ጀነራል አል ቡርሀን የአሜሪካን ማዕቀብ ውድቅ አደረጉ
የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበሩ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን አሜሪካ በእርሳቸው ላይ የጣለችውን አዲስ ማዕቀብ ምንም ተጽእኖ እንደሌለው በመግለጽ ውድቅ አድርገውታል። አል ቡርሃን ቅዳሜ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከሆነ "የዩኤስ ውሳኔን ለማንበብ እንኳ አልጓጓሁም" ብለዋል።
በውጭ ሀገር የተከፈተ የባንክ አካውንት ወይም ሪል እስቴት የለኝም፣ በኦምዱርማን ብሔራዊ ባንክ ውስጥ ያለኝ የሀገር ውስጥ አካውንት እንኳን እንደማንኛውም የጦር ሃይል መኮንን ደሞዜን ለመቀበል ብቻ የተገደበ ነው” ያሉት አልቡርሀን የዋሽንግተን ንብረቱን ለማገድ መወሰን እንዳስገረማቸው ገልፀዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ በአል ቡርሃን ላይ የሰላም ድርድርን በማደናቀፍ እና በሲቪሎች ላይ ጉዳት ሲደርስ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ባለፈው ሐሙስ ማዕቀብ መጣሏ አይዘነጋም። የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ለማዕቀቡ መንስኤ ምክንያት የጎደለው የቦምብ ጥቃት፣ በሲቪል ኢላማዎች ላይ እንደ ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎች የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እና ከህግ አግባብ ውጭ የሆኑ ግድያዎች መሆናቸውን ጠቅሷል።
አል-ቡርሃን ግን የሱዳን ህዝብ ድል ለመጠለፍ ለሚፈልጉ ሁሉ እንደማይፈቅዱ እና ሰራዊቱን የሚደግፉ ኃይሎች ከጦርነቱ በኋላ ስልጣን እንደማይዙ በመግለጽ ሰራዊቱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ያለውን ገለልተኝነት ገልፀዋል። አክለውም ፈጣን የድጋፍ ሰጪ ኃይሎች በሀገሪቱ የወደፊት ሁኔታ ውስጥ ለሚደግፏቸው ሰዎች ምንም ቦታ የለም ብለዋል። ያለን አማራጭ መሬቱን ነፃ አውጥተን ከፖለቲካ ደጋፊዎቻቸው ጋር ለዘላለም ማባረር ነው ድል ቅርብ ነው ሲሉም አክለዋል።
በአልጃዚራህ ግዛት በሲቪሎች ላይ ጉዳት መድረሱን አስመልክቶ ቡርሃን እንዳሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ምንም አይነት ችግር እንደሌለ አረጋግጠውላቸዋል። የሱዳን ጦር የመንግስት ዋና ከተማ የሆነችውን ዋድ ማዳኒን መልሶ ከተቆጣጠረ በኋላ ሰራዊቱ ሰላማዊ ሰዎችን ገድሏል ሲሉ የተቃዋሚው የሲቪልና ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ማስተባበሪያ (ታጋዱም) ተችቷል።
በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል