የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 701 ሺሕ 489 ተማሪዎች ይወስዳሉ - የትምህርት ሚኒስቴር
ሰኔ 4/2016 (አዲስ ዋልታ) የዘንድሮ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 701 ሺሕ 489 ተማሪዎች እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ዘንድሮ በሚሰጠው ድብልቅ የ12ኛ ክፍል መልቂያያ ፈተና ላይ መግለጫ ሰጥቷል።
ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን እንደሀገር የአቅም ችግር በመኖሩ ምክንያት ፈተናውን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት አለመቻሉን ተገልጿል።
በመሆኑም የዘንድሮ የፈተና አሰጣጥ በትምህርት ቤቶች አቅም የሚወሰን ይሆናል ነው የተባለው።
የኦንላይን ፈተና ውጤትን በቶሎ በማሳወቅ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ፈተናን ለመስጠት፣ ስህተትን በመቀነስ እና በሌሎችም ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ላይ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።
ከኢንተርኔት እና የመብራት መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ያሉ ስጋቶችን ለመቀነስ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብብር በመስራትና የመብራት መቆራረጥ እንዳይኖር ጀነሬተሮችን በፈተና መስጫ ተቋማት ማሟላት መቻሉ ተገልጿል።
ተማሪዎች ለኦንላይን ፈተና የመፈተኛ ኮምፒውተር እንዲያመጡ ተገደዋል የሚባለው ወሬ እውነትነት የሌለውና ከትምህርት ሚኒስቴር እውቅና ውጪ እንደሆነም በመግለጫው ተነስቷል።
SHARE❤️
https://t.me/+QcLpbg9EiMllODhk