አንድ የግሪክ አፈታሪክ አለ። ፕሮሜቴየስ የተባለው የእሳት አምላክ የሆነው እሳቱን ለሰው ልጆች ከሰጠ በኋላ ዜኡስ(የመብረቅና የሰማይ አምላክ) የሆነው ለሄፋስተስ(የጥበባት አምላክ) የመጀመሪያዋን ሴት ከአፈርና ከውሃ እንዲፈጥር አዘዘው። ሴቲቱም ከፈጠራት በኋላ ሁሉም አማልክት ለሴቲቱ በስጦታ ያበሸብሿት ጀመር። አቴና - ጥበብን፣ አፍሮዳይት - ውበትን፣ ሄርሜስ - ተንኮልን የመሳሰሉትን እንደ ስጦታ ሰጧት።
የዚህች ውብ ሴት ስም ፓንዶራ ነበር። በግሪክ ፓንዶራ ማለት 'ሁሉንም ስጦታ የተሰጣት' ማለት ነው። ዜኡስ ለፓንዶራ አንድ ማሰሮ ሰጣት፤ ቀጠለና "ይህ ማሰሮ በየትኛውም አጋጣሚ እንዳትከፍቺው!" ብሎ ከጥብቅ ማስጠንቀቂያ ጋር ሰጣት።
ኤፒሜቲየስ የተባለው 'ለሰው ዘር እንደተወካይ' የነበረው ለፓንዶራ ከዜኡስ ምንም ስጦታ እንዳትቀበል ብሎ መንታ ወንድሙ የሆነው የጥበባትና የእሳት ባለቤት የሆነው ፕሮሚትየስ አስጠንቅቆት ነበርና፤ ማሰሮውን ተቀብሏት ዜኡስ እንዳትከፍቺው ያላትን ትዕዛዛ በማፍረስ ማሰሮውን ይከፍተዋል።
ልክ ማሰሮውን እንደከፈተው በአለም ላይ ሁሉንም ጥፋቶችና መቅሰፍቶች ተለቀቁ። በሽታ፣ ጦርነት፣ ጥላቻ፣ ረሀብ፣ ሞት፣ ህመም፣ አደጋዎች ........የመሳሰሉትን !
ያቺ ፓንዶራ በስጦታዎች የተንበሸበሸችሁ ባመጣችው ጦስ፣ ያ ዜኡስ በሰጠው ትዕዛዝ፣ ያ 'ለሰው ልጅ ተወካይ ነኝ' በሚለው ኤፒሜቲየስ አስተዳደራዊ ስህተት አለም በጥፋትና በመቅሰፍት እንድትቀጣ ሆነ።
ዛሬም ፓንዶራዎች አሉ ለጥፋት ሰበብ የሆኑ!
ዛሬም ኤፒሜቲየሶች አሉ በእነርሱ እንዝላልነት ትውልዱ የሚቀጣ!
ምን ለማለት ነው..... ፓንዶራዎችና ኤፒሜቲየሶች ስጦታዎቻችሁና ፀጋዎቻችሁ በስርዓቱ ተጠቀሙ። የሌላን ንፁህ ነፍስ ስቀቀን አትሁኑ!
https://t.me/yinuca