ቲክቶክ ሕፃናትን በሚያካትቱ የወሲብ የቀጥታ ስርጭት ትርፍ እያገኘ ነው ተባለ
ቲክ ቶክ ገና ከ15 ዓመት በታች በሆኑ እና በአሥራዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች በሚከናወኑ ወሲባዊ የቀጥታ ስርጭት ትርፋማ እየሆነ እንደሚገኝ ተመላክቷል። በኬንያ የሚኖሩ ሦስት ሴቶችን እንደተናገሩት ይህን ተግባር የጀመሩት በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያሉ ነው። በሌሎች የመልእክት መላላኪያ መድረኮች ለሚላክ ወሲባዊ ይዘት በግልፅ ለማስተዋወቅ እና ክፍያ ለመደራደር ቲክቶክን እንደተጠቀሙ ተናግረዋል።
ቲክ ቶክ “ለመሰል ብዝበዛ ምንም ትዕግስት የለኝም” ሲል ለቢቢሲ አስታውቋል። የቀጥታ ስርጭቶች ከኬንያ በቲክ ቶክ ታዋቂ ናቸው ። በእያንዳንዱ ምሽት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ሴቶች በአለም ዙሪያ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚመለከቱት ገጾች ላይ ሲጨፍሩ ይታያል።ናይሮቢ ውስጥ ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ነው፣ እና የቲክ ቶክ ህይወት ሙሉ በሙሉ እንደቀጠለ ነው። አንዲት ሴት ካሜራዋን አብርታ በመቀመጫዋ ስትጨፍር ወይም ቀስቃሽ ምስል ስትነሳ ሙዚቃ በኃይ ይደመጣል፣ ሌሎች ተጠቃሚዎች እርስ በርሳቸው ይጨዋወታሉ። ስሜት ገላጭ ምስሎች "ስጦታዎች" ከዚያም ይቀጥላሉ።ባየናቸው አንዳንድ የቀጥታ ስርጭቶች ላይ የጾታዊ አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ ኮድ የተደረገባቸው የወሲብ ቃላት ጥቅም ላይ ውለዋል ሲል ቢቢሲ ዙግቧል።
የኢሞጂ ስጦታዎች ለቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት ክፍያ ሆነው ያገለግላሉ ። ምክንያቱም ቲክቶክ ግልጽ የሆኑ ወሲባዊ ድርጊቶችን እና እርቃን ይዘቶችን ስለሚያስወግድ ነው።በሌሎች መድረኮች ላይ የበለጠ ግልጽነት ያለው ይዘት ይላካል። ስጦታዎች ወደ ገንዘብ ሊለወጡ ይችላሉ።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል