አንድ የስነ-ሰብ /Anthropology/ ተመራማሪ ወደ ደቡብ አፍሪካ ገጠራማ መንደር ለስራ ያቀናል። በቆይታውም ከህጻናት ጋር መግባባትን ይፈጥራል። እናም ሕጻናቱን ለማስደሰት አንድ ሽልማት ያለው ጨዋታ ያዘጋጃል።
ጨዋታውም፣ በማንጎ የተሞላ አንድ ቅርጫት ከዛፍ ስር ያስቀምጣል፣ ህጻናቱን ከዛፉ አንድ መቶ ሜትር እንዲርቁ አደረገ፣ ከዛም እንዲህ አላቸው ፦
"እኔ ጀምሩ ስል ቀድሞ ቅርጫቱ ጋ የደረሰ የፈለገውንና የሚችለውን ያህል ማንጎ ይበላል።"
ጨዋታው ተጀመረ።
ህጻናቱ ግን ከጨዋታው ህግ ውጪ ያልተጠበቀ ነገር አደረጉ።
ይህም ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው እኩል ወደ ቅርጫቱ ሮጡ። ከዚያም አንድ ላይ በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ማንጎ በአሸናፊነት መንፈስ ተካፍለው መብላት ጀመሩ።
የስነ-ሰብ ተመራማሪውም በመገረም "ለምን እንዲህ አደረጋቹ?"ሲል ጠየቃቸው።
ሁሉም በአንድነት "ኡቡንቱ /Ubuntu/ !" በማለት መለሱለት።
በመቀጠል አንዱ ህፃን እንዲህ አለው ፦
"እንዴት ሌሎች ጓደኞቻችን ተከፍተው አንድ ልጅ ብቻውን ይደሰታል? ይሄ ባህላችን አይደለም።"
"ኡቡንቱ/Ubuntu/" የቃሉ መሠረት የደቡብ አፍሪካው የዙሉ ማሕበረሰብ ሲሆን፤ ትርጓሜውም ፦
"ለመኖሬ ምክንያት አንተ ነህ፤ ላንተም መኖር እኔ!" የሚል ሰብዓዊነትን ያዘለ ፍልስፍና ነው።
👉 https://t.me/yinuca