✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
#አደራ
°°°°°°°°°°°°
በቀል የእግዚአብሔር ነው ስጥ ለሱ ቂምህን፤
ሁለቱን አትጨፍን ግለጥ አንድ አይንህን፤
አባትህን አስብ እንዴት እንደኖረ፤
በጀግንነት ታሪክ ጠላት ያባረረ ክንዱን የሠበረ፤
እናትህን አስብ እንዴት እንደኖረች፤
በእምነት በሀይማኖት አንተን ያሳደገች አንተን ያስተማረች፤
ወገኔ ታናሽህ ነኝ እኔ የምልህ የለኝም፤
ብቻ ግን አድምጠኝ ጀግና ሁን ሳትፈራ፤
ጣናን እንዳናጣው እባክህ አደራ!
አሁን ዘራፍ ብትል ብትቀብጥ ብታቅራራ፤
ያኔ ገዝተናታል ግብፅን እንዳትፈራ፤
ብቻ ግን ወገኔ አባይን አደራ!!
አባቶች አውርሰው ፍቅር ያላት ሀገር፤
ደማቸውን አፍሰው በእናቲቷ ምድር፤
እኛ ስንባጨቅ ስንባላ እንዳትፈርስ፤
እባክህ ወንድሜ በዘር እና ክልል በጎሳ አትኩራ፣
አጥተን እንዳናጣት ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አደራ!!!
ተዉ አትንኳት እሷን ላትፈርስ አትቆስቁሷት፣
ይልቅ ተጠቃለል እሷን ተከተላት በእምነት ምሰላት፣
እሷ እንዳታዝንብህ እድሜህ እንዳያጥር፤
መቅሠፍት እንዳይከብህ ሳታለቅስ አምርራ፤
የሀገሪቷን እናት የአለሙን መዳኛ ተዋህዶን አደራ!!!
ተዋህዶን አደራ!!!
በ✍ዲ/ን:የአብስራ ዘኢትዮጵያ
#አደራ
°°°°°°°°°°°°
በቀል የእግዚአብሔር ነው ስጥ ለሱ ቂምህን፤
ሁለቱን አትጨፍን ግለጥ አንድ አይንህን፤
አባትህን አስብ እንዴት እንደኖረ፤
በጀግንነት ታሪክ ጠላት ያባረረ ክንዱን የሠበረ፤
እናትህን አስብ እንዴት እንደኖረች፤
በእምነት በሀይማኖት አንተን ያሳደገች አንተን ያስተማረች፤
ወገኔ ታናሽህ ነኝ እኔ የምልህ የለኝም፤
ብቻ ግን አድምጠኝ ጀግና ሁን ሳትፈራ፤
ጣናን እንዳናጣው እባክህ አደራ!
አሁን ዘራፍ ብትል ብትቀብጥ ብታቅራራ፤
ያኔ ገዝተናታል ግብፅን እንዳትፈራ፤
ብቻ ግን ወገኔ አባይን አደራ!!
አባቶች አውርሰው ፍቅር ያላት ሀገር፤
ደማቸውን አፍሰው በእናቲቷ ምድር፤
እኛ ስንባጨቅ ስንባላ እንዳትፈርስ፤
እባክህ ወንድሜ በዘር እና ክልል በጎሳ አትኩራ፣
አጥተን እንዳናጣት ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አደራ!!!
ተዉ አትንኳት እሷን ላትፈርስ አትቆስቁሷት፣
ይልቅ ተጠቃለል እሷን ተከተላት በእምነት ምሰላት፣
እሷ እንዳታዝንብህ እድሜህ እንዳያጥር፤
መቅሠፍት እንዳይከብህ ሳታለቅስ አምርራ፤
የሀገሪቷን እናት የአለሙን መዳኛ ተዋህዶን አደራ!!!
ተዋህዶን አደራ!!!
በ✍ዲ/ን:የአብስራ ዘኢትዮጵያ