ዕለታዊ ዜናዎች
1.ባለፉት ስድስት ወራት ከደረሱት የተሸከርካሪ ግጭቶች 40 አደጋዎች በቀለበት መንገድ ላይ የተከሰቱ ናቸው ተባለ። በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት በአጠቃላይ 150 የተሽከርካሪ ግጭት አደጋዎች የደረሱ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 40 አደጋዎች በቀለበት መንገድ ላይ የተከሰተ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ተናግሯል፡፡ ቀሪዎቹ 110 የግጭት አደጋዎች ደግሞ ከቀለበት መንገድ ውጪ የደረሱ ናቸው።
በመንፈቅ ጊዜ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በተሽከርካሪዎች ግጭት ሳቢያ ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ባለው የመንገድ መሰረተ-ልማት ላይ ጉዳት መድረሱን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡
2. በኢትዮጵያ 28 ሺህ ሰዎች ለውሻ ዕብደት በሽታ መጋለጣቸው ተገልጿል። ከነዚህ ውስጥም93 በመቶዎቹ ከሞት ድነዋል ተብሏል። በተያዘው በጀት ዓመት በስድስት ወራት ውስጥ 28 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በውሻ ዕብደት በሽታ (ራቢስ) መያዛቸውን የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። በበሽታው ከተያዙት 93 በመቶ የሚሆኑት በተደረገላቸው ሕክምና ከሞት ተርፈዋል ብሏል ኢንስቲትዩቱ። የውሻ ዕብደት በሽታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ለበሽታው ተጋላጭ ሆነዋል፣ በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ ወደ 28 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በውሻ ተነክሰው የሕክምና ርዳታ ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት መጥተዋል ተብሏል። ከነዚህ ውስጥ 93 በመቶ የሚሆኑት የሕክምና ርዳታ በማግኘታቸው ከሞት መትረፋቸውን ተጠቅሷል፡፡
3. 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል ዳፕና ዩሪያ የጫኑ መርከቦች ወደብ ደረሱ። ለ2017/18 የምርት ዘመን 1 ሚሊየን 100 ሺህ ኩንታል ዳፕ እና ዩሪያ የጫኑ መርከቦች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተናግሯል፡፡ ይህንን ተከትሎ እስከ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ከውጭ የተጓጓዘው የአፈር ማዳበሪያ መጠን ወደ 5 ሚሊየን 392 ሺህ 600 ኩንታል ከፍ ማለቱ ተጠቁሟል፡፡ ከዚህ ውስጥ 3 ሚሊየን 717 ሺህ 212 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካይነት ለአርሶ አደሮች በመከፋፈል ላይ ይገኛል።
@zena_ethiopia24