ላንተ ብቻ አልተዘጋጀም!
ህይወት የምልልስ መንገድ ነች ። የከፍታውና የዝቅታው መንገድ ምልልስ ፣ የመጎዳትና የመንፃት ምልልስ ፣ የመሰበርና የመጠገን ምልልስ ፣ የማዘንና የመደሰት ምልልስ ። ስለዚህም ነው የነዚህን ምልልስ አይቀሬነት ተገንዝቦ ችግሮችን ከማጉላትና በደስታም ጫፍ ከመንካት መቆጠብ አስፈላጊ የሆነው ። የዝቅታ ጊዜያት ፣ የመረበሽ ወቅቶች የሚባሉት የፍራቻ ፣ የሃዘን ፣ የመገለል ፣ የመጎዳት ፣ የመቸገር ፣ የመሰቃየትና አስጨናቂ ጊዜያት እንዲሁ መጥተው የሚሔዱና የተለመዱ (normal) የሚባሉ የህይወት ክስተቶች ናቸው ። ብቻህን መፍታት ያልቻልከው ችግር ካለ እርዳታ ጠይቅ ፣ እንቅልፍ የሚነሳህ አስጨናቂ ሃሳብ ካለብህ ለልብ ወዳጅህ ተንፈስ በል ፣ እንደ ከባድ ጭነት የከበደህ ሸክም ካለብህ ለአምላክ አዋየው ፣ ለእርሱ አስረክበው ፣ በእርሱ ላይ ጣለው ። ያንተን ችግር በማቅለሉ የሚመፃደቅ አምላክ እንዳልሆነም አስታውስ ።
አዎ! ጀግናዬ..! አንተን መርጦ አልመጣም! ላንተ ብቻ አልተዘጋጀም ፣ አንተ ላይ ስለሆነ ብቻ ተዓምርና የማይሆን አይነት ነገር እንዳይመስልህ ። ማንኛውም ሰው እንደሚወድቀው ትውድቃለህ ፣ እንደማንኛው ሰው ትሰበራለህ ፣ ተስፋ ትቆርጣለህ ፣ ታዝናለህ ። ማንም እንደሚሆነው ትከዳለህ ፣ ትናቃለህ ፣ ትገፋለህ ። ይህ ሁሉ ግን አንተ ላይ ብቻ የተከሰተ እንዳልሆነ አስታውስ ። በሰወኛው ባህሪ ለብቻ ከፍ ማለት እንጂ ለብቻ መጎዳትን አንወድ ይሆናል ። ነገር ግን የሰውነት ማንነታችን ማለፍ የሚገባንን አስቸጋሪና አስከፊ ጊዜም እንድናልፍ ያደርገናል ። በውስጣችን የገነባነው ጠንካራው ስብዕና ወደፊት ያሻግረናል ።
አዎ! የሆነብህ ፣ የደረሰብህ ፣ እየሆነብህ ያለው ሁሉ አዲስ አንዳልሆነ አስተውል ። አመጣጡ ያንተ መዳረሻ እርሱን አልፈህ ፣ እርሱን ተሻግረህ የምትደርስበት መሆኑን ለማስገንዘብ እንደሆነ እወቅ ። መጨነቅህ ፣ ማዘንህ ፣ ተስፋ ማጣትህ አዲስ አይደለም ፤ ሰው ነህና ከእነዚህ ከባድ ሁኔታዎች መንፃት አትችልም ። ከመጡ ቦሃላ ግን ማንፃትና ማስተካከል ትችላለህ ፤ ከእነርሱ ነፃ መውጣት ትችላለህ ። በነገሮች መበላሸት አትደነቅ ፣ በእቅድህ አለመሳካት እትረበሽ ፣ በሚያስጨንቁና በሚያናድዱ የህይወት አጋጣሚዎች የውድቀትና የበታችነት ስሜት አይሰማህ ፣ ብዙ እንቅልፍ አልባ ምሺቶችን ማሳለፍህ ፣ ረፍት አልባ ጊዜያት ውስጥ መገኘትህ የማይታመንና ይበልጥ ጫና ውስጥ ከከተተህ ማመንንና መቀበልን የመጀመሪያ አማራጭህ አድርገው ። ለብቻ የመብሰልሰልን ፣ በውስጥ የመያዝን ፣ በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገር መፍራትን እንመፍትሔ መቁጠር አቁም ። ካንተ ችግር በላይ አሳልፈው ዛሬም ደስተኛ የሆኑ ሰዎች እንዳሉ አስታውስ ። እንዲያልፍ የፈቀድክለት የትኛውም ከባድና አስቸጋሪ ጊዜ ያልፋልና በማካበድና ብዙ በመጨነቅ ስሜትህንና ጊዜህን አታባክን ።