የአሜሪካ ተዋጊ ጄት በቀይ ባህር ላይ 'በስህተት' ተመትቶ ወደቀ!
የአሜሪካው የጦር መርከብ በቀይ ባህር ላይ በስህተት የራሱን ተዋጊ ጄት መትቶ መጣሉን የአሜሪካ ጦር አስታወቀ።ሁለቱም የአሜሪካ የጦር ኃይል አባላት ጉዳት ሳይደርስባቸው መውጣት መቻላቸውን የጦሩ የማዕከላዊ ዕዝ ገልጿል።አሜሪካ በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ በሚገኘው እና በኢራን በሚደገፉ የሁቲ ታጣቂዎች የሚተዳደረውን የሚሳኤል ማከማቻ እና ማዘዣ ጣቢያ ላይ ተከታታይ የአየር ድብደባ ካደረገች በኋላ አጋጣሚው መከሰቱ ተገልጿል።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ አክሎም በቀይ ባህር ላይ የሚገኙ በርካታ የሁቲ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ፀረ መርከብ ክሩዝ ሚሳዔሎችን መምታቱን አስታውቋል።ማዕከላዊ ዕዙ በሰጠው መግለጫ በቀይ ባህር ላይ በነበረ ተኩስ ወቅት አደጋው መከሰቱን አረጋግጧል።"የአሜሪካው ሃሪ ኤስ ትሩማን የጦር መርከብ አካል የሆነው የዩናይትድ ስቴትስ ጌቲስበርግ በስህተት ከመርከቡ ሲነሳ ነበረውን ኤፍ/ኤ-18 መትቶታል" ሲል በመግለጫው አስታውቋል።
የወደቀው አይሮፕላን በየመን ዘመቻ ውስጥ ስለመሳተፍ አለመሳተፉ የታወቀ ነገር የለም።በሰንዓ በሚገኙ ዒላማዎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት "ሁቲዎች በአሜሪካ የባህር ኃይል መርከቦች እና በደቡብ ቀይ ባህር፣ ባብ አል-ማንደብ እና በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ ያሉ የንግድ መርከቦች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ለማደናቀፍ እና ለማቀጨጭ ነው" ሲል የማዕከላዊ ኮማንዱ አስታውቋል።
የአሜሪካ ወታደራዊ ሃይል "ኤፍ/ኤ-18ን ጨምሮ የአሜሪካ አየር ኃይል እና የባህር ሃይሎችን" በመጠቀም "በርካታ የሁቲ ተሽከርካሪዎች ወይም ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና በቀይ ባህር ላይ የሚገኙ ጸረ-መርከብ ክሩዝ ሚሳዔል" መምታቱን ተናግሯል።ሰሜን ምዕራብ የመንን የሚቆጣጠረው እና በኢራን የሚደገፈው አማፂው የሁቲ ቡድን ከፍልስጤማውያን ጎን መቆሙን በማስታወቅ የጋዛ ጦርነት መጀመርን ተከትሎ በእስራኤል እና በዓለም አቀፍ መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘር ጀመረ።
ከህዳር 2023 ወዲህ እንኳን የሁቲ ሚሳዔል ጥቃቶች ሁለት መርከቦችን በቀይ ባህር ሲያሰጥሙ ሌሎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል። ከእስራኤል፣ ዩናይትድ ኪንግደም ወይም እንግሊዝ ጋር የተገናኙ መርከቦች ላይ ብቻ እያነጣጠርን ነው ይላሉ።ባለፈው ታህሳስ ወር አሜሪካ፣ ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሌሎች 12 አገራት የቀይ ባህርን የመርከቦች እንቅስቃሴ ከጥቃት ለመከላከል 'ኦፕሬሽን ፕሮስፐሪቲ ጋርዲያን' የሚባል ዘመቻ አስተዋውቀዋል።
@YeneTube @FikerAssefa