የሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የገጠመው ችግር ለመቅረፍ የገቢ ማሰባሰብ ስራ ሊጀመር ነው
👉 አካባቢው በረሃማ በመሆኑ ለከፍተኛ ድርቅ የሚጋለጥ ነው
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በማዕከላዊ ጎንደር ሃገር ስብከት በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት ለሚገኘው የሙት አንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንደነት ገዳም የገቢ ማሰባሰቢ መርሃ ግብር ሊከናወን ነው።ለገዳሙ እስካሁን 11 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ የነበረውን ቦታ የማስተካከል እንዲሁም ሌሎች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ እና ወደ ገዳሙ የሚደርስ 8 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ ተከናውኗል ።
እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት እና ገዳማት መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን እየሰጡ እያገለገሉ እንዲቀጥሉ ገቢ የማሰባሰብ መርሃ የሚከናወን መሆኑ ተነግሯል በራሳቸው አቅም ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን ማከናወን እንዲሁም ምዕመኑ በሚሰጠው መባ እና አስራት በኩራት ይጠቀሳሉ። ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም በአሁኑ ወቅት የገጠመው ችግር ለመቅረፍ የገቢ ማሰባሰብ ስራ አስፈላጊ ነው ተብሏል።
በማዕከላዊ ጎንደር ሐገረ ስብከት በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት የሚገኘው ይህ ገዳም፣ ከዘጠና በላይ መነኮሳትና በመቶ የሚቆጠሩ ፀበልተኞች የሚገኙበት እጅግ ድንቅ ተዓምር ያለበት ታሪካዊ የአንድነት ገዳም ነው ። ይሁን እና መነኮሳቱ በአሁኑ ወቅት ትልቅ ችግር ውስጥ ይገኛሉ። አካባቢው በርሃማ በመሆኑ በበጋ ወቅት ለከፍተኛ ድርቅ ይጋለጣል። በዚህም ምክንያት ምንም ዓይነት አዝዕርት አይበቅልበትም ይህን ተከትሎ ቀደም ሲል ድጋፍ ያደርጉ የነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ሳይቀር ለገዳሙ ምንም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ተቸግረዋል መባሉ ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ሰምቷል።
ገዳማዊያኑ የሚቀምሱት እህል፣ የሚለብሱት ልብስ በመጠኑ የተሟላላቸው ቢሆንም ከጾም፣ ጸሎት መልስ ስጋቸውን የሚያሳርፉበት ቤት የላቸውም። በአንድ ጎጆ ውስጥ ለሶስት ለአራት የሚያድሩበት ሁኔታ መኖሩ ተነግሯል ።በዚህ ገዳም የሚገኙ ገዳማዊያን ከጸሃይ፣ ከብርድ፣ከዝናብ የሚከላከል መጠለያ አጥተው በከፍተኛ ችግር እየተፈተኑ የሚገኙ በመሆኑ፣ ገዳማዊያኑን ከነዚህ ችግሮች እንዲወጡና በቀጣይም ገዳሙ ራሱን እንዲችል ለማድረግ፣ በጠቅላይ ቤተክህነት እውቅና እና በሐገረ ስብከቱ ፍቃድ ገዳሙ ብቻ የሚጠቀመው በገዳሙ ስም የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ይፋ ተደርገዋል ። በሕዝበ ክርስቲያኑ በሚደረገው ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን፣ ገዳሙም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በወረዳ ቤተ-ክህነት፣በሐገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጸድቆ በሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬና የቅርብ ክትትል እየተደረገበት በመሰራት ላይ ይገኛል።
እነዚህን የታቀዱ ለገዳሙ አስፈላጊ እና መሰረታዊ የሆኑትን የልማት ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ገቢ ለማሰባሰብ የሚረዱ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶችን ለመጠቀም ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል