🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟
⭐️ክፍል 🟰2️⃣2️⃣
ባለቤቴ ቀና ብላ አየቻትና ድፍት ብላ ማልቀስ ጀመረች ።
እኔ ትንሽ ለማረጋጋት ሞከርኩ የገጠር ልብስ ስለለበስንና ቆሽሸን ስለታየን በሷ ቤት መርዳቷ ነው አትቀየሚያት ብዬ አፅናናኋትና ወደቤት ተመለስን።
እዚህ ከመጡ ቡሀላ ህይወት በጣም ከባድ ሆነች ሁላችንም ቤት ውስጥ ታፍነን ነው ምንውለው በቀን አንዴ በልተን ሁለተኛ ለመድገም ደሞ ብራችን እንዳያልቅ ተሳቀን ሞትን።
የገጠር ሰው ደሞ እህል ትሪው ላይ ተርፎ ካልተነሳ ሰው የጠገበ ስለማይመስለው እንደልብ መብላትን ለምደናል ።
ባለቤቴ አባትህጋ እንሂድ እሱ ጥሎ አይጥለንም እባክህን ብላ ለመነችኝ መጀመሪያ ላይ እንቢ አሻፈረኝ አልኩኝ ቆይቶ ግን ችግራችን በጣም ሲጠና ሴቷን ልጄን ይዤ ሄድኩኝ ለቤተሰቡ በሙሉ ይቅርታ አቀረብኩኝ ልጄን አስተዋወኳቸው በጣም ወደዷት ፊታቸው እንደመጀመሪያው ባይሆንም ብዙም አልተከፉብኝም ነበር።
ልጄን ሲያዩ ደሞ ውስጣቸው እራራ መሰለኝ በቃ ኑና አንዷ ክፍል ውስጥ ተቀመጡ አሉን እሺ አልኳቸው የዛን ቀን እዛው አደርኩኝና በነጋታው ልጄን እዛው ትቻት ባለቤቴንና ልጆቼን ላመጣ ወደ እንጦጦ ተመለስኩ ።
ስመለስ ባለቤቴ እሳት ጎርሳ እሳት ለብሳ ጠበቀችኝ
ምን እንደተፈጠረ ጠየኳት ያባቷ ወንድም (አጎቷ) የገጠሩ ቤታችንን ሰብሮ ገብቶ እሱ እየኖረበት እንደሆነ እንደነገሯትና ገጠር አሁኑኑ መውረድ እንዳለባት ነገረችኝ ሁለቱ ልጆቻችንን ይዘን እንዳበደ ድንገት ተነስተን ወደ ላም በረት ሄድንና በአራት ሰአቱ መኪና ወደገጠር ሄድን።
ባለቤቴ ንዴቷን መቆጣጠር አቅቷት መኪና ውስጥ እያለቀሰች ነበር የወረድነው ስንደርስ እንደተባለው እቃችንን እንኳን ሳያወጣ ሶስት ልጆቹን ይዞ ገብቶ እልል ያለ ኑሮ እየኖረ አገኘነው ቀጥታ እመቤት ቤት ሄድንና ልጆቹን አስቀምጠን ልናናግረው ወደቤት ሄድን አጋጣሚ ሆኖ ቤት ቁጭ ብሎ አገኘነው ባለቤቴ ንዴቷ ስላልበረደ ጥርሷን ነክሳ እንዴት ብትደፍረኝ ነው ዘግቼ የሄድኩትን በር ካለማንም ፍቃድ ሰብረህ የገባኸው አለችው።
ሰውዬው ቀለል አድርጎ ምቀኛ ስለሆንሽ ነው እንጂ አዲስ አበባ ከሄድሽ ቤቱ ምን ይሰራልሻል እኔ ብኖርበት አይሻልም እንዴ ደሞኮ የወንድሜ መብት ነው ወንድሜ ደሞ ከኔ ነው የወሰደው መሬቱን አላት ።
ነው አለችው አፉን ሞልቶ አዎ አላት መሬት ላይ ምራቋን ተፍታ ጠብቀኝ ብላው ወደ እመቤት ቤት ሄደች እኔ እንደሴት ዝም ብዬ ከኋላ ከኋላዋ እሄዳለሁ።
ቤት ከደረስን ቡሀላ ንዴቷን መቋቋም አቃታት መቀመጥም መነሳትም መተኛትም አቃታት ደጅ ደጁን እንዳየች ቁጭ ብላ ነጋላት ጠዋት ሰማዩ ትንሽ ወገግ ሲል ተነስታ ወደ ህግ ሄደች መጥሪያ ተላከለት ሳይሄድ ቀረ
በተላከለት የቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት አለመገኘቱ ደሞ ህጉን አጠበቀበት እራሱ ፍርድ ቤቱ ህግ ከሳሽ ብሎ ከሰስውና ታጣቂዎችን ላከበት ተይዞ ለህግ ቀረበ ፍርድ ቤቱ የሰው ቤት ሰብሮ መግባት እንደሌባ እንደሚያስጠይቀው የሰው ቤት ሰብሮ ገብቶ እዛ ለመኖር መሞከሩ ደሞ የሰው መብት እንደመጋፋት ስለሚቆጠር ለሰራኸው ወንጀል መታሰር አለብህ ተብሎ ታሰረ።
ልጆቹ ከኛ ቤት ወጥተው አጎታቸውጋ አረፉ እኛም ቤታችን ገባን።
ባለቤቴ የሰውዬውን ልጆች ስታይ ደሞ አንጀቷ አልችል አላት እናት ስለሌላቸው እሱ ብቻውን ነው ሚያሳድጋቸው ያንን ስለምታውቅ እራሷ ዋስ ጠርታ አጠገቧ እንዳይደርስ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ አሰጥታ ከእስር እንዲፈታ አደረገችውና ተፈታ።
ከእስር ቤት ከወጣ ቡሀላ ጭራሽ ይዝትባት ይገላምጣት ጀመር ።
እኔ ካንዴም ሁለቴ በፀባይ ላናግረው ሞከርኩ ሊሰማኝ ስላልቻለ ተውኩት።
የክሱ ጉዳይ 15 ቀን ፈጅቶ ነበር 15 ቀን ሙሉ ልጄን በስልክ እንኳን ሳላገኛት ስለቆየሁ እሁድ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ይዣት ወደገጠር ለመመለስ ከባለቤቴጋ አውርተን ተስማማን ።
ቅዳሜ ቀን ደሞ ባለቤቴ የተጠራችበት ማህበር ነበራትና ሄደች::
እኔ ወንዱን ልጄንና ትንሿን ልጄን ይዤ 12 ሰአት አካባቢ ይዣቸው ከቤት ወጣሁ ብስኩት ገዝቼላቸው ቀስ እያልን በእግራችን እየተመለስን ቤታችንጋ ስንደርስ ድብልቅልቅ ያለ ጩኸት ሰማሁና ልጆቹን በቆሙበት ትቼ እሮጥኩኝ
አውጥታ የባለቤቴ እጅ ላይ አስቀምጣላት ሄደች......
🔻ክፍል ሀያ ሶሥት ነገ ማታ3️⃣🟰3️⃣0️⃣ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtu@Kezerareaction33' rel='nofollow'>be.com/@Kezerareaction333
@Kezerareaction33' rel='nofollow'>https://www.youtube.com/@Kezerareaction33
💗 ጥቁር ልብ 💗