Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት የጠራው ሰልፍ እየተካሄደ ነው
ምክርቤቱ ለክልሉ መገናኛ ብዙሀን በላከው ደብዳቤ በአክሱም ከተማ በሚገኙ ሁለተኛ ደረጀ ትምህርት ቤቶች ከጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የተፈፀመው ህገወጥ በሆነ የሂጃብ ክልከላ ምክንያት የእስልምና እምነት ተከታይ ሴት ተማሪዎች ለወራት ከትምህርት ገበታ እንዲገለሉ ማድረጉን ገልፆል።
ምክርቤቱ አክሎም እስካሁን ድረስ ለተለያዩ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ያልናቸው አካላት በአካልና በፅሑፍ ጥያቄ ስናቀርብ ብንቆይም እስካሁን ድረስ ጉዳዩ መፍትሄ ሳያገኝ መጥቷል ብሏል።
በዚህ ምክንያትም ጥያቂውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ በአደባባይ ለመጠየቅ ምክርቤቱ ዛሬ ጥር 13 ቀን 2017 ዓ/ም በመቀለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ይገኛል። ሰልፉ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክርቤትና ከክልሉ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዋና ፅህፈት ቤት መነሻውን አድርጎ በሮማናት አደባባይ ፍፃሜውን እንደሚያደርግ ዳጉ ጆርናል ከትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።
በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል