የ75 ዓመቷ አዛውንት ህንድ አገር ለሌላ ህክምና የወሰዳቸው ጉዳይ የልጅ እናት አደረጋቸዉ
የ75 ዓመቷ ወይዘሮ መድህን ሓጎስ የመቀለ ከተማ 18 ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ ከዚህ ቀደም ልጅ ያልወለዱ ብሎም አንድ ጊዜ ፅንስ መቋጠር ችለው የነበሩ ቢሆንም ፅንሱ በመቋረጡ ምክንያት ከዚህ ቀደም ልጅ ወልደው አቅፈው ለመሳም አልታደሉም፡፡
ታድያ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነው እየኖሩ ሳለ ላለባቸው ከባድ የጭንቅላት ህመም ህክምና ለማድረግ ወደ ህንድ ሀገር ያቀናሉ። በህንድ ሀገር ህክምናቸውን እየተከታተሉበት በነበሩት ተቋም ውስጥ በርካታ ሴቶች ሰልፍ ይዘው እየተጠባበቁ ይመለከታሉ በዚህ ሰዓትም አዛውንቷ ሰልፉ የምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። በቦታው የነበሩ ሰዎችም በተፈጥሮአዊ መንግድ ፅንስ መቋጠር ያልቻሉ እንስቶች በሰው ሰራሽ መንገድ ፅንስ ለመቋጠርና ልጅ ወልደው ለመሳም የሚጠባበቁ መሆናቸው ይነገራቸዋል።
ይሄኔም ነበር የ75 ዓመቷ አዛውንት ከሄዱበት ህክምና በተጨማሪ ምናልባት ልጅ የሚወልዱበት እድል ካለ ለመሞከር የወሰኑት። በውሳኔያቸው መሰረትም በሰው ሰራሽ መንገድ ፅንስ ቋጥረው ለሶስት ወራት በህንድ ሀገር ከቆዩ በኃላ ወደ ትግራይ መቐለ ከተማ በመመለስ ህክምናቸውን መከታተል ይቀጥላሉ።
ከዚህ ቀደም ፈጣሪዬን ልጅ እንዲሰጠኝ ሳይሆን ካለብኝ በሽታ እንዲፈውሰኝ ነበር የምፀልየው የሚሉት ወ/ሮ መድህን የአከባቢው ሰው ብሎም የሀይማኖት አባቶች ምን ይሉኛል በሚል ፍራቻ እርግዝናውን 9 ወራት እስኪሞላው ድረስ ከቤተ ዘመድ ሆነ ከጎረቤት ደብቀውት መቆየታቸውን ይናገራሉ።
ታድያ ለዘጠኝ ወራት እርጉዝ በነበሩበት ሰዓት የተለመዱት የእርግዝና ምልክቶችም ሆነ አምሮት አልነበረኝም የሚሉት አዛውንቷ በመጨረሻም በቀዶ ህክምና ወንድ ልጅ ተገላግለው አሁን ህፃኑ በጥሩ ጤንነት እንደሚገኙ የአዛውንቷን ቃለ መጠይቅ የሰራቸው የሰግለለት ሾው ጋዜጠኛዋ አድሓነት ገብረእግዚአብሄር ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥኝ ተናግራለች።
በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል