የሃማስ ባለስልጣን ሳሚ አቡ ዙህሪ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥ ለመቆጣጠር ያሰቡት እቅድ 'አስቂኝ' እና 'የማይረባ' እንዲሁም መካከለኛው ምስራቅን ሊያተራመስ ይችላል ብለዋል።
"ትረምፕ ጋዛን ለመቆጣጠር ስላላቸው ፍላጎት የሰጡት አስተያየት አስቂኝ እና የማይረባ ነው። እንደዚህ አይነት ሀሳቦች ክልሉን ወደ ቀውስ ሊከቱ የሚችሉ ናቸው" ሲሉ አቡ ዙህሪ ለሮይተርስ ተናግረዋል።
ፍልስጤማውያን ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ ከተደረገ በኋላ አሜሪካ በጦርነት የተጎዳውን የጋዛ ሰርጥ በመቆጣጠር በኢኮኖሚ እንደሚያዳብር ተናግረዋል።
ትራምፕ ይሄን አስገራሚ እቅዳቸውን ዝርዝር መረጃ ሳያቀርቡ ይፋ ያደረጉት ማክሰኞ ዕለት በዋሽንግተን ከጎበኙት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
ሳውዲ አረቢያ ፍልስጤማውያንን ከመሬታቸው ለማፈናቀል የሚደረገውን ማንኛውንም ሙከራ ውድቅ እንዳደረገች የሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
@zena_ethiopia24