የፍቅር ቀን 💕


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


♣♦♣ @Qelematcommentbot
Comment===== @blc_lion
@betty1012

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


❤️‍🩹አንዳንዶች ምንም ነገር ሳንሰጣቸው
ንፁህ ፍቅር ይሰጡናል አንዳንዶች ደግሞ
ሁሉንም ነገር ሰተናቸው ህመም ይሰጡናል❤️🔐🥀

     🔥🌷ከወደዱት ያጋሩ🌷🔥

https://t.me/+T3iav1JquCYERetm


ጃክ ማ” እንዲህ ይላል፡-

‘’#ገንዘብና_ሙዝን #ከዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጥ ዝንጀሮዎች #ሙዙን ይመርጣሉ። ምክንያቱም #ገንዘብ ብዙ ሙዝ እንደሚገዛ አያውቁም!

አብዛኛው ሰው ላይ ተመሳሳይ ሙከራ ብታደርጉና በአንድ የተወሰነ የግል ስራ (ቢዝነስ) እና በወር ደመወዝ መካከል ምርጫቸው ምን እንደሆነ ብትጠይቁ አብዛኛው ሰው ወርሃዊ ደመወዝ ያለው ስራን ይመርጣል። ምክንያቱም ወራዊ ደመዝ ከስጋት ነፃ ስለሚያደርግ እና ልክ እንደ ወንዝ ውሃ ዘወትር የሚፈስ ስለሆነ ነው።

እውነቱ ግን ትንሽም ቢሆን የግል ስራ (ቢዝነስ) ከወርሃዊ ደሞዝ የበለጠ ገቢ እንደሚያመጣ ፣ ከግል ስራ የሚመጡ ዕድሎች የተሻለ ህይወት እንደሚሰጥ ብዙዎች ስለማይረዱ ነው።
ለምሣሌ: በእኛ ሀገር እንኳን ጠንክሮ የሰሩ ማህበራት የኑሮ ለውጥ አስመዝግበዋል። ከስራ አጥነት ዛሬ የራሳቸው የግል ገቢ ማገኛዎችን ፈጥረው ካደረጃው አካል ተሽለው እየኖሩ ነው።

#ጃክ_ማ ከሀያ ጊዜ በላይ ለቅጥር ወይም ለደመወዝ ቢሎ ለመቀጠር የሞከረ ነገር ግን ዛሬ አለመሳካቱን ለበጎ ነው ቢሎ ወስዶ የአለማችን አንቱ የተባለ የግል ቢዝነስ ባለበት ነው።


​​​​​​​​❦ ​​​​​​══•⊰❂ ጣፋጭ ግጥሞች  ❂⊱•══ ❦


#ወረኛ_ነው_እያልሽ

የቤቴን ገመና ዘራብኝ አውጥቶ
ያሽሟጡብኝ ጀመር ሀገር ሁሉ ሰምቶ።

አደባባይ ወጣ ጉዴን አዳረሰው
በምላሱ ስለት ገመናዬን ማሰው።

አጋሬ ነው ብዬ ሁሉንም ብነግረው የልቤን ዘርዝሬ
ሹክ ቱስ እያለ ያደባባይ ሚስጥር ሆነብኝ ሚስጥሬ።

በ'ኔና አንተ ይቅር ብዬ የነገርኩትን የጓዳዬን እውነት
ከ እንቅልፉ ተነስቶ አፉን አሟሸበት።

እንዲ እንዲ እያልሽ ላየሺው ሰው ሁሉ
የኔን ወረኛነት ትሰብኪያለሽ አሉ።
ከጀማሽ መካከል በጄ ሚልሽ ጠፋ
ሀሜት ነው ቅኝቱ ቱልቱላሽ ሲነፋ።

እውነቱ ግን እየው እውነቱን ግን ስሚ
ከቆሰልሽም ቁሰይ ከደማሽም ድሚ።

የኛኑ ገመና አውጥቼ አልበተንኩም
እንዲ ናትም ብዬ ለማንም አላልኩም።

ግን የሚያሳዝነው ማስተዋል ተስኖሽ እንደ ቸኮለ ጅብ ቀንድ እንደሚነክሰው
ተናግረሽ አረፍሺው ወሬ ሰምቶ ቢያድር በቃኝ ለማይል ሰው።

እኔን ያማሽ መስሎሽ የምላስሽን በትር
ወረኛ ነው እያልሽ በምሽት በቀትር
እየሰነዘርሺው ልክ ላንቺው ቢጤ ወሬን አሰንቆ አሽሙር ለሚጠጣ
እድሜ ላንቺ ፍቅሬ የቤታችን ጓዳ አደባባይ ወጣ።

እውነቱ ግን እየው እውነቱን ግን ስሚ
ከቆሰልሽም ቁሰይ ከደማሽም ድሚ።

እኔማ ነበርኩኝ ያሳብሽ ከረጢት የሚስጥርሽ ዋሻ
ወረኛ ነው ብለሽ ብታሚኝም እንኳ በስተመጨረሻ።

የሚገርመው ነገር ካለስም ስም ሰተሽ ብትለጥፊብኝም
ላንቺ ይብላኝ እንጂ እኔን አልከፋኝም።

ይባስ ደስ ብሎኛል ክበሪልኝ ፍቅሬ
አይደለሁም እንጂ
ወረኛ እንኳ ብሆን ወሬን ያስተማርሺኝ የወሬ መምህሬ
አንቺ መሆንሽን ባደባባይ ቆመሽ መስክረሻል ዛሬ።

#በሄኖክ_ብርሃኑ


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏



➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

Join us  👉


አንድ ልብ አለችኝ ብዙ የተጎዳች😔
ከጎኗ የሚሆን ሰው ፈልጋ ያጣች🤷‍♂
በሰው ተከብቤ ሰው ይናፍቀኛል🤦‍♂
ልቤ ነጋ ጠባ አንድ ሰው ይለኛል😢
ልቤ የናፈቃት አንዷን የኔ ተስፋ💔
ልቧ አልረጥብ አለ ብደክም ብለፋ🙆‍♂
አውቃለሁ ፈሪ ነኝ አንቺን ለማሳመን ቃለት ማልደረድር😞
እመኝኝ የኔ ውድ ልቤ ማፍቀር እንጂ አይችልም መናገር።


       ,,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,,
                  •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
     @   ,,,,,,📩
━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━
     


​​​​​​​
                   
                    ❣:¨·.·¨: ❣
                 አይንሽን ጨፍኚ🌺
             ┈┈••◉❖◉●••┈┈


ልዩ ተሰጥኦ አለሽ፤
ታጣቂ ዘራፊ
በአይንሽ አይተሽ ብቻ፤
ልብ የምታጠፊ
የሆዴን የአንጀቴን፤
ልነግርሽ መጥቼ
ዲዳ ሆኜ ቀረሁ፤
አይንሽን አይቼ
ጀግና ወንድ ተብሎ፤
በኔ አፍ ሚጠራ
አይንሽን እያየ፤
የልቡን ሚያወራ
ለደቂቃ አይንሽን፤
አተኩሬ ባየው
አትጠራጠሪ፤
ወድያው እሞታለሁ
የልቤን ያንጀቴን፤
ልትሰሚኝ ከፈለግሽ
እባክሽ አዋሪኝ፤
አይንሽን ጨፍነሽ

               🌸SHARE AND JOIN🌸


       ,,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,,
                  •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
        ,,,,,,📩
━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━
     


ብለህ ንገራቸው❤️
==========
ሲከፋህ ተከፍታ😒 ስትስቅ የምትስቀው
ባንተ ደስተኛ ፊት የምትፈነድቀው
ስትታመም ታማ ጎንህ የምትሆነው
ቆይ ምንህ ብትሆን ነው

በሷ ስሜቶች ልክ ቀንህ የሚለካዉ፤
ሀዘኗ ጠውልጓ በሳቋ ሚፈካው፤
ብለው ሲጠይቁህ ሴጣን አሳስቶህ፤
ፍቅረኛዬ እንዳትል🙅 ምናልባት ተስቶህ፤
ይልቁንስ ውዴ እሷ ማናት ሲሉህ......

ንግግር ስትጀምር ከመካከላቸው
ስለኔ መጠየቅ ከሆነ ስራቸው
የዘላለሜ ናት ብለህ ንገራቸው
ምንህ ናት ያሉህ ለት
"ሚስቴ ናት"በላቸው


ላንተ ብቻ አልተዘጋጀም!

ህይወት የምልልስ መንገድ ነች ። የከፍታውና የዝቅታው መንገድ ምልልስ ፣ የመጎዳትና የመንፃት ምልልስ ፣ የመሰበርና የመጠገን ምልልስ ፣ የማዘንና የመደሰት ምልልስ ። ስለዚህም ነው የነዚህን ምልልስ አይቀሬነት ተገንዝቦ ችግሮችን ከማጉላትና በደስታም ጫፍ ከመንካት መቆጠብ አስፈላጊ የሆነው ። የዝቅታ ጊዜያት ፣ የመረበሽ ወቅቶች የሚባሉት የፍራቻ ፣ የሃዘን ፣ የመገለል ፣ የመጎዳት ፣ የመቸገር ፣ የመሰቃየትና አስጨናቂ ጊዜያት እንዲሁ መጥተው የሚሔዱና የተለመዱ (normal) የሚባሉ የህይወት ክስተቶች ናቸው ። ብቻህን መፍታት ያልቻልከው ችግር ካለ እርዳታ ጠይቅ ፣ እንቅልፍ የሚነሳህ አስጨናቂ ሃሳብ ካለብህ ለልብ ወዳጅህ ተንፈስ በል ፣ እንደ ከባድ ጭነት የከበደህ ሸክም ካለብህ ለአምላክ አዋየው ፣ ለእርሱ አስረክበው ፣ በእርሱ ላይ ጣለው ። ያንተን ችግር በማቅለሉ የሚመፃደቅ አምላክ እንዳልሆነም አስታውስ ።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተን መርጦ አልመጣም! ላንተ ብቻ አልተዘጋጀም ፣ አንተ ላይ ስለሆነ ብቻ ተዓምርና የማይሆን አይነት ነገር እንዳይመስልህ ። ማንኛውም ሰው እንደሚወድቀው ትውድቃለህ ፣ እንደማንኛው ሰው ትሰበራለህ ፣ ተስፋ ትቆርጣለህ ፣ ታዝናለህ ። ማንም እንደሚሆነው ትከዳለህ ፣ ትናቃለህ ፣ ትገፋለህ ። ይህ ሁሉ ግን አንተ ላይ ብቻ የተከሰተ እንዳልሆነ አስታውስ ። በሰወኛው ባህሪ ለብቻ ከፍ ማለት እንጂ ለብቻ መጎዳትን አንወድ ይሆናል ። ነገር ግን የሰውነት ማንነታችን ማለፍ የሚገባንን አስቸጋሪና አስከፊ ጊዜም እንድናልፍ ያደርገናል ። በውስጣችን የገነባነው ጠንካራው ስብዕና ወደፊት ያሻግረናል ።

አዎ! የሆነብህ ፣ የደረሰብህ ፣ እየሆነብህ ያለው ሁሉ አዲስ አንዳልሆነ አስተውል ። አመጣጡ ያንተ መዳረሻ እርሱን አልፈህ ፣ እርሱን ተሻግረህ የምትደርስበት መሆኑን ለማስገንዘብ እንደሆነ እወቅ ። መጨነቅህ ፣ ማዘንህ ፣ ተስፋ ማጣትህ አዲስ አይደለም ፤ ሰው ነህና ከእነዚህ ከባድ ሁኔታዎች መንፃት አትችልም ። ከመጡ ቦሃላ ግን ማንፃትና ማስተካከል ትችላለህ ፤ ከእነርሱ ነፃ መውጣት ትችላለህ ። በነገሮች መበላሸት አትደነቅ ፣ በእቅድህ አለመሳካት እትረበሽ ፣ በሚያስጨንቁና በሚያናድዱ የህይወት አጋጣሚዎች የውድቀትና የበታችነት ስሜት አይሰማህ ፣ ብዙ እንቅልፍ አልባ ምሺቶችን ማሳለፍህ ፣ ረፍት አልባ ጊዜያት ውስጥ መገኘትህ የማይታመንና ይበልጥ ጫና ውስጥ ከከተተህ ማመንንና መቀበልን የመጀመሪያ አማራጭህ አድርገው ። ለብቻ የመብሰልሰልን ፣ በውስጥ የመያዝን ፣ በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገር መፍራትን እንመፍትሔ መቁጠር አቁም ። ካንተ ችግር በላይ አሳልፈው ዛሬም ደስተኛ የሆኑ ሰዎች እንዳሉ አስታውስ ። እንዲያልፍ የፈቀድክለት የትኛውም ከባድና አስቸጋሪ ጊዜ ያልፋልና በማካበድና ብዙ በመጨነቅ ስሜትህንና ጊዜህን አታባክን ።


​​​​​​​​​​💗🤍    አንቺን ያጠሁ ለታ    🤍💗

አንድ እውነት ልንገርሽ ስሚኝማ ውዴ
አንቺን ያጣሁ 'ለታ ከበፊት መውደዴ
     ሲቃዬም አይሎ
     እስትንፋሴ ግሎ
ጭንቀቴ ይጨምራል
የናፍቆቴ ልኬት ከመጠኑ ያልፋል

    አዎ ውዴ አንቺን ያጣሁሽ 'ለታ .......

ደግሞ ስትናፍቂኝ ሀገር ይጠበኛል
ከአንደበቴ ቃላት ማውጣት ይጨንቀኛል
     የማወራው ሁሉ ግራ ይገባኛል
     በቀን በጠራራ ለኔ ይጨልማል
ማታም በጨረቃ
ድንገት እያነቃ
     ተነስ ተነስ ተነስ ብረርና
     ካለችበት ደርሰህ እቅፍ አርጋትና
ናፍቆትህ ይውጣለህ
ሳማት እንደልብህ
      ይለኛል መንፈሴ
      እስክትወጣ ነብሴ
አዎ የኔ መውደድ አንቺን ያጣው ለታ
ድምፅሽ የራቀለት ከሰማይ ከፍታ
      የቆጡን የባጡን መልሼ መልሼ
      በሀሳቤ ቅኝት ሁሉን አዳርሼ
ደግሞ ምንአገኛት ምን ሆናነው ፍቅሬ
በናፍቆት ልትቀጣኝ የጠፋችው ዛሬ
      ብዬ አስባለው አገኝሽ ይመሥል
       ከምናቤ ጓዳ ካንቺጋ ስዋልል።
ያለፈን ትዝታ እያነሳው ስጥል
በሳቆችሽ ድምፀት ደግሞ ፈገግ ስል
       ከተጓዝኩት ዓለም ከምናብ ስነቃ
       ትውስ ይለኝና የናፍቆቴ ሲቃ
ስብር ስብርብር እያለ መንፈሴ ሲከዳ
ቃልሽ ሲሆን ብርታት የእምነቴ እዳ
       በዝምታ ልሳን በመጥፋት አለንጋ
       ሲገርፈኝ ያደረው ናፍቆትሽ ለሊቱ እስኪነጋ
ለቀን ይጥለኛል እንቅልፌን ሳልተኛ
ለፀሐዩ ግለት አድርጎ ተረኛ
      ዳግም ሊያዋትተኝ ባይን እያስማተረ
      ድምፅሽን በንፋስ ጭኖ እያመጣ ጆሮ እየቀሰረ
ስሞችም ሲጠሩ ለኔ እያስመሠለ
ሲያሰዞረኝ ይውላል ቀና እያስባለ

     እናም የኔ ናፍቆት :- ......
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
እውነታው ይሄ ነው አንቺን ያጠሁ ለታ
ናፍቆትሽ ሲበዛ ሳቄም ተደብቆ ያልፋል በዝምታ።


    ❣️ ✍️Daniel😑Mak❣️




       ,,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,,
                  •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━
     


🌺 ቅምጥሏ 💋

ቅምጥል አፍቅሬ ፣
ለሷ ተቸግሬ
ኩሽና እንዳትገባ ፣ ካልጋ እንዳትነሳ
ምግብ አብሳይ ቀጠርኩ ፣ ሳስብላት ለሷ

የእንጀራ ጠርዝ ጣቷን ፣ እንዳይቆርጣት ብዬ
አጉራሽም ቀጠርኩኝ ፣ አሳቢ መስዬ

ቅምጥሏን ፍቅሬን ፣ ድንገት ቢያስነጥሳት
ይማርሽ የምትል ፣ ሞግዚት ቀጠርኩላት

የሞልቃቃ ነገር ፣ መጨረሻው አያምር
ቅጥ ያጣውን ፍቅሬን ፣ ውስጤን ስላየችው
ባል ቀጥረህ አምጣልኝ ፣ ብላኝ አረፈችው።
😂😂😂


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏


➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢


አው የሆነ ጊዜ ላይ ትፈተናለህ
አው የሆነ ጊዜ ላይ ብቻክን ትቀራለህ
አው የሆነ ጊዜ ላይ ሁሉም ይተውካል
አው የሆነ ጊዜ ላይ ያመንከው ይከዳካል
አው የሆነ ጊዜ ላይ ገንዘብ ይቸግርካለ
አው የሆነ ጊዜ ላይ በፀና ትታማለሀ
አው የሆነ ጊዜ ላይ ትፈተናለህ ግን ወርቅ እንኳን በእሳት ተፈትኖ ነው ወርቅ ሚሆነው ታድያ ያ ግዑዝ እንኳን እሳቱን ተቋቁሞ ፈተናውን አልፎ ወርቅ ከተባለ አንተ ሰው የተባልከው ከሁሉ የምትልቀው ፍጥርት ይሄን ማለፍ ያቅትሀል????


━━━━━━━✦✿🌹✦━━━━━━━


የናፍቆት ደብዳቤ💌💌
   
     ይድረስ ለማፈቅርህ ለነፍሴ ውድ ሰው
     ባለበስከኝ መውደድ አንጀቴ ለራሰው
    ጤናህ እንደምን ነው ፍቅር እንዴት ይዞሀል?
    ከሳህ ወይስ ጠቆርክ ወይስ ተስማምቶሀል?

    እኔ ክብሩ ይስፋ እንዳስቀመጥከኝ ነኝ
    በየሰከንዳቱ ልቤ ተንሰፍስፎ ፍቅርህ እንደራበኝ

    አሁን አሁንማ...
  እኔ እኔን ክዶ ወዳንተ ከጅሏል
ባለቤቱን ሸሽቶ አንተን አንተን ብሏል
ምን ተሻለኝ ብለህ?ምንስ ምን ይባላል?

አንተን ካላገኘው ልቤም ካልመጣልኝ
ቀልቤም ከኔነቴ አድሮ ካልዋለልኝ
ለከርሞ ፍቅርህን ማየትክን እንጃልኝ።

ግና የኔ ፍቅር ፍርሀት መሳሳቴ ቢሰማኝም ዘልቆ
ተስፋዬ ህያው ነው ዳግም አይሀለው ይሄ ሁሉ አልቆ
እግዜሩም አይጨክን መላውን ሁሉ አውቆ

    እናማ የኔ ባል...
ለኔ 'ናንተ ናፍቆት እስኪወጣ በጋ
ልሰናበትህ ነው ያብቃን ለአይነ ስጋ
ይሄ ቅዠት አልፎ ፅልመቱ ሲነጋ።

ነፍሳችን ተጣብቆ እንደተዋደድን
ሁለታችን በአንድ እንደተገመድን
ዳግም ያሳየኛ...
አፍቃሪዋ ነፍሴ ፈፅማ እንድትድን።
🙏🙏🙏
    ሰላም ሁን ጌታዬ በውድ ግዴታ ፍቅር የገዛኸኝ
    የዘላለም ሚስትህ ያንተው ምርኮኛ ነኝ
💋😘😘😘😘


💔
     አንዳንዴ ልብን❤️ መከተል አይምሮን ማጣት ነው
     እያለቀሰ 😢የሚሞትልህን ትተህ
     እየሳቀ የሚገልህን እንድትከተል ያረግሀል


        አንዳንዴ ደሞ አይምሮን መከተል
        ልብን❤️ ማጣት ይሆንብሀል ፍቅርህን ❣ትተህ
        ፍልስፍናን  እንድትከተል ያረግሀል


     ⊶⊷⊶⊷❍ ♥️የኔ ጌታ♥️ ❍⊶⊷⊶⊷


         ይከፋ ብዬ ጠላቴ
        ከቶ እንዳይሸሽ ደግነቴ
        ደስ እያለኝ ባለኝ ኑሮ
       ያንተ  ፍቅር ተጨምሮ
       ደግነትህ ልዩ መልኬ
ደግነቴ      ላመስግንህ ተበንርክኬ
       ያጣሁት ቢኖር የጎደለብኝ
      እኔ ግን ባንተ ላይ ቅር አይለኝ
      ምስጋና ይድረስህ የጌቶቹ ጌታ
      ላንተ ዘምራለሁ ሁሌም ጠዋት ማታ
               
                  ✍ አይዳ ሀይሉ


       ,,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,,
                  •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
  
    
━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━
     


።።።።።።አጠይቁኝ ይቅር💔።።።።።።

ለምን ሆነ አትበሉኝ አጠይቁኝ ይቅር
ሁሉን ብነግራችሁ ላይገባችሁ ነገር😕
እንዴት አትበሉ ለማወቅ ጓጉታችሁ
ነገሩን ብታውቁ ምንም ላይጠቅማችሁ
አጠይቁኝ እኔን ትላንትስ ብላችሁ
ታሪኬን የዃሊት እያስታወሳችሁ😡
የት ነበርሽ አትበሉ አታብዙ ጥያቄ
የትስ እንደነበርኩ እኔ የት አውቄ
ምላሼን በመሻት ጥያቄ አታብዙ
ዃላ ብነግራችሁ ብዙ ነው መዘዙ
አታድሙት ቁስሌን በሾክ ወጋግታችሁ
የማያባራ ደም ጉድ እንዳይሰራችሁ😔
ዝምታዬ ጎልቶ  ስሜት ካልሰጣችሁ🙍‍♂
አላደክምም ራሴን አንዱም ላይገባችሁ🤦‍♀

ስለዚህ እባካችሁ።።።።።።።

አጠይቁኝ ይቅር የለኝም መልሳችሁ።🤷‍♂🤷‍♀
 
    


#ማርኮኛል❤️

ጥበብ የፈሰሰው ሚያስደንቅ ቁንጅናሽ
ከፍዬ ኣልጨርሰው በዛብኝ ውለታሽ

ማድነቅ ስራ ሆኖኝ ለውቡ ተስጦሽ
ዝምተኛ መሆንሽ ከሰው ኣርቆሽ

ከበራችን ደጅ ሁኜ ኣንቺን ስጠብቅሽ
ልዩ ሁነሽ ኣንቺ እኔን #መማረክሽ🥰

ማራኪዬ ብዬ ኣስውቤ ሰየምኩሽ🤗
ታደልኩኝ ብያለው ሁኜ ጎረቤትሽ😜🥰

     
  ━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━


ወዳጄ

"አታማርር ፣ አትተክዝ ፣ በደረሰብህ ነገር ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ ፣ ክፋ ነገር ደርሶብህ ቢሆን እንኳን ፈጽሞ አትሸነፍ ፣ ለመሰናክል እጅህን አትስጥ። መከራ መከራነቱ ለተንበረከኩለት እንጂ እየተፍገመገሙ ለሚታገሉት መወጣጫ መሰላል ነው።

ስላለህ ነገር አመስግን ፣ ባለህ ነገር ላይ መርካት ካልቻልክ መቼም የተሻለ ነገር አይኖርህም። ደስታ እና እርካታ አመስጋኞች ጋር ናት።

ድሀ ነኝ ብለህ ባሰብክ ግዜ ወደ ታች እይ ፤ ካንተ ይልቅ የከፋ ድህነት እና ችግር ውስጥ ወዳሉት ተመልከት። እነርሱ አንተ ያለህበትን ደረጃ አጥብቀው ይመኙታል። አትጠራጠር ስለ ራስህ ማማረርን አቁመህ ትረዳቸዋለህ።

ደስታህን ፈልገህ አታገኘውም ፤ ጠብቀህም አታገኘውም። ደስታን ፍለጋ ገንዘብክን አታፍስስ ፤ በገንዘብ አተገዛም ፤ ተራሮችን አታቋርጥ ፤ ውቅያኖስን አታቋርጥ ፤ ደስታ በፈላስፎች መራቀቅ ላይም አትገለጥም። ደስታ አጠገብህ ናት ደስታ ፊት ለፊትህ ናት ፤ እርሷን ስትፈልግ አንተን እርሷ ትከተልሀለች።
ደስታ ራስን መሆን ናት ፤ ደስታ ባለህ ነገር መርካት ናት ፤ ደስታ እውነት ናት።



➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢


#በልብህ ውስጥ በርካታ ጦርነቶች ይኖራሉ። ልብህ እጅግ የሚጣረሱ ሀሳቦችን የያዙ ወታደሮች የመስዋትነት አውድማ እንደሆነም አትዘንጋ። ያመንክበት ወታደር ግን ከትግል ሜዳው እንዲያፈገፍግና ከመሀል መንገድ እንዲመለስ አትፍቀድ። ያኔ ነው የመርህ ሰው የምትሆነው።
🥰Share lv


ፍቅር ሁለት እግሮች ካልኖሩት ራሱን ችሎ መቋም አይችልም። የመንከባከብ እግር እና የመከባበር እግር ናቸው...አንዱ አንዱን ካጣ አንካሳ ፍቅር ይሆናል።
─━━━━❤️⊱✿⊰❤️━━━━━─


✨✨❤️‍🩹✨✨
ከሰዎች ጋር ባለህ መስተጋብር ውስጥ መልካም ሰው ሁን። አንተ በዚህ አለም ውስጥ ያለህ አንድ ሰው ብትሆንም በአንዳንድ ሰዎች ልብ ውስጥ ግን ሁለንተና ዓለም ልትሆን ትችላለህ። ለማንም የማያጋሩትን ችግር ላንተ የሚነግሩህና ለህይወት መፍትሄ የሚፈልጉህ ዓለማቸው።


በጣም እንደምትወዳቸው ንገራቸው …
ነገን ማንም አያውቅም፣ ማን እንደሚቆይ፣ማን እንደሚሄድ አናውቅም።
ዛሬ ከአጠጋባችን ያሉ ሰዎች ነገ ይኖራሉ ማለት አይቻልም።
ህይወት አጭር ናት…
🥰🥰😊🥰🥰

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

8 403

obunachilar
Kanal statistikasi