በኢትዮጵያ የተከሰተው የቤንዚን እጥረት በሱዳን ካለው ጦርነት ጋር ተያያዥ መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳሃረላ አብዱላህ ገለጹ።
የኢትዮጵያ እስከ 80 በመቶ የሚሆነው ቤንዚን በሱዳን ወደብ የሚገባ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሯ በሱዳን ጦርነት ምክንያት ሙሉ አቅርቦቱ ለሙሉ ወደ ጅቡቱ መዞሩን ገልጸዋል። በዚህም ጁቡቲ ማስተናገድ ከሚችለው አቅም በላይ በመሆኑ ችግሮች መፈጠራቸውን ገልጸዋል።
“ከፈረንጆቹ 2024 የካቲት ወር ጀምሮ የጅቡቲው ሆራይዘን ተርሚናል ከአቅም በታች ሲያስተናግድ በመቆየቱ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ተከስቷል” ሲሉ ለኢቢሲ ተናግረዋል። ሌላኛው ሰሞኑን የተፈጠረው እጥረት የዋጋ ጭማሪ ይኖራል በሚል ግምት ነዳጅ በመያዝ መከሰቱንም አክለው ገልጸዋል።
@YeneTube @FikerAssefa