረሰው ስምምነት የሁለቱ አገራት ጉዳይ መሆኑን እና ሶማሊላንድ ሌላ አገር በመሆኗ ይህ ጉዳይ የሚመለከታት እንዳልሆነ አስረድተዋል።"የፈረሙት ሁለቱ አገራት ናቸው፣ እኛ ሶማሊላንድ ነን። ሁለቱ ወንድማማች አገራት የራሳቸውን ስምምነት ነው የተፈራረሙት። እነሱ ተነጋግረው ከስምምነት ላይ መድረሳቸው የተለመደ ነገር ነው።
እኛን የሚመለከት አይደለም" ሲሉ የገዢው ዋዳኒ ፓርቲ ቃል አቀባይ ሞሐመድ ፋራህ አብዲ ተናግረዋል።በተጨማሪም ቀደም ሲል በሶማሊላንድ ሥልጣን ላይ የነበረው መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ ያለበትን ሁኔታን በተመለከተ ሲናገሩ አዲሱ መንግሥት ገና ሥልጣን መረከቡ በመሆኑ ጊዜ ወስዶ እንደሚመለከተው እና የሚወስንበት መሆኑን ገልጸዋል።
"ገና ሥልጣን መረከባችን ነው፤ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገውን ስምምነት አልተመለከትነውም። ነገር ግን የምናየው ይሆናል፤ አይተነው የሶማሊላንድን ጥቅም የሚያስጠብቅ ከሆነ እንሠራበታለን፤ ካልሆነ ግን የሚቀር ይሆናል። ስለዚህ ምን እንሚሆን ለማወቅ መጠበቅ አለብን፣ ከዚያ በኋላ ውሳኔ ይሰጥበታል" ብለዋል ቃል አቀባዩ።
@YeneTube @FikerAssefa