"አዎ ! እሱ ጋ ያመኛል " መጽሐፍ አንዳንድ ሀሳቦች ፦
___
➫ ሁልጊዜ እሮሮ የሚዘበዝቡ፣ ሁልጊዜ ሰው ማጣጣል ላይ የተመሰጡ ሰዎች፣ ሁልጊዜም አልተሳካልን ዓይነት ደረት የሚመቱ፤ ለውድቀታቸው ሰው የሚወቅሱ ሰዎች፣ ለመውደቃቸው ኃላፊነት ከማይወስዱ ጋ አትወዳጅ ” ( ገጽ 17 )
➫ ደካማነት ምቹ ስፍራ ሲያገኝ እና ጊዜ ሲደላደልለት የሚያብብ ደዌ ነው። ( ገጽ 25 )
➫ መልካም አድራጎት የሚገዝፈው መልካም አድራጊው በየሰበቡ ካልፎከረበት ነው። ( ገጽ 28 )
➫ ወደ በጎ መለወጥ ብዙ ጠመዝማዛ መንገድ አለው። እንደ መበላሸት ቀላል አይደለም። ( 31 )
➫ አንዳንድ ትናንት ትናንት ላይ ብቻ አይቆምም። ዛሬያችንን የፈለገ ከትናንት አርቀን ሰቅለነዋል ብንል ፣ ጥለነው ብዙ መጥተናል ያልነው ትንናት ነጋችን ላይ በሁለት እግሩ ቆሞ እናገኘዋለን። ( ገጽ 49 )
➫ ፍቅር ማለት ለሚያፈቅሩት ሲሉ ከማይችሉት ጋ መታገል እንጂ የሚያሸንፉትን ማሸማቀቅ አይደለም። ( ገጽ 59 )
➫ ከአማኝ ጥቅማጥቅማችን አንደኛው ከአቅማችን በላይ የሆነ ሁነት ሲጋረጥብን እግዜር ላይ ሙጥኝ ማለት አይደል ?” ( ገጽ 65 )
➫ ለራስ ሰው አለመድረስን ያህል አርፋጅነት የለም። ( ገጽ 70 )
➫ ሴት ልጅ ትታለልልሃለች እንጂ አታታልላትም። ( 72 )
➫ የወንዶች መስገብገብ ይመስለኛል ወሲብን ወንድ ብቻውን የተለየ ደስታ የሚያገኝበት ያስመሰለው። ( ገጽ 91 )
➫ ፍቅራችን ለምናፈቅራቸው እንድንጠነቀቅ ካላደረገን ፍቅራችን የእውነት ላለመሆኑ ምስክር ነው። ( 95 )
➫ ሰው በዕድሜ ብዛት ማስተዋል ከቻለ የሚማረው ነገር አለመፍረድን ነው። ( 96 )
➫ የበዳይን ምክንያት ሳንጠይቅ በደልን ከምንጩ ማድረቅ እንዴት ይቻላል ?” ( 99 )
➫ ችግራችንን የምናይበት መንገድ የገዘፈ ስለሆነ ነው ከችግራችን በታች የምንሆነው። ( 104 )
➫ በአለም ላይ ስሜቱን እንደሚከተል ሰነፍ የለም፤ ስሜቱን ብቻ መከተል የሰው ባሕሪ አይደለም፡፡ ከስሜት እውነት ይበልጣል ፣ እውነት ነው በጊዜ ብዛት የማይደበዝዘው ፣ ስሜት ዘለቄታዊ ደስታን አይፈጥርም። ማደግ ማለት ደግሞ እውነትን እየመረረንም ቢሆን የመዋጥ ክህሎትን የማዳበር ሂደት ነው። ( 118 )
➫ አሸናፊነት የሚመጣው ተጋጣሚ የሚፈልገውን ባለመስጠት ነው። የምንፈልገውን የምናገኘው እራሳችንን ከምንፈልገው ነገር ባለማሳነስ ነው። ( ገጽ 130 )
➫ ራስን የመሆን እና ራስን የማወቅ ጥግ ራስን መቀበል ነው። በዙሪያችን ያሉ ሰዎች እንዲቀበሉን እኛ ቀድመን ራሳችን መቀበል አለብን። ደካማ ሰው ነው ድክመት ላይ የሚመሰጠው ፣ በራሱ የማይተማመን ፣ እንከኑ የሚያሳቅቀው ነው ጉድለት የሚያስሰው። የማይለወጥ ነገርን መቀበል ከራስ ጋ ያዋሕዳል። ያየነውን ጥሩ ነገር በትክክለኛው ሰዓት ማንፀባረቅ በራስ መተማመን ይባላል። በራሳቸው የማይተማመኑ ሰው ማሳነስ ላይ ሲረማመዱ የሚውሉ ናቸው። ( ገጽ 130 )
➫ ማደጋችን የሚለካው የምንፈልገውን ሁሉ ባለማድረግ ነው። ( ገጽ 155 )
➫ ሕመማችን የሚባባሰው የበሽታችን ምክንያቶች እናክምህ ሲሉን አይደል ?” ወዳጃችን ሲያቆስለን ሕመማችን የሚበረታው እንደሚያስብልን ማስመሰሉ ስለማይቀር ነው። ( 155 )
➫ ባልተሳተፍንበት ነገር መስዋዕት የመሆን ያህል ከንቱነት የለም !! ( ገጽ 157 )
➫ ተገማች አለመሆን ዓላማን ለማሳካት ምቹ ነው። ( 162 )
➫ ከተበደለ የበለጠ ፣ መበደሉ የገባው በዳይ ኑሮው ሲኦል ነው !! ( 165 )
(Rama Gutema)
https://t.me/yinuca