ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትምህርት ተቋማት የሰለጠነ ሰው ኃይል ምንጭ እንዲሆኑ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ተሰማ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ተቋማት መተግበር አለበት ያሉትን መመርያ ማውረዳቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ተቋማቱ መሰረታዊ ለውጥ እንዲደረግባበቸው መታዘዙን የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
ተላለፈ የተባለውን ይኸው መመርያ ከተለያዩ አገራት ልምድ የተቀሰመ የስልጠና አሰጣጥ የትምህርት ሞዴል መሆኑን ተገልጿል።"ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ላይ አስተላለፉት የተባለው የስልጠና ሞዴል ለመሆኑ ምን መሳይ ነው?" ሲል አሐዱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድርን (ዶ/ር) ጠይቋል።
የኢንስቲትዮቱ ዋና ዳይሬክተር ላነሳንላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ "የስልጠና ሞዴሉ ፐብሊክ ፕራይቬት ኮንኔክሽን ይሰኛል" ብለዋል።አሐዱም ይኸው የስልጠና ሞዴል በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ጉብኝት ካደረጉባቸው የሩቅ ምስራቅ አገራት የተቀዳ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ጋር በነበረው ቃለ ምልልስ ለማወቅ ችሏል።
በኢትዮጵያ በርካታ ቁጥር ያለው ወጣት ኃይል ቢኖርም አብዛኛው የሰለጠነና የክህሎት ባለቤት እንዳልሆነ ዶክተር ብሩክ የገለጹ ሲሆን፤ የትምህርት ሞዴሉ ሁነኛ መፍትሔ መሆኑን ተናግረዋል።አክለውም፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክረ ሀሳብ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችል መሆኑንና ተፈፃሚነቱ እንዲረጋገጥ ብርቱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
ይህንን የስልጠና ሞዴል በተመለከተም በሌሎች አገራት ያለውን ልምድ ጠቅሰው፤ "አዋጭነቱን የተረጋገጠለት ነው" ብለዋል።አሁን ላይ በኢትዮጵያ የሙያ ትምህርት ተቋማትን ለማስፋፋት እየተደረገ ያለውን ጥረት ጨምሮ እየተስተዋለ ያለው ውጤት ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ መሆኑ ተነግሯል።ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ቢሆኑ ከቀለም ትምህርት ባሻገር ሙያ ተኮር የትምህርት ዝግጅት እንዲሰጡ እየተመከረበት መሆኑን ከዋና ዳይሬክተሩ ሰምተናል።
Via Ahadu
✅ University News ✅