የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በኢትዮጵያ ወደ ምድር ሲንቀሳቀሱ የታዩት የቁስ አካላት ስብስብ የጠፈር ፍርስራሾች አልያም የሚቲዮር አለቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ አስታወቀ!
የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 1፡30 ገደማ በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የታዩት የቁስ አካላት ስብስብ የጠፈር ፍርስራሾች አልያም የሚቲዮር አለቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ አስታውቋል።የታየው ስብስብ ወደ ደቡባዊ የሃገሪቱ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት በሰማይ ላይ ሲምዘገዘግ እንደነበረም ለማወቅ ተችሏል ሲል ተቋሙ ገልጿል።
የእነዚህ አካላት ስብስብ ክስተት ተፈጥሮ በእርግጠኝነት ለማብራራት ያስችል ዘንድ ሁኔታውን በቅርበት እያጣራ እንደሚገኝም አክሎ አስታውቋል።በቅርቡ በኬንያ በማኩኒ ካውንቲ ሙኩኩ በተባለችው መንደር ክብ ቁስ 2 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን 500 ኪሎግራም ክብደት ያለው ግዙፍ ብረት ከሰማይ መወደቁ ይታወቃል።
@YeneTube @FikerAssefa