በሰሜን ወሎ ዞን በ11 ቀበሌዎች ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሰብል ክምር በከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ወደመ!
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ 11 ቀበሌዎች ጥር 1/2017 ዓ.ም በደረሰው “ምክንያቱ ባልታወቀ” የእሳት ቃጠሎ የ154 አርሶ አደሮች የሰብል ክምር መቃጠሉ ተገልጿል፡፡የዋድላ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሉየ ረታ 4 ሺህ 560 ኩንታል የሚኾን 152 ክምር ላይ የደረሰው ቃጠሎ ጉዳት ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ጠቁመዋል፡፡
የዋድላ ወረዳ የአደጋ መከላከል እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ጽሕፈት ቤት ቡድን መሪ ምትኩ ሞላ በበኩላቸው እስካሁን ባለው መረጃ 770 የሚኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጉዳቱ ሰለባ መኾናቸውን መግለጻቸውን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa