የቴሌ ብር ኤጀንት ሲሆኑ በሶስት የተለያዩ አይነቶች የኮሚሽን ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ
1. ከደንበኛ ብር ሲቀበሉ ወይም ብር ሲሰጡ(Transaction Commission):- የቴሌብር ተጠቃሚዎች በኤጀንት ሲስተናገዱ ከያንዳንዱ ትራንዛንክሽን የ 5% ኮሚሽን ለኤጀንቶች ይታሰብላቸዋል።
2. ደንበኛ ሲመዘግቡ (Registration Commission):- ደንበኞች በኤጀንት በኩል ሲመዘገቡ በያንዳንዱ ተመዝጋቢ የ15 ብር ኮሚሽን ለመዘገበው ኤጀንት ይሰጠዋል
3. የአየር ሰአት ሲሸጡ (airtime sales commission):- አንድ ሰው የቴሌብር ኤጀንት ሆኖ ከተመዘገበ በቀላሉ ከኤጀንት ሞባይል አፑ ላይ
የአየር ሰዓት መሸጥ ይችላል። ኢትዮ ቴሌኮም ከያንዳንዱ ሺያጭ የ 9% ኮሚሽን ለኤጀንቱ ታሳቢ ያደርጋል
ከላይ የተጠቀሱት ኮሚሽኖች በምን መልኩ ኤጀንቱ ይሰበስባቸዋል?
የቴሌብር ኤጀንት ሆነው መስራት ሲጀምሩ የኤጀንት አፑ ላይ ሁለት የብር ማስቀመጫ ኪሶች (wallet) ይኖሩታል። አንደኛው ተንቀሳቃሽ ብርዎ የሚቀመጥበት(main wallet) ሲሆን ሁለተኛው ደሞ ከላይ የተጠቀሱትን ስራዎች ሲሰሩ የሚያገኙትን ኮሚሽን የሚሰበስቡበት(commission wallet) ነው። ይህ ማለት ለያንዳንዱ የሚሰሩት ስራ የሚሰጥዎ ኮሚሽን ወድያውኑ ይደርሶታል ማለት ነው።
ኤጀንት ሆኖ ለመመዝገብ የሚያስፈልጉት መስፈርቶች ዋና ዋናዎቹ
1. የታደሰ የንግድ ፍቃድ
2. የታክስ ከፋይ ቁጥር ናትቸው(TIN number)
ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ካሟሉ በሚቀጥለው ዌብሳይት ተመዝግበው ስራ መጀመር ይችላሉ
http://mobilemoney.et/