ዜና ETHIOPIA 🇪🇹


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Telegram


ዜና ETHIOPIA 24 || ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ
ተአማኒ እና ትክክለኛ መረጃዎችን በፍጥነት የምታገኙበት ልዩ የኢትዮጵያውያን ቻናል ነው።
🇪🇹ወቅታዊ መረጃዎች
🇪🇹ልዩ ልዩ ዘገባዎች
🇪🇹መዝናኛ ዜናዎች
🇪🇹ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል
ጥቆማ ለመስጠት 👇
@Zena_ethiopia_support_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ዴንማርካውያን የአሜሪካዋን ካሊፎርኒያ ለመግዛት ዘመቻ ጀመሩ

ዴንማርካውያን ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የአሜሪካዋን ግዛት ካሊፎርኒያ ለመግዛት የኦንላይን ዘመቻ ጀምረዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዴንማርክ ግዛት ስር ያለችውን ግሪንላንድ ለመግዛት ያቀረቡት ሃሳብን ተከትሎ ነው ዘመቻው የተጀመረው።

ሃቪየር ዱቶይት በተባለ ግለሰብ የተጀመረው ዘመቻ በጥቂት ስአታት ውስጥ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎችን ፊርማ አሰባስቧል።
@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


ዜናወችን በፍጥነት ለማግኘት 👉 https://t.me/+UkCE9JasVeY5NzU0


የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የሱማሊያ አቻቸውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸውን ሱማሊያ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው የሱማሊያ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሀይል ውስጥ የኡጋንዳ ወታደሮች የኢትዮጵያን ወታደሮች ተክተው እንዲገቡ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡

በተለይም የኢትዮጵያ ወታደሮች በሚገኙበት በጌዶ፣ ቤይና ባኩል ግዛቶች የኡጋንዳ ወታደሮች እንዲሰማሩ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር አስረድቷል፡፡ በተጨማሪም የሱማሊያ ደቡብ ምእራብ ግዛት በሚገኘው ባይደዋ ከተማ የኡጋንዳ ጦር ሀይል የጦር ሰፈር እንዲያቋቁም ሀሳብ አቅርበው የነበረ ሲሆን ሙሴቪኒ ግን ውድቅ ማድረጋቸውን ዘገባው ገልጿል፡፡

ፕሬዝደንት ሙሴቪኒ በባይደዋ ከተማና በሞቃዲሾ መካከል ርቀት እንዳለ ጠቅሰው በመሀል ያለው መንገድ ደግሞ በአሸባሪ ሀይል መያዙን አስረድተዋል፡፡ የኡጋንዳ ወታደሮች ከተሰማሩ በኋላ ሀይል ለማጠናከር ተጨማሪ ወታደሮችን በአውሮፕላን ማጓጓዝ አስቸጋሪ ስለሚሆን እዚያው ያሉት የኢትዮጵያና የኬንያ ወታደሮች ባሉበት እንዲቀጥሉ ማለታቸውን ዘገባው አስረድቷል፡፡
@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


ኬላዎች እንዲነሱ ተወስኗል ተባለ‼

ሙሉ መረጅ ለማግኝት
👉👉👉👉@zena_ethiopia24


ሙሉ መረጅ ለማግኝት
👉👉👉👉@zena_ethiopia24


ሙሉ መረጃለማግኝት
👉👉👉👉👉@zena_ethiopia24


"የፍትሕ ሚኒስቴር በእኔ እና በእኔ ስም በሚጠራው መዝገብ ላይ ያቀረበው ክስ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የለውም::

ሙሉ መረጃ ለማግኝት ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
👉👉👉@zena_ethiopia24


"የተከሰስኩት የመንግሥትን ብልሹ አሠራር በማጋለጤ ነው:: 


ሙሉ መረጃ ለማግኝት ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
👉👉👉@zena_ethiopia24


ሙሉ መረጅ ለማግኝት ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
👉👉👉@zena_ethiopia24


ሙሉ መረጆለማግኝት ,,,,,,,,,,,,,,,,,
👉👉👉👉@zena_ethiopia24


ሙሉ መረጅ ለማግኝት,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
👉👉👉👉@zena_ethiopia24


በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ.....
👉@zena_ethiopia24


በታገዱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ “ተጨማሪ ምርመራ” እየተከናወነ መሆኑን ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑ አስታወቀ

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ.....
👉@zena_ethiopia24


በባህርዳር ዩኒቨርስቲና ሆስፒታሎች የሚሰሩ የህክምና ዶክተሮች የዶ/ር አንዷለምን ግድያና በህክምና ባለሙያዎች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እንዲቆም የሚጠይቅ ሰልፍ ጠየቁ።

ቪዲዮውን ለመመልከት......

👉 @zena_ethiopia24


አስመጪዎች መክፈል የሚችሉት ቅድመ ክፍያ መጠን ላይ ማሻሻያ ሊደረግ ነው


ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ.....
👉@zena_ethiopia24


የ14 አመት ታዳጊ በማገት ከወላጆቿ 1.5 ሚሊየን ብር የተቀበሉ ግለሰቦች

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ.....
👉@zena_ethiopia24


የሃማስ ባለስልጣን ሳሚ አቡ ዙህሪ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የአሜሪካ  ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥ ለመቆጣጠር ያሰቡት እቅድ  'አስቂኝ' እና 'የማይረባ' እንዲሁም  መካከለኛው ምስራቅን ሊያተራመስ  ይችላል ብለዋል።

"ትረምፕ ጋዛን ለመቆጣጠር ስላላቸው  ፍላጎት  የሰጡት አስተያየት አስቂኝ እና የማይረባ ነው። እንደዚህ አይነት ሀሳቦች ክልሉን ወደ ቀውስ ሊከቱ  የሚችሉ ናቸው" ሲሉ አቡ ዙህሪ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ፍልስጤማውያን ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ ከተደረገ በኋላ አሜሪካ  በጦርነት የተጎዳውን የጋዛ ሰርጥ በመቆጣጠር በኢኮኖሚ እንደሚያዳብር ተናግረዋል።


ትራምፕ ይሄን አስገራሚ እቅዳቸውን ዝርዝር መረጃ ሳያቀርቡ ይፋ ያደረጉት ማክሰኞ ዕለት በዋሽንግተን ከጎበኙት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ሳውዲ አረቢያ ፍልስጤማውያንን ከመሬታቸው ለማፈናቀል የሚደረገውን ማንኛውንም ሙከራ ውድቅ እንዳደረገች የሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ  በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


ወደ ትልቁ ዜና ETHIOPIA ቻናላችን ይቀላቀሉ👉 @zena_ethiopia24


ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ለማሰባሰብ ታቅዷል !!

ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ለማሰባሰብ መታቀዱ የተገለጸ ሲሆን አገልግሎቱን ለማስፋት እና የተጀመረውን የሕንጻ ግንባታ ለማጠናቀቅ የፊታችን የካቲት 01 ቀን 2017 ዓ.ም በሰይፉ ፋንታሁን ዩቱብና ፣ በሌሎችም መገናኛ አውታሮች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብርን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጥቷል።

በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች 44 ቅርንጫፎችን ከፍቶ ደጋፊና ጧሪ የሌላቸው አረጋውያን፣የአእምሮ ሕሙማን፣ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ የማይችሉ የአልጋ ቁራኛ የሆኑትን እና በጎዳና ላይ የወደቁትን በማንሳት ሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ለዚህም በቀን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርግ አቶ ብንያም በለጠ ተናግረዋል።

አክለውም የበጎ አድራጎት ማኅበሩ ለጀመረው ሕንጻ ማጠናቀቂያ ለመሰብሰብ ከታቀደው የገንዘብ ገቢ በተጨማሪም በአይነትና በተለያዩ ነገሮች ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻልም ገልጸልዋል።

አያይዘውም መቄዶንያ መንግሥታዊ እና ሃይማኖታዊ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ተቋሙን በማገዝ ረገድ የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24


ዕለታዊ ዜናዎች

1.ባለፉት ስድስት ወራት ከደረሱት የተሸከርካሪ ግጭቶች 40 አደጋዎች በቀለበት መንገድ ላይ የተከሰቱ ናቸው ተባለ። በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት በአጠቃላይ 150 የተሽከርካሪ ግጭት አደጋዎች የደረሱ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 40 አደጋዎች በቀለበት መንገድ ላይ የተከሰተ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ተናግሯል፡፡ ቀሪዎቹ 110 የግጭት አደጋዎች ደግሞ ከቀለበት መንገድ ውጪ የደረሱ ናቸው።
በመንፈቅ ጊዜ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በተሽከርካሪዎች ግጭት ሳቢያ ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ባለው የመንገድ መሰረተ-ልማት ላይ ጉዳት መድረሱን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

2. በኢትዮጵያ 28 ሺህ ሰዎች ለውሻ ዕብደት በሽታ መጋለጣቸው ተገልጿል። ከነዚህ ውስጥም93 በመቶዎቹ ከሞት ድነዋል ተብሏል። በተያዘው በጀት ዓመት በስድስት ወራት ውስጥ 28 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በውሻ ዕብደት በሽታ (ራቢስ) መያዛቸውን የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። በበሽታው ከተያዙት 93 በመቶ የሚሆኑት በተደረገላቸው ሕክምና ከሞት ተርፈዋል ብሏል ኢንስቲትዩቱ። የውሻ ዕብደት በሽታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ለበሽታው ተጋላጭ ሆነዋል፣ በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ ወደ 28 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በውሻ ተነክሰው የሕክምና ርዳታ ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት መጥተዋል ተብሏል። ከነዚህ ውስጥ 93 በመቶ የሚሆኑት የሕክምና ርዳታ በማግኘታቸው ከሞት መትረፋቸውን ተጠቅሷል፡፡

3. 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል ዳፕና ዩሪያ የጫኑ መርከቦች ወደብ ደረሱ። ለ2017/18 የምርት ዘመን 1 ሚሊየን 100 ሺህ ኩንታል ዳፕ እና ዩሪያ የጫኑ መርከቦች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተናግሯል፡፡ ይህንን ተከትሎ እስከ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ከውጭ የተጓጓዘው የአፈር ማዳበሪያ መጠን ወደ 5 ሚሊየን 392 ሺህ 600 ኩንታል ከፍ ማለቱ ተጠቁሟል፡፡ ከዚህ ውስጥ 3 ሚሊየን 717 ሺህ 212 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካይነት ለአርሶ አደሮች በመከፋፈል ላይ ይገኛል።

@zena_ethiopia24
@zena_ethiopia24

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.