በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ፤ ራሳቸውን ፋኖ ብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች ትላንት በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ንጹሃን ተገደሉ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ሰለልኩላ በተባለች ቀበሌ ራሳቸውን ፋኖ ብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች ትላንት በፈጸሙት ጥቃት ቁጥራቸው ያልታወቁ በርካታ ነዋሪዎች እንደተገደሉ ዋዜማ በሥፍራው ካሉ ምንጮቿ ሰምታለች፡፡
ጥቃቱ ማንነትን መሠረት ያደረገ እንደኾነ የጠቀሱት ምንጮች፣ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ወደ ነዋሪዎች ቤት ዘልቀው በመግባት በስለታማ መሳሪያዎች አሰቃቂ ጥቃት መፈጸማቸውን ዋዜማ ከነዋሪዎቹ መረዳት ችላለች።
ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ሲፈጽሙ በተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረጽና በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በማጋራት ጭምር እንደነበር ያወሱት ምንጮች፣ ጥቃቱን ተከትሎ ባካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መንገሱንና ነዋሪዎች ከፍተኛ በስጋት ውስጥ መኾናቸውን አስረድተዋል።
Via ዋዜማ
#ዳጉ_ጆርናል