♡ የኢዮብ መልሱ ♡
በአንድ ቀን ሲነጠቅ ልጆችና ንብረት
አካሉ በቁስል ተይዞ በፀና
ኢዮብ እንዴት ቻለ ለአምላኩ ምስጋና
አምላኬ እንዳያዝን ምነው ዝም በአልኩኝ
ልሳኔ እንዳይጠራ ሞት እና መከራ
ለምስጋና ቆሜ ነገን ዛሬ ልስራ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
እንደምነህ ቢሉት ዘመዶች ከድተውትበሕይወት ገጥሞት የበረታ ፅልመት
ሚስቱ ትታው ሄዳ ልጆች ሞተውበት
ዓይኖቹ በምሬት እንባ አላፈሰሱ
እግዚአብሔር ይመስገን ነበር የኢዮብ መልሱ /፪/
በአንድ ቀን ሲነጠቅ ልጆችና ንብረት
አካሉ በቁስል ተይዞ በፀና
ኢዮብ እንዴት ቻለ ለአምላኩ ምስጋና
በሰጠበት መንደር ሲቆም ለልመናቅን ነገር መናገር ለአፌ ከቸገረኝ
ሚስቱ ሙት ስትለው ጌታን እርገሞ እና
የስንፍናን ነገር አይሰማም ጆሮዬ
ይክሰኛል እርሱ ይችላል ጌታዬ
አምላኬ እንዳያዝን ምነው ዝም በአልኩኝ
ልሳኔ እንዳይጠራ ሞት እና መከራ
ለምስጋና ቆሜ ነገን ዛሬ ልስራ
እግዚአብሔር ይመስገን ቢጎድልም ቢሞላም
ለዓይኔ ሽፋሽፍት እንቅልፍ እንኳን ባጣም
ብዙ እንደነበረው ትናንትና ደጄ
ክፉውንም ደግሞ ይቀበላል እጄ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈